የፌዴሬሽን ምክር ቤት እና የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን የተሰጣቸውን አገራዊ ኃላፊነት በትብብር ለመወጣት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።  ስምምነቱን የፈረሙት የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ አቶ አደም ፋራህና የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ዶክተር ጣሰው ገብሬ ናቸው።

በዚሁ ወቅት አፈ-ጉባኤው እንደተናገሩት፤ በአገሪቱ ራስን በራስ ከማስተዳደር፣ ከአስተዳደር ወሰንና  ከማንነት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ ባለማግኘታቸው ለግጭት መንስኤ ሆነው ቀጥለዋል። ይህንን ችግር ለመፍታትና የምክር ቤቱን ሥራ እንዲያግዝ ባለፈው ዓመት የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን በአዋጅ መቋቋሙን አስታውሰዋል።

Related stories   ምርጫ ቦርድ ኢዜማን ጨምሮ ስድስት ፓርቲዎችን የምርጫ ምልክት ቀይሩ አለ፤ ኢዜማ በመላው አገሪቱ ብቻውን እንደሚወዳደር አስታወቀ

በዛሬው እለት የተደረገው ስምምነት ሁለቱ ተቋማት በህገ-መንግሥቱና በአዋጅ የተሰጣቸውን ኃላፊነት ተቀራርበው በቅንጅትና በመደጋገፍ  ለመሥራት ያለመ ስምምነትና ውይይትም ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።

የተደረገው ስምምነት በተቋማቱ መካከል የሚፈጠረውን የሥራ ድግግሞሽ፣ የሃብትና የጊዜ ብክነት ለማስቀረት ያለመ መሆኑን ጠቁመው፤ ተቋማቱ በትኩረት ለመሥራት የጋራ እቅድ ማውጣት እንደሚያስፈልጋቸው ተናግረዋል። የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ዶክተር ጣሰው ገብሬ በበኩላቸው ተቋማቱ  በተሰጣቸው ኃላፊነት ዙሪያ ተቀራርበው ባለመሥራታቸው ጊዜ መባከኑን ተናግረዋል።

Related stories   የትግራይ ረሃብ ድሮም ተደብቆ የኖረ ወይስ አዲስ በሁለት ወር የተፈጠረ? ገለልተኛ ፈራጅ ያጣው አወዛጋቢው አጀንዳ! – ሪፖርት

በቀጣይም በአቅም ግንባታ ስራዎች የጋራ እቅድና የድርጊት መርሐ-ግብር በማዘጋጀት ቅንጅታዊ ሥራዎችን በማጎልበት አገራዊ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ በአዋጅ የተሰጠውን ከአስተዳደር ወሰኖች፣ ከማንነትና ራስን በራስ ከማስተዳደር ጋር የተገናኙ ጥያቄዎችን በማያሻማ መልኩ ለመመለስ የሦስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ አውጥቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስረድተዋል።

”የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት  የምክር ቤቱን ድጋፍና ቅንጅታዊ አሠራር ማግኘት አስፈላጊ ነው” ብለዋል። የመግባቢያ ስምምነቱ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆንና በቀጣይ አፈጻጸሙን የሚከታተል የጋራ ግብረ-ኃይል እንደሚቋቋም ተጠቁሟል።

Related stories   የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር በሚያስችሉ ጉዳዮች ከስምምነት መድረሱን አስታወቀ

( ኢዜአ)

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *