የምርመራ ናሙና ከተወሰደ በሁዋላ ውጤቱ ሳይታወቅ አሽከርካሪዎቹ ሄዱ፤ ውጤቱ ሲታወቅ በስፋራው የሉም። ሰዶ ማሳደድ!!

ሰሜን ሸዋ ዞን የኮሮናቫይረስ ምርመራ ተደርጎላቸው ለቫይረሱ መጋለጣቸው ከተረጋገጠ ሃያ ሁለት ሰዎች ውስጥ አሥራ ስድስቱ የደረሱበት ስላልታወቀ እየተፈለጉ መሆኑን ሃላፊዎች አስታወቁ።

ተፈላጊዎቹ አሽከርካሪዎች በመሆናቸው በሚያልፉባቸው አካባቢዎችና በሚያገኟቸው ሰዎች ላይ ሊደርስ የሚችለው የቫይረሱ መዛመት እንደሚያሳስባቸው ጠቅሶ ዜናውን ያሰራጨው  የአሜሪካ ድምፅ ነው። የሰሜን ሸዋ ነዋሪዎችን ጠቅሶ ዘገባው እንዳለው ሰዎቹ የምርመራ ውጤቱ እስኪታወቅ በማቆያ መቀመጥ ነበረባቸው።

Related stories   ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሳይቲስት - ችግር የመፍታት አቅም እንዳለህ ከተሰማህ ፣ያንን ፍጥነት መቀነስ በእውነቱ መልካም አይደለም

መስፍን አራጌ ሃላፊዎችን ጠቅሶ እንዳለው 79 ሰዎች ምርመራ ሲደረግባቸው። 36 የሚሆኑት ቫይረሱ አለባቸው። ከነሱ ውስጥ 22 የሚሆኑት አሽከርካሪዎች ሲሆን 16 የደረሱበት አልታወቀም። የክልሉ ሃላፊዎች ፍለጋ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *