ኢትዮ ቴሌኮም በ2012 በጀት ዓመት 47 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ። የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ ዛሬ በተቋሙ የ2012 በጀት ዓመት አፈጻጸም ዙሪያ በሰጡት መግለጫ ድርጅቱ 47 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ አግኝተናል ብለዋል።

ከትርፉ ላይም 11 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ግብር ከፍያለሁ ያለው ኢትዮ ቴሌኮም 318 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር እዳንም ከፍያለሁ ብሏል። የውጪ ምንዛሬ ከሚያስገኙ አገልግሎቶች ደግሞ 147 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር ገቢም መገኘቱ ተገልጿል።

Related stories   The National Movement of Amhara(NaMA) Denounces International Violations of the Sovereignty of Ethiopia

እንደ ወ/ት ፍሬህይወት የተገኘው ትርፍ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ31 ነጥብ 4 መቶ ብልጫ አለው ። በአጠቃላይ የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ቁጥር 46.2 ሚሊዮን ደርሷልም ብለዋል።

የሞባይል ድምፅ ደንበኞች ብዛት 44.5 ሚሊዮን፣ የዳታ እና የኢንተርኔት ተጠቃሚ 23.8 ሚሊዮን፣ የብሮድባንድ ደንበኞች ብዛት 212.2 ሺ እንዲሁም የመደበኛ ስልክ 980 ሺ ደንበኞች አሉትም ተብሏል።

Related stories   Speaking Truth to Power, Samantha: Stop Defending Ethiopia’s “Proud Boys”!

ለማህበራዊ ሀላፊነት 1 ነጥብ 15 ቢሊየን ብር ወጪ ያደረገው ኢትዮ ቴሌኮም ከዚህ ውስጥ 792 ሚሊየን ይህሉን ብር ለኮቪድ19 ወረርሽኝ መከላከያ በዓይነት እንዲሁም በገንዘብ የተደረግ ድጋፍ ነው።

ኢትዮ ቴሌኮም 36 ሺ ቋሚ እና ጊዜአዊ ሰራተኞች ያሉት ሲሆን ምርትና አገልግሎት ለደንበኞች የሚያደርሱ ደግሞ 249 ሺህ አከፋፋዮች እና 624 አጋሮችም አሉኝ ብሏል።

ፎቶ ካፒታል ጋዜጣ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *