የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል እንዲሁም የብድር ውሎችን ሰነድ አረጋግጦ የመመዝገብ አገልግሎት ላይ የአሰራር ለውጥ ማድረጉን አስታወቀ።
ኤጀንሲው ዛሬ ለሸገር እንዳለው ከላይ የተገለጹትን አገልግሎቶች ለማግኘት
– የሽያጭ ዋጋ ወይም የብድሩ ገንዘብ አከፋፈልን በተመለከተ ክፍያው መፈጸም ያለበት፣ በሽያጭ ውል ጊዜ የሽያጭ ዋጋው ባንክ ከሚገኝ የገዢ ሂሳብ ተቀናሽ ሆኖ ወደ ሻጭ የባንክ ሂሳብ የተላለፈ (Transfer) ሲሆን ብቻ ነው።
– በብድር ውል ጊዜ የብድሩ ገንዘብ ባንክ ከሚገኝ የአበዳሪ ሂሳብ ተቀናሽ ሆኖ ወደ ተበዳሪ የባንክ ሂሳብ የተላለፈ (Transfer) መሆን አለበት ሲል የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ለሸገር ገልጿል።
በተጨማሪም ህገወጥነትን ለመከላከል ሲባል የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረትን በስጦታ የማስተላለፍ ውልን አረጋግጦ የመመዝገብ አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ የማይሰጥ መሆኑን ኤጀንሲው እወቁልኝ ብሏል። የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ አሰራሩን የለወጠው ከባንክ ውጪ የሚንቀሳቀስ ጥሬ ገንዘብን ሥርዓት ለማስያዝ ፣ህገወጥነትን ለመከላከል እና ዘመናዊ አሰራርን ለማስፈን ነው ብሏል።
ይህ አሰራር ከነገ መስከረም 7,2013 ይጀመራል!
- ትህነግ – ሚስጥሩ “ሚስጥር” የሆነበት ተዋጊ!! የፕላኔቱ ሆቴል ሚስጢር ዜሮ ብዜት!!ኢትዮ 12 ዜና – “ ሚስጢር ነበር” ይላል የኢትዮ 12 መረጃ አቀባይ። ሚስጥሩ በሚስጢር የተቆለፈ መሆኑንን የማያውቁ ሚስጢረኞች ሲል ተንደርድሮ ፓርላማ ይገባል። ፓርላማ ገብቶ ከትንታኔውContinue Reading
- Ethiopia Briefs EU Delegation On Latest Development In TigrayMinister of Finance Ahmed Shide received Erik Habers, Charge De Affair and Head of Cooperation of EU Delegation in Addis Ababa at his office today.Continue Reading
- እጃቸውን የሰጡ ከፍተኛ መኮንኖች ተገደው ሚኒሻ ሲያደራጁ እንደነበር ለችሎት አስረዱበቅርቡ ለአገር መከላከያ ሠራዊት እጃቸውን የሰጡት ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ኒሻን ጨምሮ አራት የቀድሞ የጦር መኮንኖች በህወሓት ጸረ ሰላም ቡድን አመራሮች ተገደው ሚኒሻዎችን ሲያደራጁ እንደነበር ለፍርድContinue Reading
- ምርጫ ቦርድ ኢዜማን ጨምሮ ስድስት ፓርቲዎችን የምርጫ ምልክት ቀይሩ አለ፤ ኢዜማ በመላው አገሪቱ ብቻውን እንደሚወዳደር አስታወቀስድስት የፖለቲካ ፓርቲዎች የመረጧቸውን ምልክቶች በተለያዩ ምክንያቶች ቀይረው እንዲያቀርቡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥሪ አደረገ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የፓርቲዎች የምርጫContinue Reading