መንግስት የብር ኖቶች መቀየራቸውና የባለ 200 ብር አዲስ ኖት ስራ ላይ እንደሚውል ይፋ መድረጉን ተከትሎ መንጫጫት ተጀመሯል። አብዛኞች ውሳኔው ከመዘግየቱ በቀር የአዲስ ብር ለውጥ መደረጉን በመልካም አይተውታል። ዳንኤል ብርሃኔ ” የብር ለውጥ መረጃ ቀደም ብሎ ስላፈተለከ ብዙ ብር ያላቸው የተለያየ አማራጭ ተጠቅመዋል። ብራቸውን ወደ ዶላር፣ ወደ ወርቅ እና ወደ ቋሚ ንብረት አዙረዋል” ሲል ለተቃውሞ ግንባር ቀደም ሆኗል።
የኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበር ከፍተኛ አመራሮች በመግለጫቸው መንግሥት ከባንክ ውጪ እየተንቀሳቀሰ ያለውን ከ113 ቢሊዮን ብር በላይ ወደ ሕጋዊ ሥርዓት ማስገባት እንዳለበት ገልጸው፤ ለዚህም ሲባል የገንዘብ ኖት እንዲቀየር የማሳሰቢያ ምክር ለግሰው ነበር።
ኢትዮጵያ ነባሮቹን የ10፣ የ50 እና የ100 ብር ኖቶች ዓይነቶችን ሙሉ ለሙሉ በመተካት ለግብይት የሚሆን አዲስ የብር ኖት መጠቀም እንደምትጀምር ይፋ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ይፋ አድረገዋል። የፋና ዘገባ ያንብቡ።
ነባሮቹ ኖቶች ከሚተኩት በተጨማሪ በዛሬው ዕለት የ200 ብር ኖት ይፋ እንደሆነ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃ የገለፁት። የ5 ብር ኖት ባለበት ቀጥሎ፤ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ወደ ሣንቲም የሚለወጥ ይሆናል ተብሏል።
እነዚህ አዲስ የገንዘብ ዓይነቶች ለሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎች የሚደረግን ድጋፍ፣ ሙስናን እና የኮንትሮባንድ ሥራዎችን ለመቀልበስ እንደሚረዱ ተጠቁሟል።
እንዲሁም የፋይናንስ ተቋማት የገንዘብ እጥረትን ለመቋቋም እንዲችሉም ያግዛል ነው የተባለው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲሶቹ የገንዘብ ዓይነቶች ላይ የተካተቱ መለያዎች አመሳስሎ ገንዘብ ለማተም የሚደረጉ ሕገ ወጥ ጥረቶችንም ለማስቀረት እንደሚያግዙ ገልፀዋል። አዲስ የታተሙት የብር ኖቶቹ በአካላቸው ላይ የሚገኙ የደህንነት መጠበቂያ ምልክቶች ያሉባቸው ናቸው።
እነዚህን ያላሟሉ ወይም ተመሳስለው የተዘጋጁ ገንዘቦች የያዙ ወይም የሚጠቀሙ ግለሰቦች ካጋጠሙ ለፀጥታ አካላት መጠቆም እንደሚገባ ተነግሯል።
በአሁኑ ወቅት የአዲሶቹ የብር ኖቶች አብዛኛው የህትመት ሥራ ተገባዶ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ግምጃ ቤት እንደሚገኝ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። የስርጭት ስርዓት እና ዕቅድ የተዘጋጀ ሲሆን፣ በሚመለከታቸው አካላት አማካኝነት እንደሚተገበር ተጠቁሟል።
በገንዘብ ቅያሬው ሂደት የጸጥታ ማስከበር አካላት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖራቸው የተገለፀ ሲሆን፥ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ከማህበረሰቡ ጋር በመተባበር ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ እንደሚያስፈፅሙ ተነግሯል። ለዚህም ከብሔራዊ መከላከያ ሠራዊት፣ ከብሔራዊ የመረጃ እና ደህንነት አገልግሎት እና ከፌደራል ፖሊስ የተውጣጣ ኮማንድ ፖስት ተቋቁሞ፤ ሂደቱን በበላይነት ያስተባብራል።
እንዲሁም የክልል መንግሥታት ተመሳሳይ ኮማንድ ፖስት አቋቁመው ሥራውን እንዲያከናውኑ ይጠበቃል። የገንዘብ ቁጥሮቹ በሚያጎላ መሳሪያ ሲታዩ ከጥቁር ወደ አረንጓዴ ፍሎረሰንት ቀለም እንደሚለወጡ ብሄራዊ ባንክ አስታውቋል።
ለአይነ ስውራንም የእውቅና ምልክት ያለው ሲሆን የብሩን ዋጋ በእጅ ዳሰሳ ማወቅ የሚችሉበት የደህንነት መጠበቂያ ያለው ነው። በተመሳሳይ ገንዘቡ ወደ ላይ ወይንም ወደታች ሲዞር የሚንቀሳቀስ ደማቅ የቀለም ፍንጣቂ የደህንነት መጠበቂያ ምልክት እንዳለውም ነው ተነግሯል።
የብር ኖቱ ሲዳሰስ የመጎርበጥ ስሜት እንዲሁም የኖቱ ዋጋ ይታያል። የሚሽከረከር ደማቅ ቀለም ኮኮብ አዲስ የደህንነት መጠበቂያ ክር፤ በክሩ ውስጥም NBET፣ ኢብባ እና ገንዘቡ አይኖቶች ተፅፈው ይገኙበታል ነው የተባለው።
ገንዘቡ ወደ ብርሃን አቅጣጫ ተደርጎ ሲታይ በላይ ላይ ከሚገኘው ምስል ፊት ለፊት ተመሳሳይ ደብዛዛ ውሃ መልክ ያለው ምልክት እንደሚታይ ተጠቁሟል።
የብር ኖቶቹ በብርሃን አቅጣጫ ሲታዮ ኳስ መሳይ ምልክት ከኖቶቹ በስተኋላ ካለው ተመሳሳይ ምልክት ጋር በፍፁም ትይዩ ሆነው በአንድ ቦታ ላይ ያርፋሉ። እንዲሁም አንበሳው ምስል ራስ ላይ አልትራቯዮሌት ጨረር ሲበራበት ወደ ቢጫነት የሚለወጥ ፍሎረሰንት ምልክት አለው ተብሏል።
- First Russian warship enters Port Sudan ahead of plans to open naval base: InterfaxThe Russian warship, “Admiral Grigorovich” frigate, entered the Sudanese port where Moscow plans to build a naval base on the country’s Red Sea coast, Russia’s Interfax newsContinue Reading
- US Attempt To Make Pronouncements On Ethiopia’s Internal Affairs Regrettable :MoFAThe Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia (MoFA) has rejected the press statement issued by the US Secretary of State Mr. Antony J. Blinken yesterdayContinue Reading
- “አማራ ከትግራይ ክልል ውጣ”አሜሪካ ”ግፍ” ታውቃለች? ጋምቤላ፣ ማይካድራ፣ ራያ፣ በደኖ፣ሆራ፣ ዋተር…ምን ተደርጓል?አሜሪካ እጅግ አስገራሚ መግለጫ አሰራጭታለች። አማራ ከትግራይ ክልል ይውጣ ብላለች። በትግራይ ግፍ መፈጸሙን አምናለች። ግን ለሜሪካ ” ግፍ” ምንድን ነው? አሜሪካኖች ስለ ግፍ የማውራት ሞራልContinue Reading
- WAR, JUSTIFIABLE WAR? “ጦርነት ለሃገር ህልውና” by Dr. Haymanot“አንድ መንግስት ዜጎቹን የመጠበቅ ግዴታ አለበት። በመሆኑም ራስን የመከላከል ጦርነቶች ሁሉ በሥነ ምግባር የተፈቀዱ ናቸው ” የቅዱስ አውጉስቲን አባባል አስቅቀድመው የሜሪካን መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርContinue Reading