የሶማሌላንድ ከግብጽ ጋር አዲስ ግንኙነት ጀመረች የሚለው ዜና ፈጠራ መሆኑንን አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን ለዛጎል ገለጹ። ዜናውን በማጣመም የሚዘገቡት የፑንት ላንድ አፈ ቀላጤ የሆኑ ሚዲያዎች እንደሆኑም አመለከቱ።

ባለስልጣኑ በኢሜል “ሶማሊላንድ በምንም መስፈርት የኢትዮጵያ ጠላት ልትሆን አትችልም። ይህ በቅርቡ ማረጋገጫ ይሰጥበታል” ሲሉ ነው ያስታወቁት።

በሚኖሴታ በሚኖሩ አማካሪ አማካይነት ለዛጎል ምላሽ የሰጡት የሶማሌላንድ ባለስልጣን ዚያድባሬ የሶማሌላንድን በጀት ሲደበድ ቁጥራቸው አምስት መቶ ሺህ የሚጠጉ ዜጎቻቸው ወደ ኢትዮጵያ አቅንተው እንደነበር ያስታውሳሉ።

“ ማንም ቀና ብሎ ሳያየን ድሬደዋ ኖርን፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ነግደን ሰርተን ያን ጊዜ አሳለፍን። በዛ የክፉ ቀን ወዳጅ የሆነን የኢትዮጵያ ሕዝብ ቤተሰባችን ነው። አንክደውም። ብንክደውም ተጠቃሚ አንሆንም ” ያሉት ባለስልጣኑ፣ ይህንን ዜና የሚያሰራጩት የግብጽና የግብጽ ወዳጅ ሚዲያዎች ሲሆኑ ዋና ምንጫቸው garoweonline.com የሚባለው የፑንትላንድ አፍ የሆነው የዜና ፋብሪካ መሆኑንን አመልክተዋል።

Related stories   "ሬንጀርስ" የሚባል በመሳሪያ የተደገፈ ዝርፊያ የሚፈጽም የማፍያ ቅርጽ ያለው ቡድን በቁጥጥር ስር ዋለ

እሳቸው ይህንን ባሉ ማግስት ኢትዮጵያ በገንዘብ ሚኒስትሯ አህመድ ሸዴ የሚመራ ልዑክ ወደ ሃርጌሳ መላክዋን የአካባቢው ሚዲያዎች ዘግበዋል። እንደሚዲያዎቹ ከሆነ የኢትዮጵያ ልዑክ ወደ ሃርጌሳ ያቀናው ጠንከር ላለ ውይይት ነው።

በሶማሌ ክልል የድንበር ከተማ በሆነችው ቶጎጫሌ ከተማና በበርበራ ወደብ በኩል የሚያገናኘውን መንገድ በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ በ90 ሚሊዮን ዶላር በጀት ተገንብቷል። ኢትዮጵያ በበርበራ ወደብ ላይ የአስራዘጠኝ በመቶ ድርሻ ያላት ሲሆን፣ 250 ኪሎሜትር ርዝመት ያለው ከበርበራ እስከ ቶጎጃሌ የሚደርስ አውራጎዳና የተጀመረውን የኢኮኖሚ ትብብር የሚያሳይ፣ ዘላቂ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ እንደሆነ በተለያዩ ወቅቶች መዘገቡ የሚታወስ ነው።

ለዛጎል መረጃ የሰጡት ባለስልጣን ከሳምንት በፊት የግብጽ ልዑክ ሃርጌሳ መምጣታቸውን ባይክዱም ራሳቸውን “ የኢትዮጵያ” እያሉ የሚጠሩ ሚዲያዎች እንደዘገቡት የሆነ ነገር የለም። “ እኔ እስከማውቀው” አሉ ባለስልጣኑ “ እኔ እስከማውቀው የግብጽ የድሮን አውሮፕላኖች ሶማሌላንድ አልመጡም። የተቆፈረ ምሽግም ሆነ የተቆረቆረ የጦር ምሽግ የለም”

Related stories   በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከሃሰተኛ መረጃ ራሳቸውን እንዲጠብቁ ጥሪ ቀረበ፣ የተጭበረበረ መረጃ ተሰራጭቶ ነበር

ወደፊት የሚገለጽ ቢሆንም ሲሉ እንዳመለከቱት መንግስታቸው ኢትዮጵያን ለማተራመስ ከለላ እንዲሰጣቸው ጠይቀው ለነበሩ የተሰጠው ምላሽ “ አታስቡት ” የሚል ሲሆን በድብቅ ገብተው የነበሩም ተለቅመው ለኢትዮጵያ ተሰጥተዋል።

ግብጽ የተለያየ ፍላጎት ማሳደሯ የሚገርም ባይሆንም የሶማሌላንድ ግን ኢትዮጵያን በየትኛውም መንገድ ቅር ሊያሰኝና ሕዝቧን ሊያሳዝን የሚችል አንዳችም ጉዳይ እንደማይኖር ባለስልጣኑ አረጋግጠዋል። ሶማሌላንድ ድረስ መጥተው ለግብጽ የተቆረቆረ የጦር ካምፕም ሆነ የጦር አውሮፕላን ስለመኖሩ መዘገብ ለሚፈልጉ ወገኖች ጥሪ እንደሚደረግም ገልጸዋል።

ሶማሌ ላንድ የአማርኛን ትምህርት በዩኒቨርስቲ ደረጃ የምታስተምር ሲሆን፣ በየዓመቱ  ቁጥራቸው 600 የሚደርሱ ዜጎቿ ኢትዮጵያ ውስጥ ዩኒቨርሲ እንደሚማሩ እንደሚደረግ የሚታወስ ነው።

ዛጎል ባለስልጣኑን እንድታገኝ የረዱት አማካሪ “ ኢትዮጵያ ውስጥ ችግር ቢፈጠር የመጀመሪያዋ ጠፊ አገር ሶማሌ ላንድ እንደሆነች በጥናትና በመረጃ አስደገፈን አስረድተናል። ይህንን ጠንቀቀው ስለሚያውቁ ራሳቸውን ችግር ውስጥ እንደማይከቱ አምናለሁ” ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል። አያይዘውም “ ከሁሉም በላይ ግን ግብጽ የሶአምሌ ላንድን በቋሚነት የምትጠቅም አጋር አይደለችም ” ብለዋል።

Related stories   በትግራይ የፖሊስ አባላት ተሃድሶ ወስደው ወደ ስራ እየተመለሱ ነው

ከስድሰት ወር በፊት ጃዋር መሀመድ ወደ ሶማሌ ላንድ አቅንቶ እንደነበርና በድንበር ላይ ፈቅድ ተከልክሎ እንዶመለስ መደረጉን አማካሪው ጨምረው ገልጸዋል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *