(ኢዜአ) ለረጅም ዘመናት የቆዩ የአደረጃጀት፤የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ ጥረት እየተደረገ ባለበት ወቅት በህወሃት ተልዕኮ አስፈጻሚዎች በኩል የክልሉን ሰላም ለማወክ የሚደረገውን ሴራ በንቃት ማክሸፍ እንደሚገባ የደቡብ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

የጽሕፈት ቤት ኃላፊው አቶ ጥላሁን ከበደ ሃዋሳ ላይ እየተካሔደ ባለው የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ የአመራሮች መድረክ ላይ እንደተናገሩት ህወሃቶች የክልሉን ሰላም ለማወክ ለዓላማቸው ማስፈጸሚያ የሚሆኑ የአመራርነት ሚና ያልገባቸውን አካላት እየተጠቀሙ ነው።

“በመሆኑም ለለውጥ አደናቃፊ ሃይል መጋለቢያ ፈረስ መሆን አይቻልም” ያሉት አቶ ጥላሁን “በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች በአመለካከትም ሆነ በተግባር አንድ ላይ በመሆን የለውጥ ሂደቱን ውጤታማ ማድረግ የሚያስችል ቁመና ላይ የደረሰ አመራር ለመፍጠር በትኩረት ይሠራል”ብለዋል።