የሰኔ 15 / 2011 ዋና ዋና እውነታወች :

* እነ ዶ/ር አምባቸውን፣ እዘዝንና ምግባሩን ከአስር የማይበልጡና የሚታወቁ ወታደሮችን ይዞ የስብሰባ አዳራሻቸው ውስጥ በድንገት ገብቶ የገደላቸውና ያስገደላቸው ብ/ጀ አሳምነው ጽጌ ነው።/ በአይኔ በብረቱ ያየውት እውነታ ነው/

* የእነ ዶ/ ር አምባቸው ግድያ ከፌደራል መንግስት ጋር ለማያያዝ የሚደረገው ጥረት ፍጹም ውሸት ነው።
-የግድያ ወንጀሉን የመፈጸመ ሃሳብና እቅድ የራሱ የአሳምነው መሆኑን አምናለሁ።

* አሳምነውን የባላሃብቶችና የአክቲቪስቶች ግፊት ነው ለዚህ ያበቃው የሚባለውን ሃሳብ ዋነኛ አድርጌ አልወስደውም፣ የአሳምነውን የቆየ ባሃሪ እና በወቅቱ የነበረውን ፍላጎት አወቀው ነበር፣ በወቅቱም አሳምነው እሱ ያሰበውንና የፈለገውን ብቻ የመፈጸም እንጅ የሌላ ሃሳብ የመስማትም ሆነ የመቀበል በባሃሪ አልነበረውም።በርግጥ በተወሰኑ አክቲቪስቶችና ጥቂት ግለሰቦች ስለ አሳምነውን ባልሆነ ሁኔታ የስም ግንባታ ላይ መጠመዳቸው ይታወሳል፣ ያን ግርግር እንደ ጉልበት አይቶታል ብየ አስባለሁ።

Related stories   ቦርዱ ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ የክልል ቢሮዎችን ለመክፈት የሚያስፈልጉ ትብብሮች እንዲደረጉለት ለክልል መስተዳደሮች በድጋሜ ጥሪ አቀረበ

* አሳምነው ከክልሉ አመራር፣ ከአዴፓ አመራር፣ ከጸጥታ አመራሮችና ከዞን ሃላፊወች ጋርም ተግባብቶ መስራት አልቻለም ነበር።

* እኔም ሆንኩ ሌሎች የጸጥታ አመራሮች በግልም በቡድንም ከሚመለከታቸው ጋር ተግባብቶ እንዲሰራ መክረነው ነበር፣ ግን ከሁላችንም ግንኙነቱን እያበላሸ ቀጠለ።

* መደበኛ የቢሮውንና እና የክልሉን የጸጥታ ስራ ከስሩ ያሉትን አስተባብሮ ከላይ ካሉት ጋር ተናቦ መስራት አቆመ፣ በሚመለከተው የጸጥታ የስብሰባ መድረኮች መገኘትም አቆመ።

Related stories   “አንዳንድ አገራት ኢትዮጵያ ከተበታተነች የህዳሴ ግድቡ ሊቆም ይችላል የሚል እምነት እላቸው” – ፕሮፌሰር ተገኝ

* ሁላችንም በነበረው ሁኔታ ደስተኞች ስላልነበርን ቅድሚያ እሱን ለማሳመን ጥረት አደረግን፣ እንደማይሆን ስናውቅ ግን ለሚመለከታቸው የአዴፓ አመራሮች ችግሩን እንዲፈቱና እንዲያስተካክሉ ነግረናል፣ የፖለቲካ አመራሩ ይታዩ የነበሩትን ግልጽ አለመግባባቶችንና ችግሮችን ባለመፍታታቸው ተጠያቂ ያደርጋቸዋል ብየ አምናለሁ።

* አሁን ሶሻል ሚዲያ ላይ በተወሰነ ደረጃ እንደሚገለጸው የሌሎች ሴራ አለበት የሚባለው ዋናው ስራ የባለሙያ ቢሆንም ከአሳምነው ባሃሪና በወቅቱ ከነበረበት ሁኔታ አንጻር ከራሱ ያለፈ ይሆናል ብየ አላምን።

* ሰኔ 12 አዲስ አበባ ላይ የነበረን የጸጥታ ግምገማ አስተማሪ ነበር፣ ብዙ መላላጥ የነበረ ቢሆንም መጨረሻ ግን እሱም የግምገማ ሃሳቡን ተቀብሎት ነበር፣ የሚቀጥለው ሰፋ ያለው የባህርዳሩ የጸጥታ መድረክም በአዲስ አበባው አይነት ሳይሆን የየአካባቢውን የጸጥታ ሁኔታ ለመገምገም የታሰበ ነበር።

Related stories   የትግራይ ረሃብ ድሮም ተደብቆ የኖረ ወይስ አዲስ በሁለት ወር የተፈጠረ? ገለልተኛ ፈራጅ ያጣው አወዛጋቢው አጀንዳ! – ሪፖርት

* የግድያ እቅዱ / ሙከራው / ከባህርዳርም አልፎ ጎንደርና ወሎም ሙከራ ነበር።

* ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በወቅቱ በገፍ እያፈሱ የማሰሩ ድርጊት ተገቢ አልነበረም፣ አሁንም ያለ አግባብ የታሰሩ ስለመኖራቸው አምናለሁ።

በነዚህ እውነታወች ላይ በመመስረት ቀጣይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ በተለያዩ ሚዲያወች ይዠ እመለሳለሁ።
አላማየ እውነታውን ህዝቡ እንዲያውቅና ካለፈው ስህተት ተጸጥተን ወደፊት መልካሙን እንድናይ ነው!!!

ከዚህ እውነታ በማፈንገጥ አሉባልታና በሬ ወለደ ውሸት በመፈብረክ የአማራን ህዝብ አንድነት ለመከፋፈል የሚደረገው ቁማር ማብቃት አለነበር።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *