ባለፉት ቅዳሜና እሁድ ለሁለት ቀናት ከተመሰረተ የመጀመሪያውን ኮንፌረንሱን ያካሄደው የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማስተላለፍ ነው ትናንት ማምሻውን ስብሰባውን ያጠናቀቀው።

በዚሁ ኮንፌረንስ ከተላለፉ ውሳኔዎች በትልቁ ትኩረት የሳበው ጉዳይም ከወራት በፊት በፓርቲው ተሳትፎያቸው እየደበዘዘ የመጣው፤ አሁን ሃገርን እያስተዳደረ ላለው የለውጥ መንግስት ስኬታማነት ግን የአንበሳውን ድርሻ ተጫውቷል የሚባልላቸው የአቶ ለማ መገርሳ እና ሌሎች ሁለት የፓርቲው አመራሮች ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት መታገድ ነው።

የኮንፌረንሱን መጠናቀቅን ተከትሎ መግለጫ የሰጡት የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ኮንፌረንሱ ፓርቲውንና ፓርቲው የሚያስተዳድረውን ክልል አጋጥሞታል በሚል እንደ ክፍተት ከገመገማቸው ጉዳዮች አንደኛው የአመራሮች በኃላፊነታቸው ልክ አለመስራት መሆኑን ጠቁመዋል።

በዚህም “በየደረጃው ያሉት አመራሮች ተጨባጭ ውጤት ከማስመዝገብ ይልቅ አውርተው የመኖር አዝማሚያ መስተዋሉ ተገምግሟል” የሚሉት የጽህፈት ቤት ኃላፊው በቅርቡ በክልሉ ከተፈጠረው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ ክፍተት አሳይተዋል የተባሉ ከ800 በላይ የወረዳ፣ እንዲሁም 117 የዞንና ከተማ አስተዳደር አመራሮችን ለማጥራት መታሰቡን አስረዱ።

መሰል ውሳኔ በታችኛው የአመራር እርከን ብቻ መቆም የለበትም የሚል ሃሳብ ከአባላቱ ተነስቷል ያሉት አቶ ፍቃዱ ተሰማ በተደረገው ግምገማ ለጊዜው ሶስት የድርጅቱ የበላይ አመራሮች ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ታግደዋል። ከነዚህ መሃከል አንደኛው የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንትና የአሁኑ የመከላከያ ሚንስትር አቶ ለማ መገርሳ ናቸው።

Related stories   የትግራይ ረሃብ ድሮም ተደብቆ የኖረ ወይስ አዲስ በሁለት ወር የተፈጠረ? ገለልተኛ ፈራጅ ያጣው አወዛጋቢው አጀንዳ! – ሪፖርት

Subscribe to our newsletter!

[newsletter_form type=”minimal” lists=”undefined” button_color=”undefined”]

የጽህፈት ቤት ኃላፊው አቶ ፍቃዱ ተሰማ አቶ ለማ መገርሳ ከማዕከላዊ ኮሚቴው የታገዱበትን ምክኒያት ሲያስረዱም፤ “ጓድ ለማ በአንድ ወቅት ሃሳባቸውን በሚዲያ መግለጻቸው ይታወሳል። ያንን ተከትሎ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በጉዳዩ ላይ ከመከረ በኋላ እሳቸውም ተሳስቻለሁ ብለው ይቅርታ ጠይቀው ነበር። ከዚያም በአመራርነታቸው እንዲቀጥሉ ተደረገ። ይሁንና በብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚም ሆነ ማዕከላዊ ኮሚቴ እንዲሁም ኃላፊነቱን ሰጥቶአቸው የነበረውን አካል ወክለው ድምጽ እንዲያሰሙ ቢጠየቁም ያን አላከበሩም። ይህ ደግሞ በፓርቲው መተዳደሪያ አሰራር ክልክል በመሆኑ የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች ጉዳዩን ካዩት በኋላ እኚ ሰው ምንም እንኳ አገራዊ ለውጥ በማምጣት ሂደት ውስጥ ትልቅ ክብር የሚገባቸው ቢሆኑም፤ ማንም ከፓርቲውና ከኦሮሞ ህዝብ በላይ ባለመሆኑ፣ በዚህ ኮንፌረንስ ላይም እንዲሳተፉ በተደጋጋሚ ተጠይቀው መሳተፍ ባለመቻላቸው፣ ሃሳባቸውንም ዴሞክራሳዊ በሆነ መንግድ ወደ መድረክ ለማቅረብ ፈቃደንነትን ባለማሳየታቸው፣ ለጊዜው ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ታግደዋል” ብለዋል።

አቶ ለማ መገርሳ እንደ ክፍተት የተነሳባቸውን ነጥቦች ለማስተካከል ፈቃደኛ ሲሆኑ ወደ የፓርቲው አመራርነት መመለስ እንደሚችሉ ውሳኔ ላይ መደረሱም ነው የተገለጸው። ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት የታገዱ ሌሎች የፓርቲው አመራሮች ዶ/ር ሚልኬሳ ሚዴጋ እና ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን ናቸው።

Related stories   የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር በሚያስችሉ ጉዳዮች ከስምምነት መድረሱን አስታወቀ

አቶ ፍቃዱ ለእነዚህ አመራሮች መታገድም ምክኒያቱን ሲያስረዱ፤ “ዶክትር ሚልኬሳ ሚዴጋ የፓርቲውን አሰራር ጠብቀው እዲሳተፉ ብጠየቁም መፈጸም ስላልቻሉ፣ ያላቸውን የሃሳብ ልዩነትም በፓርቲው ውስጥ ማንጸባረቅ ሲችሉ ወደ ውጪ በመውሰዳቸው በፓርቲው ደምብ መሰረት በአመራርነት ሊያስቀጥላቸው ባለመቻሉ ነው ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት የታገዱት።

በርግጥ ይህ ጉዳይ በቀጣይነት በብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሚረጋገጥ ነው የሚሆነው። ወ/ሮ ጠይባ ሀሰንም በተለያዩ መንገዶች ኃላፊነታቸውን ሲወጡ ብቆዩም ከአባላቱ በተነሳው ሃሳብ መሰረት በተለያዩ አከባቢዎች በተፈጠሩ ችግሮች ላይ በእጅ አዙር ተሳትፈዋል የሚል ጥርጣሬ ስለተፈጠረ ጉዳያቸው እስኪጣራ እሳቸውም ታግደዋል” ነው ያሉት።

ኮንፌረንሱ የፓርቲው ውስጣዊ ችግር ነው ብሎ የገመገመው ሌላው ጉዳይ የአመራሮቹ የተለያዩ ቦታዎችን መርገጥ ነው ተብሏል። ችግሩ በየአመራር እርከኑ በሰፊው የተስተዋለ ቢሆንም በርካቶቹ ህሳቸውን አውርደው በቀጠይነትም እንደሚሰራበት ነው የተጠቆመው። ሌላው በየደረጃው ያሉ አመራሮች ይታሙበታል የተባለው የሌብነት ጉዳይ እንዲለዩና ማስተካከያ እንዲደረግበትም አቅጣጫ መቀመጡ ተገልጿል። ውሳኔዎቹ የተላለፉትም በመገፋፋት ስሜት ሳይሆን የፓርቲው አሰራርና የህግ የበላይነትን ለማስከበር በማሰብ ነው ሲሉም አስረድተዋል አቶ ፍቃዱ ተሰማ።

Related stories   “አንዳንድ አገራት ኢትዮጵያ ከተበታተነች የህዳሴ ግድቡ ሊቆም ይችላል የሚል እምነት እላቸው” – ፕሮፌሰር ተገኝ

የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ በኮንፌረንሱ የአርቲስ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን እና ግድያውን ተከትሎ በክልሉ በተፈጠረው አለመረጋጋት በዜጎች ላይ የደረሰውን ጉዳት በማውገዝ “ለውጡን ለማደናቀፍ እየጣሩ ነው” ያሏቸውን ህወሃትና ኦነግ ሸኔን እታገላቸዋለሁ ብሏል።

በሃይማኖት መሃከል የነበሩ ችግሮችን መፍታት፣ ስኬታማ የዲፕሎማሲ ስራ፣ ገጠርን ያማከለ የልማት ፖሊሲ፣ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ከችግር የማውጣት ስራ፣ የጸጥታ ዘርፍ ሪፎርም እና በህዝብ ምጣነ ተሳትፎን የሚፈቅደውና አምስት ቋንቋዎችን ያካተተው የፓርቲ ሪፎርምን ኮንፌረንሱ ስኬታማ ተግባራት የነበሩ ናቸው ሲል ገምግሟል።

©ጀርመን ድምፅ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *