ኢትዮጵያ ቢጂአይ ባዮ ቴክኖሎጂ ከተባለው ግዙፍ የቻይና ኩባንያ በመተባበር ባቋቋመችው ፋብሪካ የኮሮና መመርመሪያ ቴስት ኪት ማምረት ጀመረች። ዛሬ መስከረም 3 ቀን 2013 ዓ.ም በጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተመርቆ የተከፈተው እና በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪያል ፖርክ የተገነባው ፋብሪካ በአመት 10 ሚሊዮን የመመርመሪያ ኪቶችን የማምረት አቅም እንዳለው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለብሔራዊው የቴሌቭዥን ጣቢያ ቃለ መጠይቅ በሰጡበት ወቅት በፋብሪካው የተመረተውን መመርመሪያ ቴስት ኪት በእጃቸው ይዘው ታይተዋል። ጠቅላይ ምኒስትሩ ቴስት ኪቱን እያሳዩ “እዚህ ጋ እንደምታዩት በኢትዮጵያ የተመረተ ነው የሚለው” ሲሉ ተደምጠዋል።
“የመጀመሪያው የቴስት ኪት በኢትዮጵያ ተመርቷል። በቢጂአይ እና በኢትዮጵያ መንግሥት ትብብር ነው ይኸ ፋብሪካ የተቋቋመው። አሁን በአመት ከ10 ሚሊዮን በላይ [ቴስት ኪት የማምረት] አቅም አለው። ለእኛም ለተቀረው የአፍሪካ አገርም ምርቱን ለመላክ የሚያስችል አቅም ተፈጥሯል” ብለዋል።
“በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቤተ ሙከራ ተቋቁሞ እዚያው ምርመራ ይደረጋል። በከተማችንም ተጨማሪ ቤተ ሙከራዎች ይቋቋማሉ” ሲሉም አክለዋል። ዐቢይ የጤና ሚኒስቴር እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የቦርድ ሰብሳቢ አርከበ እቁባይ (ዶ/ር) ጨምሮ ፋብሪካው በኢትዮጵያ እንዲቋቋም ከፍ ያለ ሚና ተጫውተዋል ያሏቸውን አመስግነዋል።
ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በመተባበር ማምረቻውን የከፈተው የቻይና ኩባንያ እስካለፈው ግንቦት ወር ድረስ ብቻ 35 ሚሊዮን የኮሮና መመርመሪያዎችን ለ180 አገሮች መሸጡን እና 58 ቤተ ሙከራዎች መገንባቱን የሬውተርስ ዘገባ ይጠቁማል። የኮሮና ወረርሽኝ ዓለምን ከማመሱ በፊት ባለፈው ጥቅምት 2012 ዓ.ም የኢትዮጵያ መንግሥት ከቢጂአይ በተሰጠው መሳሪያ የዘረመል ቤተ ሙከራ ለማቋቋም ማቀዱን አስታውቆ ነበር።
መቀመጫውን በቻይናዋ ሸንዘን ከተማ ያደረገው ቢጂአይ ግሩፕ በዓለም ትልቁ የዘረመል ጥናት ኩባንያ ነው። የኩባንያው ድረ ገጽ እንደሚጠቁመው ለሥነ ሕይወት ተመራማሪዎች የዘረመል ትንተና መሳሪያዎች እና ግብዓቶች ያቀርባል። ከ 1,000 በላይ ሰራተኞች በ39 አገሮች አሉት።
ኩባንያው ከ21 አመታት በፊት ቤጂንግ ጄኖሚክስ ኢንስቲትዩት በሚል ሥያሜ በአራት ሳይንቲስቶች ሲቋቋም ዋንኛ ዓላማው የሰው ልጅን ዘረመል ለማጥናት በሚደረገው ምርምር ቻይናን መቀላቀል ነበር። ላለፉት አራት አመታት 20 ሚሊዮን የእጽዋት እና የእንስሳት ዘረመል የተከማቸበትን የቻይና ብሔራዊ የዘረመል ባንክ የሚያስተዳድረው ይኸው ኩባንያ ነው።
የኢትዮጵያ የጤና ሚኒስቴር በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የተገነባው ፋብሪካ የኮሮና ወረርሽኝ በቁጥጥር ሥር ሲውል የወባ እና የሳንባ ነቀርሳ መመርመሪያዎችን ወደ ማምረት እንደሚሸጋገር አስታውቋል።
ኢትዮጵያ እስከ ትናንት መስከረም 2 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ አንድ ሚሊዮን 130 ሺሕ 850 የኮሮና ምርመራዎች እንዳደረገች የጤና ሚኒስቴር እና የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መግለጫ ይጠቁማል። በአገሪቱ በኮሮና የተያዙ ሰዎች ቁጥር 63 ሺሕ 888 የደረሰ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 38 ሺሕ 397ቱ አሁንም ተሕዋሲው አለባቸው። ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ እስካሁን 996 ሰዎች በኢትዮጵያ ሕይወታቸውን አጥተዋል። ትናንት ይፋ በሆነው መግለጫ መሠረት 345 ሰዎች በጠና ታመዋል።
እሸቴ በቀለ = DW
- በትግራይ 3.5 ሚሊዮን ተረጂዎች የዕለት ቀለብና ተመሳሳይ እርዳታ እየተደረገላቸው ነውበትግራይ ለ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች የዕለት ደራሽ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎች እየተደረገ መሆኑን የብሄራዊ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ በክልሉ በነበረው ህግ ማስከበርContinue Reading
- የኮቪድ ጽኑ ታማሚዎች ቁጥር መብዛቱ በዲላ ሆስፒታል አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ጫና አስከትሏልበኮሮና ቫይረስ ተይዘው ጽኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር መጨመር በስራው ላይ ጫና ማሳደሩን የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል አስተወቀ የቫይረሱ ስርጭት በጌዴኦ ዞንና አጎራባች አከባቢዎችContinue Reading
- ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሳይቲስት – ችግር የመፍታት አቅም እንዳለህ ከተሰማህ ፣ያንን ፍጥነት መቀነስ በእውነቱ መልካም አይደለምፕሮፌሰር ሶስና ሀይሌ ይባላሉ።የቁስ ሳይንስና የምህንድስና ሊቅ ሲሆኑ፤የመጀመሪያውን የጠጣር አሲድ ነዳጅ ለዓለም ያስተዋወቁ ሳይንቲስት ናቸው።ከዚህ በተጨማሪ በዘርፉ ከ200 በላይ የምርምር ፅሁፎችን አሳትመው በ14ቱ የባለቤትነት መብትContinue Reading
- ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በትግራይ ያጠናውን ይፋ አደረገ፤ አስገድዶ መድፈር ተፈጽሟል፣ ክልሉ ልዩ ትኩረት ያሻዋልትግራይ ክልል፡ የመሰረታዊ ልማት፣ የማኅበራዊ እና የአስተዳደራዊ አገልግሎቶችን በአፋጣኝ የመመለሱ ተግባር ልዩ ትኩረት ይሻል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) ከሦስት ወራት ላለፈ ጊዜ የዘለቀው እናContinue Reading
- በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲው በደረሰው የእሳት ቃጠሎ የሰው ህይወት አለፈ፤ መማር ማስተማር አይስተጓጉልምበድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉንና ንብረት ላይ ጉዳት መደረሱን ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ኡባህ አደም ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት ፤ ትናንትContinue Reading