ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 6 ሺህ 886 የላብራቶሪ ምርመራ 356 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 9 ሺህ 503 መድረሱንም ሚኒስቴሩ ባወጣው ሪፖርት አመላክቷል።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከልም 255 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 48 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 14 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 1 ሰው አፋር ክልል፣ 5 ሰዎች ከሐረሪ ክልል፣ 11 ሰዎች ከድሬ ደዋ አስተዳደር፣ 11 ሰዎች ከሶማሌ ክልል፣ 5 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 4 ሰዎች ከሲዳማ ክልል እንዲሁም 2 ሰዎች ከደቡብ ክልል ናቸው።

Related stories   ህወሓት፤ የኢትዮጵያና ኤርትራ የጋራ ጠላት!

ከዚህ ባለፈ የ4 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 167 መድረሱንም ነው ሚኒስቴሩ በእለታዊ ሪፖርት ያመላከተው።

በሌላ መልኩ በትላንትናው 41 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 4 ሺህ 941 መድረሱም ተገልጿል።

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን 323 ሺህ 932 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 9 ሺህ 503 ደርሷል።

Related stories   አለቃ አጽመ ጊዮርጊስ – የተሳሳተውን የውጫሌ ውል የመረመሩ ጀግና ኢትዮጵያዊ

እስካሁን በኢትዮጵያ 4 ሺህ 941 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገገሙ፤ የ167 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 2 ሰዎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ይታወሳል።

#FBC

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *