በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች ቋት በሽብርተኝነት እስካሁን ተመዝግቦ የሚገኘውና በትግራይ መሽጎ የተቀመጠው ህወሓት የተሰኘው የበረሃ ወንበዴዎች ቡድን ነገ ለሚደረገው የፌዴሬሽን ምክርቤት ስብሰባ አጀንዳ ካልተላከልኝ አልሰበሰብም በማለት ነሐሴ 27 ቀን 2012 ዓ.ም ለፌዴሬሽን ምክር ቤት በጻፈው ደብዳቤ አስታውቆ ነበር።

ከዚህ በመቀጠል ደግሞ አገር አስገንጣይ በረኸኞቹ የተከማቹበት ምክርቤቱ በትግራይ ክልል ሊካሄድ የታሰበውን ምርጫ ለማስቆም በፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚተላለፍ ማንኛውም ውሳኔ ጦርነት አዋጅ እንደሚቆጥረው ባወጣው መግለጫ አስታውቋ። ከአሃዱ ሬዲዮና ከቢቢሲ አማርኛ ያወጡትን ዘገባ ከዚህ እንደሚከተለው አቅርበናል።

Related stories   The Forces of Evil Arrayed Against Ethiopia ( (Part I of II)-By almariam

መግለጫው የወጣው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከቀናት በፊት ነገ ቅዳሜ የሚካሄድ አስቸኳይ ስብሰባን መጥራቱን አስመልክቶ ነው።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለአባላቱ ባስተላለፈው ጥሪ ላይ 5ኛ የፓርላማ ዘመን 5ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ አስቸኳይ ስብሰባ ነሐሴ 30/2012 ዓ.ም እንደሚካሄድ ከማሳወቅ ውጪ በምን አጀንዳ ላይ ውይይት እንደሚካሄድ የገለጸው ነገር ባይኖርም፤ የትግራይ ክልል ሥራ አስፈጻሚ በክልሉ በሚካሄድ ምርጫ ላይ የሚሰጥን ውሳኔ እንደማይቀበለው ከወዲሁ አሳውቋል።

Related stories   US Attempt To Make Pronouncements On Ethiopia’s Internal Affairs Regrettable :MoFA

ጎልጉል ዜና 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *