Share and Enjoy !

Shares

በተለያየኡ ስሞች ከሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አንዱ የሆነው ኦነግ ሸኔ አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱ ዛሬ ማለዳ በሰበር ዜና ተሰማ። ስብሰባውን የጠሩት ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ አራርሶ ቢቂላ ሲሆኑ ስብሰባው በድርጅቱ ቀጣይ ህልውና ላይ ለመምከር እንደሆነ ታውቋል። ሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ እያሉ ምክትላቸው ስብሰባውን መጥራታቸው የአቶ ዳውድን የወደፊት እጣፈንታ አነጋጋሪ አድርጎታል።

ኸግሬ ኒውስ ኔትዎርክ አቶ አራርሶን ጠቅሶ እንደዘገበው ስብሰባ በአስቸኳይ እንዲካሄድ ትዕዛዝ ሰጥተዋል። የድርጅቱ መሪ አቶ ዳውድ እያሉ ምክትላቸው ስብሰባውን እንዲጠሩ አስገዳጅ የሆነውን ጉዳይ ዘገባው አላብራራም። ይሁን እንጂ አቶ ዳውድ ኢብሳ ስራ መስራት አለመቻላቸውን ጠቁሟል። ስራ መስራት ያልቻሉበትን ምክንያት ግን ነቅሶ አላቀረበም። ዛሬ ማለዳ ቢቢሲ እንዳለው ቤታቸው ተከቧል። ፖሊስ ለድህነታቸው ሲል ጥበቃ እያካሄደ መሆኑንን አቶ ገዳ ኦልጅራ ነገሩኝ ሲል አስታውቋል። ዘገባው እንዳስረዳው አቶ ዳውድ ጋር ማንም መግባት አይችልም። ስልካቸው ዝግ ነው። ጉዳዩ ልደህንነታቸው ሲባል የተደረገ አይመስልም።

Related stories   ሱዳን ባዘጋጀው መድረክ የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ልዩነት በሰላማዊ መንገድ መፈታት እንዳለበት አምባሳደሩ አሳሰቡ

የሃረርጌ ተወላጅ የሆኑትና በውጊያ መሪነት ኦነግ ውስጥ በግንባር ቀደምትነት እንደሚጠቀሱ የሚነገርላቸው አቶ አራርሶ ” በድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት አስቸኳይ ስብሰባ መጥራት መብቴ ነው” ማለታቸውን ሚዲያው አስታውቋል። ይህንን ምላሽ የሰጡት ለምን ስብሰባውን እንደጠሩ ተጠይቀው ይሁን አይሁን በዘገባው አልተገለጸም። ከሁኔታው መረዳት እንደሚቻለው ግን አመራር ለውጥ የማካሄድ ይመስላል።

አቶ ዳውድ የድርጅቱን ስራ ለምንና እንዴት እንደወትሮው ማንቀሳቀስ እንዳልቻሉ ያላብራራው ዜና፣ የድርጅቱ የዕለት ተዕለት ስራ መጓተቱንና መቀዛቀዙን አመልክቷል። አቶ ዳውድ ምን አልባትም የቁም እስረኛ ይሆናሉ የሚል ግምት ሰጥቷል።ይህ እስከታተመበት ጊዜ ድረስ ራሳቸው አቶ ዳውድም ሆኑ ድርጅታቸው የቁም እስረኛ ስለመሆናቸው በይፋ አላስታወቁም። ኦነግ ሸኔ አባላቶቹ እንደታሰሩበት በተደጋጋሚ ሲናገር ሊቀመንበሩን አስመልክቶ ቁርጥ አድርጎ የገለጸው ነበር የለም። በዚህ መነሻ አስቸኳይ ስብሰባው በምክትላቸው መጠራቱ ዜናውን ሰበር አሰኝቶታል።

Related stories   ስዩምና አባይ ጨምሮ የጁንታው ቀንደኛ አመራሮች ተደመሰሱ፣ ደብረጽዮን እጅ እንዲሰጥ ተከቦ 24 ሰዓት ተሰጥቶታል

የኦነግ ሸኔ አስቸኳይ ስብሰባውን ጉለሌ በድርጅቱ ጽህፈት ቤት እንደሚካሄድ ታውቋል። ከድርጅቱ ስራ አስፈጻሚዎች መካከል ስብሰባውን ለማካሄድ የሚያስችል አባላት እንደሚገኙም ተሰምቷል። በዋናነት አጀንዳዎቹ ይፋ ባይሆኑም አዲስ ውሳኔ እንደሚጠበቅ ዛጎል ዜና ሰምቷል።

አቶ ዳውድ ከገዳ ስርዓት አሰራር ውጪ ከስምንት ዓመት በላይ ድርጅቱን መምራታቸው ቅሬታ ሲያስነሳባቸው የቆየ ጉዳይ ነው። እሳቸው እያሉ በምክትላቸው ዛሬ የተጠራው ስብሰባ ይህንን ጉዳይ ስለማንሳቱ የታወቀ ነገር ባይኖርም ” ስራ መስራት አልቻሉም” ማለት ስምምነት ከሌለ በቀር ስብሰባ ለመጥራት የተለመደ ምክንያት እንዳልሆነ አስተያየት ተሰጥቷል።

አቶ አራርሶ ከተከፋፈሉት የኦነግ ድርጅቶች በተለይም ከኦነግ ዩኒቲ ጋር መልካም ግንኙነት ያላቸው እንደሆነ ስለእሳቸው የሚያውቁ ይናገራሉ። አቶ ዳውድ ተቀራርቦ በመስራት የሚያምኑንና ጽንፍ የያዘ አቋም የማያራምዱ እንደሆነም ታውቋል።

Related stories   ስብሃት ጨምሮ ፍርድ ቤት የቀረቡ ተጠርጣሪዎች " ጥፋተኛ አይደለንም፣ መከላከያ ሰራዊት ዋሻ ውስጥ ተደብቀን ያዘን" አሉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *