የኢትዮ ቴሌኮም 5 በመቶ ድርሻ ለዜጎች በአክስዮን እንደሚሸጥ ተገለጸ። ኢትዮ ቴሌኮምን በከፊል ወደ ግል ለማዘዋወር እና ተጨማሪ የቴሌኮም ኮርፖሬሽኖችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት የተወሰነው ውሳኔ ሂደት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት ትናንት በተገመገመበት ወቅት ኢትዮ ቴሌኮም በከፊል ወደ ግል ሲዘዋወር 40 በመቶ ድርሻ ለዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ይተላለፋል። አምስት በመቶ ድርሻ ደግሞ ለኢትዮጵያውያን ዜጎች በአክስዮን የሚሸጥ ይሆናል ተብሏል።

ይህ አምስት በመቶ አክስዮን በጥቂት ግለሰቦች የሚያዝ ሳይሆን ሁሉም ዜጋ እንደ አቅሙ የሚሳተፍበት እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ፣ ቀሪውን 55 በመቶ ድርሻ መንግሥት እንደያዘው እንደሚቀጥልም ተመልክቷል።

በኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፉን ለማዘመን የኢትዮ ቴሌኮምን ድርሻ በከፊል ከማስተላለፍ ባሻገር ለሁለት አዳዲስ ኦፕሬተሮች ፈቃድ እንደሚሸጥ ተገልጿል።

ሁለቱ አዳዲስ ኦፕሬተሮች በዓለም አቀፍ ደረጃ ስምና ልምድ ያላቸው እንዲሁም ቴክኖሎጂዎችን የሚያሸጋግሩ እንደሚሆኑም ተጠቁሟል።

Related stories   ሱዳን ባዘጋጀው መድረክ የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ልዩነት በሰላማዊ መንገድ መፈታት እንዳለበት አምባሳደሩ አሳሰቡ

በወቅቱም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ፈቃድ የመስጠትም ሆነ በከፊል የማዘዋወር ሥራዎች ከሌብነት በፀዳ፣ ሙያዊ አካሄድን በተከተለ እና የምናስበውን ጥቅም ለሀገር ማስገኘት በሚችል መልኩ ይከናወናል ብለዋል።

ዘርፉን ሊብራላይዝድ የማድረግ ሂደቱ የፖሊሲ ግፊት የሌለበት ፤ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ የቀረቡ መርሆች እና አቅጣጫዎች ላይ ተመስርቶ የሚተገበር መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

አዲስ ዘመን ጳጉሜን 3/2012

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *