Share and Enjoy !

Shares
የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት በሃገራችን ወቅታዊ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ።
ምክር ቤቱ በሃገራችን የተቃጡ፣ የከሸፉ እና ጉዳት ያደረሱ የብሔራዊ ደህንነት ስጋቶችን በዝርዝር ዳስሷል።
በአሁኑ ወቅት ያሉ ወቅታዊ የደህንነት ጉዳዮች ላይም በዝርዝር የተመለከተ ሲሆን በቀጣይ ስጋቶቹን በተቀናጀ መልኩ መግታት የሚቻልበት አግባብ ላይ ተወያይቷል።
በዚህም የሃገርን ሉዓላዊነት፣ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅና የህግ የበላይነትን ለማስከበር መንግስት ቁርጠኝነት እንደሚሰራ በመግለፅ ይህን እውን ለማድረግም መከላከያን ጨምሮ ሁሉም የደህንነትና ጸጥታ ተቋማት እስካሁን እያደረጉት ያለውን ጥረትና መስዋዕትነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ምክር ቤቱ አረጋግጧል።
Related stories   ስዩምና አባይ ጨምሮ የጁንታው ቀንደኛ አመራሮች ተደመሰሱ፣ ደብረጽዮን እጅ እንዲሰጥ ተከቦ 24 ሰዓት ተሰጥቶታል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *