በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ወምበራ ወረዳ ሳንቂና ኤባች በተባሉ ቀበሌዎች ከባለፈው ሳምንት አንስቶ ታጣቂዎች በተደጋጋሚ ጥቃት እያደረሱባቸው መሆኑንን የአካባቢው ነዋሪዎች አስታወቁ ፡፡ በጥቃቱም አራት ሰዎች ተግደለው ሌሎች ስምንት ሰዎች ታግተው መወሰዳቸውን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
በዞኑ ቡሌን ወረዳ ኤጳር በተባለ ቀበሌ ወስጥም ተመሳሳይ ጥቃቶች እየደረሱ መሆኑን ተገልጿል፡፡ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አትንኩት ሽቱ በወምበራ ወረዳ ውስጥ ከሳምንት በፊት ጥቃት መድረሱን እና የሰው ህይወት ማለፉን አረጋግጠዋል፡፡ በቡሌን ወረዳም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኤጳር ቀበሌ ላይ በአካባው የሚንቀሳቀሱ «ሽፍቶች» ያሏቸው ታጣቂዎች ጉዳት ማድረሳቸውን ገልጸዋል፡፡
በወምበራ ወረዳ ሁለት ቀበሌዎች ወስጥ ደረሰ በተባለ ጥቃት በርካታ ሰዎች ታግተው በታጠቂዎች መወሰዳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ እስካሁን የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉንም ከስፋራው ወደ ሌላ አካባቢ የሸሹ ነዋሪዎች አመልክተዋል፡፡ከነሐሰ 22/2012 ዓ.ም አንስቶ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች መታየታቸውንና ከብት መዝርፋቸውንም አክለዋል፡፡
አንድ አባታቸው በታጣቂዎች መገደላቸውን በስልክ የነገሩን የአካባቢው ነዋሪ በበረሀማ ስፋራዎች የሚኖሩ አርሶ አደርች ሙሉ በሙሉ አካባቢውን ለቀው ወደ ሌላ ስፋራ መሸሻቸውን ገልጸዋል፡፡ ጉዳዩን ለወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት እና ለሌሎችም በየደረጃው ላሉት የመንግስት አካላት ቢያመላክቱም ምላሽ ማግኘት አለመቻላቸውን ገልጸዋው ከሞቱ ሰዎች መካከከል የሶስቱ አስከሬን አስካሁን አለመነሳቱን ጠቁመዋል፡፡ በታጣቂዎች በደረሰባቸው ጥቃት የአጎታቸው ህይወት ማለፉን የነገሩን ሌላው የአካቢው ነዋሪም ኤባች ከተባለ ቀበሌን ጨምሮ ስምንት ሰዎች በታጣቂዎች መታገታቸውንና እስካሁን አለመገኘታቸውን አስረድተዋል፡፡
በወምበራ ወረዳ ሁለት ቀበሌዎች ውስጥ በደረሰው ጥቃት ምክንያም የሰው ህይወት ማለፉንና ከሁለቱም ቀበሌዎች ከ100 በላይ ሰዎች ከቤት ንብረታው በመፍናቀላቸውን የወረዳ ኮሙኒኬሽን በፌስቡክ ገጹ ይፋ አድርገዋል፡፡ በበመተከል ዞን ቡሌን ወረዳ ኤጳር እና ዶቢ በተባሉ ቀበሌዎች በተመሳሳይ ከትናት በስቲያ በታጣቂዎች ጥቃት መፈጸሙን ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ በተለይም ከከተማ ራቅ ባሉ ስፋራዎች የሚደርሱ ጥቃቶች ከፍተኛ መሆናቸውንና ብዙ ቁጥር ያላቸው የአርሶ አደሮች ከብቶች መዘረፋቸውንም አክለዋል፡፡
የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አትንኩት ሽቱ በዚህ ጉዳይ ላይ በስልክ በሰጡን ማብራሪያ በወምበራ ወረዳ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ስድስት ሰዎች መታገታቸውን የሰው ህይወትም መጥፋቱን አስረድተዋል፡፡ በቡሌን ወረዳም በአካቢው የሚንቀሳቀሱ ሽፍቶች የነዋሪውን ንብረት መዝረፋቸውን በመጥቀስ በአካባቢው የጸጥታ ሀይሎች መሰማራተቸውን ጠቁመዋል፡፡ ከጥቃት አድራሾቹ መካከል እስካሁን በቁጥጥር ስር የዋለ የለም ተብሏል፡፡
በቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል በተለይም በመተከል ዞን የተወሰኑ ወረዳዎች ከዚህ ቀደም በልዩ ሁኔታ በሀገር መከላከያ እና ፌደራል ፖሊስ እንዲሁም የክልል ጸጥታ ሀይሎች በጋራ ባቋቋሙት ኮማንድ ፖስት ሲጠበቁ የቆዩ ሲሆን በዚሁ አካባቢው ኮማንድ ፖስት የአካባቢውን የጸጥታ ችግር በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመፍታት ሲባል በአድስ መልክ በሚያዚያ ወር 2012 ዓ.ም ወደ ስራ መግባቱ የሚታወስ ነው፡፡ኮማንድ ፖስቱ ስራ ከጀመረ ወዲህም በተለያዩ ጊዜት በዞኑ ውስጥ በተከሰቱት ግጭቶችና ጥቃቶች ከ30 በላይ ሰዎች ህይወት አልፈዋል፡፡
- ከጁንታው ጎን ተሰልፈው ኢትዮጵያችንን ለሚያተራምሱ የነጭ ጁንታዎች – ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)ከጁንታው ጎን ተሰልፈው ኢትዮጵያችንን ለሚያተራምሱ የነጭ ጁንታዎችን በኢትዮጵያዊነት መንፈስ ልንታገላቸው ይገባናል!! ብራቦ አቶ ኦባንግ-እኛ ለመናገር የማንፈልገውን በግልጽ ቋንቋ ስለተናገርክ!! ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) 18.01.2021 መግቢያ ከአንድ ወርContinue Reading
- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሕወሓትን ሕጋዊ ሰውነት መሰረዙን አስታወቀ – ቅንጅት “በተጭበረበረ ተግባር”እንዲሰረዝ ተወስኗልየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ ላይ ዛሬ ባስተላለፈው ውሳኔ የሕወሃትን ሕጋዊ ሰውነት መሰረዙን አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሕግ ከተቋቋመባቸው ዋና ዋና ተግባራትContinue Reading
- የቀድሞው የሱዳን መከላከያ ሚኒስትር ኮ/ል ኢብራሂም ሸምሰዲን?#FakeNewsAlert ከ1.1 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያሉት እንደወረደ (Endewerede) የተባለ ይህ የፌስቡክ ገጽ የቀድሞው የሱዳን መከላከያ ሚኒስትር ኮ/ል ኢብራሂም ሸምሰዲንን ያሳያሉ ያላቸውን ምስሎች ዛሬ አጋርቷል። ከፎቶዎቹContinue Reading
- በዓድዋ ከተማ የመብራት አገልግሎት ዛሬ ጀመረበትግራይ ክልል የተካሄደውን የህግ ማስከበር ዘመቻ ተከትሎ በጁንታው አባላት ጉዳት ደርሶበት ከጥቅም ውጭ ሆኖ የነበረው የኤሌክትሪክ መስመር ጥገና ተደርጎለት በዛሬው እለት አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገለጸ።Continue Reading