Share and Enjoy !

Shares

በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ፣ ዝዋይ፣ አርሲ፣ ባሌ፣ ሐርርጌና የተለያዩ በስም ባልተጠቀሱ አካባቢዎች በብሄራቸውና በእምነታቸው ምክንያት የተገደሉ፣ ጥቃት የደረሰባቸው፣ ንብረታቸው የወደመና በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ዜጎች ጉዳይ ከኢትዮጵያ ወጥቶ ዓለም አቀፍ አጀንዳ የሚሆንበት ወቅት ሩቅ እንደማይሆን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ እማኞች ለዛጎል ጠቆሙ።

ተቀማጭነታቸው አውሮፓ የሆኑና በሰብአዊ መብት ዙሪያ ከሚሰሩ ድርጅቶች መካከል ዛጎል በአንዱ በመርማሪነትና አጥኚነት የሚሰሩትን ዛጎል አነጋግራ ነበር። ለጊዜው በይፋ መግለጫ መስጠት የሚቻልበት ደረጃ እንዳልተደረሰ በመጥቀስ መልስ ሲሰጡ ” እኛን ጨምሮ የተለያዩ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ኢትዮጵያ ውስጥ የተካሄደውን አስደንጋጭ ክስተት እየመረመርን ነው” ብለዋል።

የአውሮፓ ህብረት አቋም የሚይዘበት ደረጃ መድረሱን ያስታወቁት አጥኚው በንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈጸመው ጥቃት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ መረጃው ደርሷቸዋል። ያሰማሯቸውን አካላት በስም መጥቀስ አልፈለጉም እንጂ ተጎጂዎች ቃላቸውን በተለይ እንዲሰጡ ተደርጓል። ይፋ ከወጡት በተጨማሪ በተለይ እነሱ እጅ የገቡ መረጃዎች መኖራቸውን አመልክተዋል።

Related stories   አባይ ወልዱና ዶ/ር አብርሃም ተያዙ፤ የአገር መከላከያ ሰራዊትን ከሃጂ ጀነራሎችና መኮንኖች ከነጭፋራቸው ተደመሰሱ

ለወትሮው ኮሽ ሲል መግለጫ የሚያወጣው ተቋም ስለምን ዝም እንዳለ እንዲያብራሩ ሲጠየቁ ” የአሁኑ እጅግ አስደንጋጭና በጥምር የሚሰራ፣ የጠነከረ ፍትህ የሚጠየቅበትና ጉዳዩ ዓለም ባስቀመጠው የህግ ማዕቀፍ መታየት ስላለበት ነው” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ይህንን ሲሉ ወንጀሉ በምን እንደሚፈረጅ ግን ፍንጭ መስጠት አልፈለጉም።

ድርጅታቸው ያሰማራቸው ወገኖች፣ በድርጅቱ አሰራር መሰረት በሚስጢር መረጃ ሰብስቦ ምርመራ ላይ እንደሚገኝ ያወሱት አጥኚው በይፋ ገብተው መረጃ እንዳይሰበስቡ ስለመከልከላቸው ተጠይቀው ” አልጠየቅንም” ብለዋል። ይሁን እንጂ መረጃውን በለመዱት አሰራር ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ እጃቸው እንደገባ አልሸሸጉም።

አውሮፓ ህብረትን ጨምሮ ታላላቅ አገራት ከሪፖርቱ ይፋ መሆን በሁዋላ አቋማቸውን ይፋ ያደርጋሉ የሚል እምነት እንዳላቸው አመልክተዋል። ሪፖርቱ መቼ ይፋ እንደሚሆን ለተጠየቁት ” በቅርብ” ከማለት ውጪ ቀን ቆርጠው አልተናገሩም። አጥኚው ስለ ኢትዮጵያ ጉዳይ በተከታታይ ሲያጠኑ እንደነበር ዝግጅት ክፍላችን ያውቃል።

Related stories   በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከሃሰተኛ መረጃ ራሳቸውን እንዲጠብቁ ጥሪ ቀረበ፣ የተጭበረበረ መረጃ ተሰራጭቶ ነበር

ባለፈው ሳምንት “ኢትዮጵያ በተመድ የጄኖሳይድ ፍኖተ ካርታ እንድትሰፍር አየተሰራ ነው ፤ ጄኖሳይድ አልተካሄደም ማለት ከሰውነት ደረጃ መውረድ ነው” በሚል ርዕስ ተመሳሳይ ዜና መዘገባችን የሚታወስ ነው። በዜናው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ጉዳዩን እየመረመሩት መሆኑ ተጠቁሞ ነበር። ዛጎል ይህንኑ መነሻ አድርጎ ነው አጥኚውን በቅርብ በማግኘት ያነጋገረችው።


አስተያየትዎን ይጻፉልን አድራሻችን

በኢትዮጵያ ዙሪያ በብቃት እንድንሰራ ይርዱንየአቶ ልደቱ አያሌው የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደረገ

“ኢትዮጵያ በተመድ የጄኖሳይድ ፍኖተ ካርታ እንድትሰፍር አየተሰራ ነው ፤ ጄኖሳይድ አልተካሄደም ማለት ከሰውነት ደረጃ መውረድ ነው”

የሽመልስ አብዲሳ ከአስር ወር በፊት የተደረገ ንግግር ዛሬ ለምን ይፋ ሆነ? ከብልጽግና አባል የተላከ ማስታወሻ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *