በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ በቁጥጥር ስር ዋለ። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አብዱልአዚም መሀመድ እንደገለጹት በክልሉ በሚገኙ 4 የተለያዩ ኬላዎች በተደረገ ፍተሻ 2 ሚሊዮን 370 ሺህ ብር በቁጥጥር ስር የዋለው።
በክልሉ ኩርሙክ ወረዳ ሱዳን ድንበር አካባቢ በግለሰብ ሲዘዋወር የነበረ 600 ሺህ ብር የሚሆን ገንዘብ በቁጥጥር ስር እንደዋለ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡ በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ ማንኩሽ ኬላም 300 ሺህ ብር ፣በአሶሳ ከተማ አሶሳ ኬላ ደግሞ 700 ሺህ ብር በቁጥጥር ስር ውሏል ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ በአሶሳ ዞን ቡልድግሉ ወረዳ ጎንቆሮ ኬላ ደግሞ 770 ሺህ ብር በቁጥጥር ስር መዋሉንም ኮሚሽነሩ አመልክተዋል፡፡
የክልሉ መንግስት መሠል ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመቆጣጠር ክትትሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለጹት ኮሚሽነር አብዱልአዚም ኅብረተሰቡ አስፈላጊውን ትብብር ማድረጉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረባቸውን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
Related stories   “ድንበር ሲፈርስ፤ መሐሉ ዳር ይሆናል” ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *