የፌዴራል ፖሊስ ጥብቅ ፍተሻ እያደረገ ያለው ከአማራ ክልል በሚመጡ መንገደኞች ብቻ ሳይሆን ወደ መዲናዋ በሚያስገቡ በሁሉም በሮች ላይ ተመሳሳይ የቁጥጥር ስራ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል እንደሻው ጣሰው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በአልን ምክኒያት በማድረግ በአዲስ አበባ የሽብር ድርጊት ለመፈጸም እና ይህንኑ ተከትሎ ሁከት እና ግጭት እንዲፈጠር በዝግጅት ላይ የሚገኙ አካላት እንዳሉ ደርሰንበታል ያሉት ኮሚሽነር ጄኔራሉ መረጃውን መሰረት በማድረግ ወደ አዲስ አበባ በሚያስገቡ በሁሉም በሮች ላይ ጥብቅ ፍተሻ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል ።
የበዓሉን እንቅስቃሴ ለማደፍረስ ዕቅድ ያላቸው ሀይሎች እንዳሉ ፖሊስ በምርመራ እንደደረሰበት ጠቁመው፤ እነዚህ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቀቆጠቡ አሳስበዋል።
ከመስከረም 25 በኋላ መንግስት አይኖርም በሚል የተለያዩ እንስቃሴዎች የሚያደርጉ አካላት እንዳሉ ገልጸው የህዝቡን ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል።
በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ወደ አዲስ አበባ መግቢያ በሮች በሱልልታ፣ ለገጣፎ፣ ቡራዩ፣ ገላንና ሰበታ ፍተሻ እየተደረገ እንደሆነም ኮሚሽነር እንዳሻው ጣሰው ተናግረዋል።
አላስፈላጊ እንቅስቃሴዎችን ለመግታት ፖሊስ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን ገልጸው፤ በበዓሉ ለመታደም የሚመጡ ምዕምናንና እንግዶችም ትክክልኛውን የይለፍ ባጅ ማድርጋቸውን ማረጋገጥ እንዳለባቸው ተናግረዋል። ይህን ተላልፎ በሚገኝ ማንኛውንም አካል አይታገስም ፤ ፖሊስ እርምጃ ይወስዳልም ብለዋል።
ፖሊስ ከኅብረተሰብ ጋር በትብብር እየሰራ ነው ያሉት ሀላፊው፤ ህብረተሰቡ ለየት ያለ እንቅስቃሴ ሲመለከት የተለመደ ትብብርንና ጥቆማውን ለፖሊስ እንዲሰጥ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
- በሰሜን የኤርትራና ሶማሊያ ወታደሮች ጣልቃ ገብተዋል መባሉን መንግስት ” ፈጠራ የሮኬት ተኳሹ ወሬ” አለው” ጉዳዩን ቀጠናዊ ማድረግና የሌሎችን ጣልቃ ገብነት ለመጋበዘ የሚደረግ ነው። ይህንንም የሚያደረገው ወደ አስመራ ሮኬት ሲጥል የነበረው ሃይል ነው” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይContinue Reading
- ኢትዮጵያ በወታደራዊ ኃይል ጥንካሬ ከአፍሪካ 6ኛ ከዓለም 60ኛ ሆነችግሎባል ፋየር ፓወር በዓለም ዙሪያ ካሉ አገራት መካከል ባደረገው የወታደራዊ ጥንካሬ ምዘና፣ ከ50 በላይ መመዘኛዎችን የተጠቀመ ሲሆን በዚህም አገራት ያላቸውን የወታደራዊ ኃይል ጥንካሬ በዝርዝር ይፋContinue Reading
- “የትኅትና ገመድ የመጨረሻዋ ቋጠሮ ብርቱ ክንድ ናት፤ ከተሠነዘረች ሳታደቅቅ አትመለስም”“የትኅትና ገመድ የመጨረሻዋ ቋጠሮ ብርቱ ክንድ ናት። ከተሠነዘረች ሳታደቅቅ አትመለስም” ሲሉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ገለጹ። ጠቅላይ ሚንስትርሩ ይህን ያሉት ለጥምቀትና ከተራ በዓል እንኳንContinue Reading
- Ethiopia: What’s Next After Tigray?n early 2018, amidst incessant protests especially in Ethiopia’s Oromo and Amhara regions, Abiy Ahmed Ali became the new prime minister of Ethiopia. His ascentContinue Reading