እነ ኪዳኔ ዘካርያስ በተጠረጠሩበት ህገ ወጥ የሰዎች ዝዉዉር ወንጀል ምስክሮች ቃላቸዉን እንዲቀይሩ ሲያባብሉ የነበሩ አርቲስት ታረቀኝ ሙሉ እና ጠበቃ ደስታ መስፍን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ አስታውቋል።

እነ ኪዳኔ ዘካርያስ በተከሰሱበት ህገ ወጥ የሰዎች ዝዉዉር ወንጀል ላይ በሰዉ ምስክር ማስረጃነት የቀረቡ ስድስት ምስክሮችን በማግባባትና በገንዘብ በመደለል ፍርድ ቤት ገብታችሁ ለፖሊስና ለዐቃቤ ህግ የሰጣችሁትን ቃል ቀይሩ አለበለዚያም ፍርድ ቤት ሳትቀርቡ ጥፉ ይህን ካደረጋችሁ ለእያንዳንዳችሁ 500 ሺ ብር እንሰጣችኋለን ብለዉ በማግባባት ሲያባብሉ የነበሩ አርቲስት ታረቀኝ ሙሉ እና ጠበቃ ደስታ መስፍን በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን ተገለፀ፡፡

Related stories   ኤታማዦርሹሙ ሱዳን ከተደገሰላት የጦርነት ወጥመድ ይልቅ ለዕርቅ ቁርጠኛ እንድትሆን መከሩ

ከላይ በስም የተጠቀሱት ግለሰቦች ከዚሁ ጋር በተያያዘም በተከሳሽ ኪዳኔ ዘካርያስ የወንጀል ድርጊት በሊቢያ ዉስጥ ህይወታቸዉ ላለፈ ኢትዮጵያዉያን ቤተሰቦችም 200 ሺ ብር እንሰጣችኋለን ሲሉ ምስክሮችም ከዚህ በፊት የሰጣችሁትን ይህን ቃል ስትቀይሩም ምንም አይነት የህግ ተጠያቂነት አያስከትልባችሁም በማለት ምስክሮችን ሲያባብሉ የነበሩ መሆኑንም ከምስክሮቹ የድምፅ ቅጅ እንደተገኘም ተመልክቷል፡፡

ሁለተኛ ተጠርጣሪ ጠበቃ ደስታ መስፍን እነ ኪዳኔ ዘካርያስ በተጠረጠሩበት ህገ ወጥ የሰዎች ዝዉዉር ወንጀል ተከሳሽ ኪዳኔን በፍርድ ቤት በጠበቃነት ወክሎ ሲከራከር ቆይቶ በተከሳሽ ጉዳይ የማስረጃ ዝርዝር ላይ የተጠቀሱትን ምስክሮች ከተጠርጣሪ ታረቀኝ ሙሉ ጋር በመሆን ምስክሮቹ ፍርድ ቤት ቀርበዉ ለፖሊስ የሰጡትን የምስክርነት ቃል ቢክዱ የሚመጣባቸዉ ኃላፊነት የሌለዉ መሆኑን፣ በችሎት በዐቃቤ ህግ ሊጠየቋቸዉ የሚችሉ ጥያቄዎች ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ በመግለፅ፣ ፍርድ ቤቱ በሐምሌ 5/2012 ዓ.ም ምስክር ለመስማት ይዞ የነበረዉን ቀጠሮ በማስለወጥ፣ ለምስክሮቹም ይህንን ቀጠሮ ያስለወጠዉ ከምስክሮቹ ጋር ለመደራደር ጊዜ ለማግኘት እንዲያመች መሆኑን በመግለፅ እና ምስክሮቹን በማግባባት ባጠቃላይ ለፍትህ አሠጣጥ ሂደቱ እንቅፋት በመሆን ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ዉሏል፡፡

Related stories   በትግራይ የፖሊስ አባላት ተሃድሶ ወስደው ወደ ስራ እየተመለሱ ነው

በዚሁም መሰረት ተጠርጣሪ አርቲስት ታረቀኝ ሙሉ በቀን 11/2012 በቁጥጥር ስር ዉሎ ጉዳዩ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የወንጀል ችሎት ቀርቦ የ7 ቀን የጊዜ ቀጠሮ የተሰጠበት ሲሆን ጠበቃ ደስታ መስፍን በዛሬዉ እለት በቁጥጥር ስር ዉሏል፡፡ በቀጣዮቹ ቀናቶችም ፍርድ ቤት የሚቀርብ ይሆናል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን

Subscribe to our newsletter!

[newsletter_form type=”minimal” lists=”undefined” button_color=”undefined”]

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *