ህወሃት ከፌዴራሊስት ሀይሎች ጋር እየሰራሁ ነው በማለት ህብረተሰቡን እያወናበደ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ፌዴራሊስ ሀይሎች ጥምረት አስታወቀ።
በፌዴራሊስ ሀይሎች ጥላ ስር የተሰባሰብን አካላት የህወሃት አካሄድ ስላልተመቸን እንዲታገድ በማድረግ ውይይታችንን በአዲስ አበባ እያካሄድን እንገኛለን ብሏል ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ።
ህወሃት የፌዴራሊስት ሀይሎችን በመጠቀም የስልጣን ጥማቱን ለማሳከት ሲንቀሳቀስ ተመልክተነዋል ያለው ጥምረቱ አሁንም ከፌዴራል ሀይሎች ጋር እየሰራሁ ነው በማለት የትግራይን ህዝብ ለማሳሳት ሲሞክር እየተመለከትን ነው ብሏል።
የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ሀይሎች ጥምረት በመግለጫው ሀገር በታኝ የሆነ አጀንዳ ካላቸው ቡድኖች ጋር አንዳችም ዓይነት ህብረት እንደሌለን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቅ እንፈልጋለን ነው ያለው።
የፌዴራሊስት ሀይል ሆኖ ለመቀጠል በሀሳብም ይሆን በኢኮኖሚ አሃዳዊ ቁመና ይዞ መቀጠል ተገቢ አይደለም ብሏል ጥምረቱ።
የህወሃት እውነተኛ ማንነት ደግሞ ሀገርን በፌዴራል እሳቤ አስተዳድራለሁ በሚል የይስሙላ የክልል አስተዳደር ዘርግቶ የእርሱን ሀሳብ ብቻ ሲያስፈፅም የነበረ ፤ ሀገር ያመነጭቸውን ሀብት በኢ ፍትሃዊነት ሲያባክን የነበረ መሆኑን አንስቷል።
መሻሻል የማያሳይ እና ወቅታዊውን የሀገሪቱን ፓለቲካ የማይዋጅ ሆኖ በመገኘቱ ህዋሃትና ኢዲህንን በይፋ ከጥምረቱ መሰናበታቸውን ህዝቡ ተረድቶ በስማችን እየነገደ ያለውን የህወሃት ቡድን ህዝብ ከጥምረቱ ጋር በጋራ በመሆን እንዲታገል ጥሪ አቅርቧል።
ህወሃት እያራመደ የሚገኘው አቋም ኢትዮጵያ በፌዴራላዊ አስተዳደር እንዲሁም ፍትሃዊነት እና እኩልነት ባረጋገጠ እና ባጣጣመ መልኩ እድትመራ የመፈለግ አይደለም ብሏል።
ከዚያ ይልቅ እኔ ከሞትኩ ……. በሚል አመለካከት ˝እኔ ካልመራኋት ትበታተን ˝ የሚል አደጋ ከፊት የደቀነ በመሆኑ እና ኢትዮጵያን ለውጭ ጠላቶች አሳልፎ ለመስጠት የማያመነታ በመሆኑ በህግ አግባብ እንዲጠየቅ እና እንዲታረም እየተሰራ መሆኑን ጥምረቱ አስታውቋል።
አሸባሪና አገር በታኝ ቡድን ጋር ምንም ዓይነት ኅብረት የለንም -የፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት
Via – FBC
- “የትኅትና ገመድ የመጨረሻዋ ቋጠሮ ብርቱ ክንድ ናት፤ ከተሠነዘረች ሳታደቅቅ አትመለስም”“የትኅትና ገመድ የመጨረሻዋ ቋጠሮ ብርቱ ክንድ ናት። ከተሠነዘረች ሳታደቅቅ አትመለስም” ሲሉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ገለጹ። ጠቅላይ ሚንስትርሩ ይህን ያሉት ለጥምቀትና ከተራ በዓል እንኳንContinue Reading
- Ethiopia: What’s Next After Tigray?n early 2018, amidst incessant protests especially in Ethiopia’s Oromo and Amhara regions, Abiy Ahmed Ali became the new prime minister of Ethiopia. His ascentContinue Reading
- “ አንገት ቆረጣ ” የ – ሰለጠነው የ- እርስ በርስ መበላላት!ሃኪሙ የተረኛ ስም ጠራ፤ አስናቀ “ አቤት” ብሎ ከተቀመጠበት ተነሳ፡፡ ሃኪሙ አስናቀን በምልክት “ የት አለ” ሲል ጠየቀው፡፡ አስናቀ መዘናጋቱን አስታወቆ የተጠየቀውን ሊያመጣ ላፍታ ወደContinue Reading
- Death toll from violence in Sudan’s West Darfur risesCAIRO (AP) – The death toll from tribal violence between Arabs and non-Arabs in Sudan’s West Darfur province climbed to at least 83, including womenContinue Reading