የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የሩሲያ እና የኢትዮጵያን የንግድ ግንኙነቶችን አልገታም- አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ
በሩስያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የኢትዮጵያን እና የሩሲያን የንግድ ግንኙነቶች አለማስቆሙን ገለጹ።
አምባሳደሩ ከሩስያ የዜና አገልግሎት ጋር በነበራቸው ቆይታ÷ ወረርሽኙ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትብብር አለማስቆሙን ጠቁመዋል ።
በዚህም ሁለቱም ወገኖች የጠበቀ ትብብራቸውን ጠብቀው እየተጓዙ በመሆኑ የሁለቱ አገራት ግንኙነት በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛልም ነው ያሉት ።
የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በቅርቡ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውንአምባሳደሩ አስታውሰው÷ በዚህ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሩሲያ እና የኢትዮጵያ ያላቸው ኢኮኖሚያዊ ትብብርና የንግድ ግንኙነት በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል ብለዋል።
አምባሳደሩ በማሳያነትም “የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አውሮፕላኖች በሳምንት ሁለት ጊዜ“ ከሩሲያ ወደ አፍሪካ ፣ ከአፍሪካ ወደ ሩሲያ በማመላለስ በመስራት ላይ መሆኑን ” አንስተዋል፡፡
ከዚያም ባለፈ በባህላዊ መስክ ያለው ትብብር ጠንካራ ግንኑነት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ጠቁመዋል።
በዚህም ታላቁ የሩሲያ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን በኢትዮጵያም ውስጥ እጅግ ተወዳጅ መሆኑን ጠቁመዋል።
አምባሳደሩ አክለውም ኤምባሲያቸው ከሁለቱም አገራት የተውጣጡ 6 ሺህ ሰዎች የሚሳተፉበት የቪድዮ የንግድ የውይይት መድረክ ማዘጋጀቱን ተናግረዋል።
አምባሳደሩ አያይዘውም በየዓመቱ ሰኔ 6 ቀን የሩሲያ ቋንቋ ቀን በኢትዮጵያም እንደሚከበር ገልጸው÷ ቀኑን “ከሩሲያ ጓደኞቻችን ፣ ተማሪዎች ፣ ፕሮፌሰሮች ፣ የአፍሪካ ማህበረሰብ ጋር በመሆን በጋራ እናከብራለን ብለዋል፡፡
በዚህ ዓመት በወረርሽኙ ምክንያት በአካል መገናኘት ከባድ ቢሆንም ቀኑን በቪድዮ ኮንፈንስ መከበሩን ጠቅሰዋል
ምንጭ፡-የሩስያ ዜና አገልግሎት