በ2013 በጀት አመት የመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት 42 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የሚኒስቴሩ የስራ ኃላፊዎች የ2013 በጀት አመት የገቢ አሰባሰብ እቅድ እና በበጀት ዓመቱ የሁለት ወራት አፈፃፀም ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል፡፡
በዉይይቱ ወቅት እንደተገለፀው በሀምሌና በነሀሴ ወር 39 ቢሊየን 430 ሚሊየን 954ሺህ 692 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 42 ቢሊየን 204 ሚሊየን 26 ሺህ ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 107 በመቶ በላይ ማሳካት ተችሏል፡፡ ይህም ከባለፈው ተመሳሳይ ሁለት ወር ጋር ሲነጻጸር የ10 ነጥብ 7 በመቶ ብልጫ አለው፡፡
በ2013 በጀት አመት ከሀገር ውስጥ ታክስ ብቻ 164 ነጥብ 29 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ የታቀደ ሲሆን ይህም በ2012 ከሀገር ውስጥ ታክስ ከተሰበሰበው 128 ነጥብ 67 ቢሊየን አንጻር የ35 ነጥብ 62 ቢሊየን ብር ብልጫ እንዳለው ነው የተገለጸው፡፡
እቅዱን ለማሳካት የሚያስችል የተረጋጋ እና ጥሩ አቅም ያለው ሰራተኛ መኖሩና በሰራተኛውና በአመራሩ መካከል ያለው ተቀራርቦ መስራት ከምንጊዜውም በላይ እያደገ በመሆኑና ግብር ከፋዮች ግብራቸውን በፈቃደኝነት የመክፈል ባህል እዳበረ በመምጣቱ ለዕቅዱ መሳካት አስተዋፅኦ አበርክቷል ነው የተባለው፡፡
በውይይቱ ላይ የተገኙት የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው ያቀድነውን ብቻ ሳይሆን ከዚያም በላይ ለመሰብሰብ መስራት አለብን ማለታቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
#FBC
- የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና – ለኢትዮጵያ የሚፈጥራቸው እድሎችና ተግዳሮቶችአስተያየት – በጥላሁን እምሩ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር 2018 ሩዋንዳ ኪጋሊ ላይ ተፈርሞ 2021 መባቻ ላይ ወደ ተግባር የገባው የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) ታቃፊ ባደረጋቸውContinue Reading
- ኢትዮጵያና ቱርክ በመካከላቸው ያለውን የንግድ ልውውጥ 1 ቢሊየን ዶላር ለማድረስ ተስማሙኢትዮጵያና ቱርክ በመካከላቸው ያለውን የንግድ ልውውጥ 1 ቢሊየን ዶላር ለማድረስ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታወቁ። የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በተገኙበት የኢትዮ ቱርክ ስምንተኛው የኢኮኖሚ፣Continue Reading
- በአማራ ክልል ስድስት ዞኖች ሳይካተቱ በአምስት ወራት ውስጥ 8 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ገቢ ተሰበሰበበአማራ ክልል በአምስት ወራት ውስጥ 8 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰብ እንደቻለ የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ብዙአየሁ ቢያዝን ገለፁ፡፡ የአማራ ክልል ገቢዎችContinue Reading
- የትግራይ ጦርነት ኤኮኖሚያዊ ምክንያቶችበኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት እና በህወሓት መካከል የተቀሰቀሰው “ጦርነት የኢትዮጵያን ኤኮኖሚ፤ የተፈጥሮ ሐብቷን እና በየአመቱ ከአበዳሪዎች እና ለጋሾች የምታገኘውን በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ለመቆጣጠር የሚደረግ ነው” በማለትContinue Reading