” ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ያልመዘገበው ተቃዋሚ ፓርቲ ” በሚል የተሰየመው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ይቅርታ ጠይቆ ያሰራጨውን የምስል ማስረጃ በቀናት ልዩነት ማንሳቱ እያነጋገረ ነው። መረጃው ሆን ተብሎ እንደተለጠፈና መልሶ እንዲነሳ እነድተደረገ የሚከራከሩ እንደሚሉት የድርጅቱ የምስራቅ አፍሪካ ወኪል የሆኑትን አቶ ፍስሃ ተክሌን ይከሳሉ።

የተሰራጨው የምስል ቪዲዮ ካሃጫሉ ህልፈት ጋር በተያያዘ የተነሳውን ረብሻና ብጥብጥ በከፊል የሚያሳይ ሲሆን እንዲለጠፍ የተደረገው 12.12.12 በሚል ስያሜ ከተጠራው አድማ በፊት ነው። ድርጊቱን የተቃወሙ እንዳሉት አምነስቲ ይህንን ያደረገው ሆን ብሎ አመጹን ለማጋጋል ሲል እንደሆነ አመላክተዋል።

 ከወደቁ ሃይሎች ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል የሚታሙት የድርጅቱ የኬንያ ቢሮ አስተባባሪ አቶ ፍስሃ ተክሌ እጎናቸው ባለው  ቢቢሲ በኩል ወቀሳውን አስመክቶ ማስተባበያ ሰጥተዋል። ይቅርታው ለቀደመው ሪፖርት ሳይሆን በድንገት ተሰራጭቶ በድንገት ስለወረደው የሰዕል መረጃ እንደሆነ አመላክተዋል።

በፖለቲካ ወገንተኛነትና ከወደቁ ሃይሎች ጋር ባለ ግንኙነት ለቀረበው ሪፖርት አምነስቲ ግልጽ ውይይትን አሻፈረኝ አለ

አቶ ፍስሃ ተክሌ ከኬንያ ቀደም ሲል ጀመሮ ሪፖርቱ በበቂ ማስረጃ ታጅቦ የተሰራ መሆኑንና ለትክክለኛነቱ ማስተባበያ የሚቀርብበት እንዳልሆነ በተደጋጋሚ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ሰውየው የማንን አጀንዳ በአምነስቲ ካባ እያስፈጸሙ እንደሆነ የድርጅትና የግለሰቦች ስም በመጥቀስ በርካቶች የሰላ ትችት ሰንዝረውባቸውም ነበር።

Related stories   በትግራይ የፖሊስ አባላት ተሃድሶ ወስደው ወደ ስራ እየተመለሱ ነው

ዓላማው ግልጽ ባልሆነ መልኩ ተለጥፎ እንዲነሳ በተደረገው የስዕል መረጃ ስር በተመሳሳይ አምነስቲ የከፋ ወቀሳና ሃይለቃል የተሞላቸው በርካታ አስተያየቶች የደረሱት ሲሆን፤ እንደ ድርጅት ተዓማኒነቱን ያጣ ስለመሆኑም ተነግሮታል። ለቢቢሲ አስተያየት የሰጡት አቶ ፍስሃ የተሰነዘረውን ተቃውሞ አስመልክቶ ያሉት ነገር የለም።

አምነስቲ በቲውተር ገጹ ይቅርታ የጠየቀው። “የኢትዮጵያውያን ሰብአዊ መብት እንዲጠበቅ እሰራለሁ”  ያለው ተቋሙ “በኢትዮጵያ አሁን ያለውን ፖለቲካዊ ሁኔታም እንረዳለን” ብሏል። መረጃው የተነሳበትን ምክንያት በቢቢሲ በኩልም አብራርቷል።

የአምነስቲ ሪፖርት የመንግስትን ምላሽ አላካተተም፤ ለምን?

አምነስቲ ኢትዮጵያ ድንበር አፍንጫ ስር በተቀመጠው የቀጣናው ሃላፊ አቶ ፍስሃ ተክሌ አማካይነት በዘራቸው፣ ሃይማኖታቸውና አመለካከታቸው ሳቢያ ተለይተው በግፍ ስለተጨፈጨፉና ንብረታቸው ስለወደመ ንጹሃን ዜጎች እስካሁን ያለው ነገር የለም። 

የይቅርታውን አይነት በቢቢሲ በኩል ያስተባበሉት አቶ ፍስሃ ተክሌ  “ተንቀሳቃሽ ምስሉ የኛን የውስጥ ሂደት ሳያሟላ ነበር የወጣው። በዚያ ምክንያት ነው ያወረድነው። ለተፈጠረው ችግርም ይቅርታ ጠይቀናል” ሲሉ መረጃው ከሃጫሉ ግድያ በሁዋላ የነበረውን ግርግር የሚያሳይ እንደሆነ አስረድተዋል። ይሁን እንጂ ለምን ዓላማ መረጃው በዚያን ወቅት እንዲለጠፍ እንደተፈለገ ቢቢሲ አልጠየቃቸውም።

Related stories   «አባ ገዳዎች ያስተላለፉትን ውሳኔ ተቀብሎ ህዝቡ ኦነግ ሸኔን ለማፅዳት በየዞኑ ተግባራዊ እያደረገ ነው»

” የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሰብዓዊ መብት ተቋም ሪፖርት ሚዛናዊነት የጎደለው ነው »የአማራ ክልል መንግሥት

የውስጥ ሂደት ማሟላት ሲሉ ምን ማለት እንደሆነና ምን ታስቦ መረጃው አየር ላይ ሊውል እንደቻለ ቃል በቃል ባይጠየቁም ስህተት ያሉትን እንዲያብራሩ ተጋብዘው “አንድ ለሕዝብ የሚቀርብ ነገር ማለፍ የሚገባው ሂደት አለ። ይሁን እንጂ ቪዲዮ የተወሰኑትን ሳያሟላ በስህተት ተጭኗል” ሲሉ መልስ ሰጥተዋል።

አቶ ፍስሃ አርመጥምጠው ያቀረቡት ማብራሪያ ዋና አላማ ቀደም ሲል የወጣውና ከፍተኛ ተቃውሞ የተሰነዘረበት ሪፖርት ይቅርታ ያልተጠየቀበት መሆኑንን ለማሳየት ቢሆንም፤ ማስተባበያቸው ቀደም ሲል ያቀረቡትን ሪፖርት ሰንካላነት በድጋሚ ያስታወሰ ሆኗል።

ሪፖርቱ ህወሃትን ጨምሮ ለፖለቲካ ፍጆታ ያዋሉት፣ በዚሁ መነሻ በርካታ ቅስቀሳ መካሄዱና አሁን ለተፈጠረው ቀውስ እንደ ማቀጣጠያ ሆኖ ያገለገለ አንድ ግብአት እንደሆነ፣ በተጎጂዎች መብትና ስቃይ ላይ የቆመረ፣ እንዲሁም ሁሉም የአገሪቱ ክልሎች ላይ በሁሉም ወገን የደረሱ ግልጽ በደሎችን ሆን ብሎ የዘለለ፣ በዚህም ሳቢያ ራሳቸውን መንግስት ያደረጉ ያሻቸውን እንዲያደርጉ የልብ ልብ የሰጠ … ሲሉ አምነስቲን የሚከሱ በርክተዋል።

Related stories   በሰሜን የኤርትራና ሶማሊያ ወታደሮች ጣልቃ ገብተዋል መባሉን መንግስት " ፈጠራ የሮኬት ተኳሹ ወሬ" አለው

 

Subscribe to our newsletter!

[newsletter_form type=”minimal” lists=”undefined” button_color=”undefined”]

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *