የወደፊት እቅድን ተግባራዊ ለማድረግ በታቀደ ሴራ የመተከል ዞን ወደ ቤኒሻንጉል መካተቱ ለጥፋቱ ሁሉ መነሻ ምክንያት እንደሆነ ይነገራል። ለትግራይ ክልል ኮሪዶር እንድትሆን ወሽመጥ የተሰራላት ቤኒሻንጉል በኢንቨስትመንት ስም ከጋምቤላ ቀጥሎ በርካታ የትህነግ ሰዎች እንደገቡባት መረጃዎች ያሳያሉ።
መተከል ገና ከደርግ ውድቀት ጀምሮ የተሸፈነና የተዳፈነ ወንጀል በአንድ የህብረተሰብ ክፍል ላይ የተፈጸመበት ቦታ ለመሆኑ በቂ ምስክሮች አሉ። የወንጀሉን ያህል ባይሆንም ለመጻፍ የሞከሩ አሉ። ሁሉም ወገኖች እንደሚሉት በቤኒሻንጉል አሁን ድረስ የዘለቀ ግድያ የሚፈጸመው ወደፊትን አልሞ በሚተገብረው ሴራ ሳቢያ ነው።
በቅርቡ ለነጋሪ በማይመች መልኩ የተካሄደው ግድያ ” በፖሊሶች ጥለው ሮጡ” ተልካሻ ምክንያት የሚታለፍ ሳይሆን ችግሩን ከምንጩ ማድረቅ ላይ መተኮር እንዳለበት ህዝብ በቁጣ አሳስቧል። መንግስትም የክልሉን አመራሮች አንገት አንቆ እንደገመገመም ታውቋል።
ጥቃት እንደሚደርስ መረጃ እያለ በሕዝብ ደምና በቸቅላዎች ሕይወት የተጫወቱትን ቅጥረኞች ለአንዴና ለመቸረሻ ጊዜ ለማጥፋት ዘመቻ ሲጀመር በጥቅሉ አራት መቶ የሚደርሱ የክልሉ የመዋቅር ሃይሎች፣ የጸጥታ ሰራተኞችና ፖሊሦች እንዲሁም ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉና ማጥራቱ እንደሚቀጥል ይፋ ሆኗል።
ከአማራና ከኦሮሚያ ክልል ጋር በጣምራ ዝመቻው እንዲከናወን በይፋ ክልሉ ባቀረበው ጥሪ መሰረት የመተከል ዞን በልዩ ሁኔታ እንድትተዳደር ተወስኗል። ኢዜአ የሚከተለውን ዘግቧል።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ከአመት በፊት የአካባቢውን ሠላም ለማጠናከር የተዋቀረው ኮማንድ ፖስት ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት እንዲቀጥል መወሰኑ ተገለጸ።የክልሉ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ መለሰ በየነ እንዳስወቁት በክልሉ ከአንድ ዓመት በፊት የተዋቀረው ኮማንድ ፖስት ለቀጣይ ሶስት ወራት የአካባቢውን ሠላም የማስመለስ ስራውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ተወስኗል።
“ኮማንድ ፖስቱ በክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር እንደሚመራ ገልጸው፤ ከአጎራባች አማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች፣ ከሃገር መከላከያ ሠራዊት፣ በፌደራል ፖሊስ እና በየደረጃው ከሚገኙ የጸጥታ ሃይሎች ጋር በቅንጅት ይሠራል” ብለዋል።በዚሁ መሰረት በመተከል ዞን የሚገኙ ግጭት በተደጋጋሚ የተከሰተባቸው ጉባ፣ ቡለን፣ ዳንጉር እና ወምበራ ወረዳዎች የሚከናወኑ የኮማንድ ፖስቱ አጠቃላይ እንቅስቃሴዎች በሃገር መከላከያ ሠራዊት በበላይነት እንደሚከናወኑ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
“ሌሎች በዞኑ የሚገኙ ፓዌ፣ ድባጤ እና ማንዱራ ወረዳዎች ያለው እንቅስቃሴ ደግሞ በኮማንድ ፖስቱ ስር ሆነው አፈጻጸሙ በወረዳ አመራሮች ክትትል ይደረግበታል” ብለዋል።“ከዚህ ቀደም በዞኑ የተጣሉ የጦር መሳሪዎችን እና ማናቸውንም ስለታማ ነገሮችን ይዞ መንቀሳቀስ እንደተከለከለ ይቀጥላል” ብለዋል።
በየኬላዎችም ጠንካራ ፍተሻዎች እንደሚከናወኑ ጠቅሰው፤ እንደ አስፈላጊነቱ የሰዓት እላፊዎችም በክልከላው ሊኖሩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።በተለይም በግጭት የተፈናቀሉትን ሙሉ በሙሉ ወደ ቀያቸው በመመለስ በዘላቂነት ማደራጀት በኮማንድ ፖስቱ እንደሚከናወን አስታውቀዋል።በቁጥጥር ስር ያልዋሉ የጥፋት ሃይሎች ከገቡበት ገብቶ አድኖ መያዝ ሌላው የኮማንድ ፖስቱ ተግባር እንደሆነ ገልጸው፤ ስራውን ውጤታማ ለማድረግ ኮማንድ ፖስቱ ህብረተሰቡ ዋነኛ አጋር አድርጎ እንደሚሠራ ተናግረዋል።
ይህን ለማሳካት ከዚህ ቀደም በየአካባቢው የተጀመሩ ህዝባዊ የውይይት መድረኮች በከፍተኛ አመራሩ በግንባር ቀደም ሃላፊነት እንደሚቀጥሉ አቶ መለሰ አብራርተዋል።ባለድርሻ አካላት በኮማንድ ፖስቱ የተቀመጡ ክልከላዎችን ከማክበር ባሻገር አስፈላጊውን መረጃ ከመስጠት ጀምሮ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ አቶ መለሰ ጥሪ አቅርበዋል።
- ትህነግ – ሚስጥሩ “ሚስጥር” የሆነበት ተዋጊ!! የፕላኔቱ ሆቴል ሚስጢር ዜሮ ብዜት!!ኢትዮ 12 ዜና – “ ሚስጢር ነበር” ይላል የኢትዮ 12 መረጃ አቀባይ። ሚስጥሩ በሚስጢር የተቆለፈ መሆኑንን የማያውቁ ሚስጢረኞች ሲል ተንደርድሮ ፓርላማ ይገባል። ፓርላማ ገብቶ ከትንታኔውContinue Reading
- Ethiopia Briefs EU Delegation On Latest Development In TigrayMinister of Finance Ahmed Shide received Erik Habers, Charge De Affair and Head of Cooperation of EU Delegation in Addis Ababa at his office today.Continue Reading
- እጃቸውን የሰጡ ከፍተኛ መኮንኖች ተገደው ሚኒሻ ሲያደራጁ እንደነበር ለችሎት አስረዱበቅርቡ ለአገር መከላከያ ሠራዊት እጃቸውን የሰጡት ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ኒሻን ጨምሮ አራት የቀድሞ የጦር መኮንኖች በህወሓት ጸረ ሰላም ቡድን አመራሮች ተገደው ሚኒሻዎችን ሲያደራጁ እንደነበር ለፍርድContinue Reading
- ምርጫ ቦርድ ኢዜማን ጨምሮ ስድስት ፓርቲዎችን የምርጫ ምልክት ቀይሩ አለ፤ ኢዜማ በመላው አገሪቱ ብቻውን እንደሚወዳደር አስታወቀስድስት የፖለቲካ ፓርቲዎች የመረጧቸውን ምልክቶች በተለያዩ ምክንያቶች ቀይረው እንዲያቀርቡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥሪ አደረገ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የፓርቲዎች የምርጫContinue Reading