በኢትዮጵያ የሚገኙ ንግድ ባንኮች ከሚያቀርቡት ብድር 5 በመቶውን በተንቀሳቃሽ ንብረት ለሚሰጥ የብድር አይነት እንዲያውሉት የሚያዝ መመሪያ ማውጣቱን ብሄራዊ ባንክ አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ተንቀሳቃሽ ንብቶሮችን በዋስትና አስይዞ መበደር የሚያስችለው መመሪያ ላይ ከፋይናንስ ተቋማት ተወካዮች ጋር ውይይት አካሂዷል።
ብሄራዊ ባንኩ ከዚህ በተጨማሪም ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች አስይዘው የሚበደሯቸውን ንብረቶች የኢንሹራንስ ተጠቃሚ በሚያደርገው የማይክሮ ኢንሹራን መመሪያ ላይም ከፋይናንስ ተቋማት ተወካዮች ጋር ተወያይቷል።
ከዚህ ቀደም ቋሚ የሆኑ ንብረቶችን ብቻ በማስያዝ ይደረግ የነበረውን የብድር ስርአት ይቀይራል የተባለለት መመሪያው በዋናነት አርሶ አደሩን ፤አርብቶ አደሩን ፤የፈጠራ ባለሙያዎችን እና ሌሎች ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን አስይዘው መበደር የሚችሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ የብሄራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ ገልጸዋል።
የብድር ስርአቱ በሀገሪቱ የሚገኙ በተለይም በግብርናው ዘርፍ ያሉ ሀብቶችን አሟጦ ለመጠቀም እንደሚያግዝ የተናገሩት ብሄራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ ኢንቨስትመንትን በማበረታታት እና የስራ እድልን በመፍጠርም ጉልህ ድርሻ ያበረክታል ነው ያሉት።
ከዚህ ባለፈም መመሪያው አሁን ላይ በሀገሪቱ በሁሉም ዘርፎች ያለውን የተበዳሪዎች ቁጥር ከ260 ሺህ በላይ እንደሚያሳድግ እና ለፋይናንስ ዘርፉ አዲስ መንገድን ከፋች መመሪያ መሆኑን ዶክተር ይናገር ደሴ ተናግረዋል።
ዶክተር ይናገር ደሴ መመሪያ ባንኮች በዓመት ለተለያዩ ዘርፎች ለብድር ከሚያቀርቡት ገንዘብ ውስጥ 5 ከመቶ የሚሆነውን ለተንቀሳቃሽ ንብረት ለሚያቀርቡ ተበዳሪዎች ማዘጋጀት እንዳለባቸው መመሪያው እንደሚያዝ ገልጸዋል።
የብሄራዊ ባንክ በቀጣይ ዓመት መመሪያው ተግባራዊ እንዲደረግ የተለያዩ ዝግጅቶችን እያደረገ መሆኑን የገለጹት ገዥው ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን አስይዘው መበደር የሚፈልጉ ዜጎችን ለመመዝገብ በማእከል ደረጃ የመመዝገቢያ ስርዓት መዘጋጀቱን ተናግረዋል።
ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን አስይዞ መበደርን የሚፈቅደው አዋጅ በተወካዮች ምክር ቤት በዘንድሮ ዓመት መጽደቁ ይታወሳል።
በጥበበስላሴ ጀምበሩ
(ኤፍ.ቢ.ሲ)
- “የትኅትና ገመድ የመጨረሻዋ ቋጠሮ ብርቱ ክንድ ናት፤ ከተሠነዘረች ሳታደቅቅ አትመለስም”“የትኅትና ገመድ የመጨረሻዋ ቋጠሮ ብርቱ ክንድ ናት። ከተሠነዘረች ሳታደቅቅ አትመለስም” ሲሉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ገለጹ። ጠቅላይ ሚንስትርሩ ይህን ያሉት ለጥምቀትና ከተራ በዓል እንኳንContinue Reading
- Ethiopia: What’s Next After Tigray?n early 2018, amidst incessant protests especially in Ethiopia’s Oromo and Amhara regions, Abiy Ahmed Ali became the new prime minister of Ethiopia. His ascentContinue Reading
- “ አንገት ቆረጣ ” የ – ሰለጠነው የ- እርስ በርስ መበላላት!ሃኪሙ የተረኛ ስም ጠራ፤ አስናቀ “ አቤት” ብሎ ከተቀመጠበት ተነሳ፡፡ ሃኪሙ አስናቀን በምልክት “ የት አለ” ሲል ጠየቀው፡፡ አስናቀ መዘናጋቱን አስታወቆ የተጠየቀውን ሊያመጣ ላፍታ ወደContinue Reading
- Death toll from violence in Sudan’s West Darfur risesCAIRO (AP) – The death toll from tribal violence between Arabs and non-Arabs in Sudan’s West Darfur province climbed to at least 83, including womenContinue Reading