በ20/80 ፕሮግራም የዕጣው አሸናፊ ሆነው ውል ላልፈጸሙ 32 ሺህ 653 ባለ እድለኞች ውል ማዋዋሉ የተጀመረ ሲሆን በቅርቡ ቁልፍ የሚረከቡ መሆኑን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ ፋና ዘገባ። በ40/60 ፕሮግራም ከዚህ ቀደም ውል ለፈጸሙ 18 ሺህ 576 እድለኞች ቁልፍ የማስረከብ ስራ መጀመሩንም የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡
በአዲስ አበባ በየካቲት 27-2011 ዓ.ም በተደረገው ዕጣ ማውጣት ስነ-ስርአት ዕጣ ወጥቶላቸው ውል ላልገቡ እና ቁልፍ ላልተረከቡ ባለ ዕጣዎች ውል ማስገባትና ቁልፍ ማስረከቡ በአፋጣኝ እንዲፈፀም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገለፀ።
የከተማ አስተዳደሩ በየወቅቱ የሚነሱ የነዋሪዎቹን ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመመለስ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ በመግለፅ ከእነዚህም ውስጥ የጋራ መኖርያ ቤቶች ጉዳይ አንዱና የህዝብ ቅሬታና አቤቱታ የበዛበት ሆኖ መቆየቱን አመልክቷል።
በተደረገው ማጣራት እና የስራ ሪፖርት መሰረት ዕጣ ወጥቶላቸው ለባለ ዕጣዎች እጅ ያልደረሱ ቤቶች መኖራቸው ታውቋል ብሏል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ40/60 እና 20/80 ፕሮግራሞች የተገነቡ ቤቶችን የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም ዕጣ ማውጣቱ የተገለፀ ሲሆን ሆኖም ቤቶቹ በቂ የመሠረተ ልማት በሌለባቸው የማስፋፊያ አካባቢዎች በመገንባታቸው እና በሚፈለገው ልክ አጠቃላይ የሳይት ስራው በወቅቱ ባለመጠናቀቁ ለባለ እድለኞች ሳይተላለፉ መቆየታቸውን የከተማው አስተዳደር በመረዳቱ እጣ ወቶላቸው ውል ላልገቡ እና ቁልፍ ላልተረከቡ ባለ ዕጣዎች ውል ማስገባትና ቁልፍ ማስረከቡ በአፋጣኝ እንዲፈፀም አስታውቋል።
በመሆኑም በ20/80 ፕሮግራም የዕጣው አሸናፊ ሆነው ውል ላልፈጸሙ 32 ሺህ 653 ባለ እድለኞች ውል ማዋዋሉ የተጀመረ ሲሆን በቅርቡ ቁልፍ የሚረከቡ መሆኑን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በ40/60 ፕሮግራም ከዚህ ቀደም ውል ለፈጸሙ 18 ሺህ 576 እድለኞች ቁልፍ የማስረከብ ስራ መጀመሩንም የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡
- “የትኅትና ገመድ የመጨረሻዋ ቋጠሮ ብርቱ ክንድ ናት፤ ከተሠነዘረች ሳታደቅቅ አትመለስም”“የትኅትና ገመድ የመጨረሻዋ ቋጠሮ ብርቱ ክንድ ናት። ከተሠነዘረች ሳታደቅቅ አትመለስም” ሲሉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ገለጹ። ጠቅላይ ሚንስትርሩ ይህን ያሉት ለጥምቀትና ከተራ በዓል እንኳንContinue Reading
- Ethiopia: What’s Next After Tigray?n early 2018, amidst incessant protests especially in Ethiopia’s Oromo and Amhara regions, Abiy Ahmed Ali became the new prime minister of Ethiopia. His ascentContinue Reading
- “ አንገት ቆረጣ ” የ – ሰለጠነው የ- እርስ በርስ መበላላት!ሃኪሙ የተረኛ ስም ጠራ፤ አስናቀ “ አቤት” ብሎ ከተቀመጠበት ተነሳ፡፡ ሃኪሙ አስናቀን በምልክት “ የት አለ” ሲል ጠየቀው፡፡ አስናቀ መዘናጋቱን አስታወቆ የተጠየቀውን ሊያመጣ ላፍታ ወደContinue Reading
- Death toll from violence in Sudan’s West Darfur risesCAIRO (AP) – The death toll from tribal violence between Arabs and non-Arabs in Sudan’s West Darfur province climbed to at least 83, including womenContinue Reading