ውጥኑ ወደ ተግባር ሲቅየር የሚሆነው ኦሮሞን በኦሮሞ መብላት ነው። አሁን አገሪቱን የሚመሩትንም ሆነ ኦሮሚያን የሚያስተዳደሩትን ልጆቻችንን ለወያኔ ስንል እንደንበላቸው ነው እቅዱ። እርስ በእርስ የማባላት እቅድ!! ይህ እቅድ ወይም ወንድምን ከወንድም ማባላቱ ሲጀመር እንደኔ ያሉ ስሜታቸው ህወሃትን የሚጠየፍና ለህወሃት የተሸጡ መካከል ነው ግብግቡ። ይህ ግብግብ የሚፈጥረው ትርምስ የት እና በማን አሸናፊነት ሊጠቃለል እንደሚችል በተደጋጋሚ ባስብው ሊገባኝ ስላልቻለ ነው የሚሰማኝ ካገነሁ ብዬ ይህን አጭር ሃሳብ ያሰፈርኩት


ነጻ አስተያየት – ገመቹ ከዲሲ – POSTED BY ZAGGOLENES  Oct,1,2020


“ህወሃትና የኦሮሞ ህዝብ መካከል ለሚኖረው የማይፈርስ ግንብ፣ለትውልድ የሚዘልቅ የጅምላ ጭፍጨፋ ” ሲሉ ነው ነዋሪነታቸው ሚኖሶታ የሆነ የኦሮሞ ተወላጅ በውቅቱ ስማቸውን ለቤተሰቦቻቸው ሲሉ በመደበቅ ለአንድ ሚዲያ መናገራቸውን አስታውሳለሁ። በማህበራዊ ገጾችም “ተስፋ ቁረጡ፣ ካሁን በኋላ እርቅ ጠይቆ ኦሮሞ ላይ ቁማር መጫወት አይቻልም” በሚል በመረረ ስሜት ቁጣቸው ሲገልጹ የነበሩት ቁጥር ስፍር የላቸውም። የውቅቱን አረመኔያዊ የጅምላ ጭፍጨፋ ያላወገዘ ኢትዮጵያዊ አልነበረም። ዝግናኝ ነበርና!!

በውቅቱ ጭፍጨፋውን የፈጸመው ህወሃት ለማስተባበል ቢቀላምደም በስፋራው የነበሩ ጋዜጠኞች እንደዛሬው በጽንፍ ጎዳና ሳይሰለፉ መስክረውታል። ድርጊቱ ምንም ዓይነት ማስተባበያ ሊቀርብበት የማይችል ሺሆችን የበላ የጅምላ ጭፍጨፋ ነበር። 

“ህዝብ እየጨፈጨፉ ዛፍ ሥር በመቀመጥ ይቅርታ መጠየቅ ያከተመበት አስተሳሰብ ነው” በማለት የኦፌኮ መሪ ዶክተር መረራ አምረው በይፋ ድርጊቱን ኮንነው ህወሃትና ኦሮሞ በገሃድ ግንኙነታቸው መበጠሱን አብስረው ነበር። ይህ ንዴት፣ እልህና ምሬት የቆሰቆሰው ጭፍጨፋ በየትኛውም ዘመን የማይረሳ የህወሃት ጥቁር ታሪክ ስለመሆኑ በመላው አገር በተለይም በኦሮሞ ልጆች ልብ የታተመ ስለመሆኑ ክርክር አይነሳበትም። ይህንን ማህተም የሚፍቁ ሌላ ጥቁር ታሪክ ለመስራት የተዘጋጁ እንግዴዎች ካልሆኑ በቀር።

የሰው ልጅ ” በቃኝ ” በማለቱ ብቻ በጅምላ ሲጨፈጨፍ፣ መርዝ ሲረጭበትና ሲታፈን፣ በጅምላ በታንክ ፣ በመትረየስ እየነዳ በቁሙ ጉድጓድ የከተተ ብቻኛ ባለታሪክ ቢኖር ትህነግ ነው። ትህነግ በሺዎች ሞተው ሳለ ሃምሳ አምስት ሰዎች ብቻ መሞታቸውን አምኖ ሲሳለቅ እኛ እንብተናል። ሃዘን ዘልቆን ገብቷል። ወላዶች ማቅ ለብሰው ቀርተዋል። ለነገሩ ህወሃት ምን ያልቀጠፈው ነብስ አለ? እስር ቤቱ፣ የድብቅ ማሰቃያው… 

Related stories   ሊቁ ቴዎድሮስ "አመሰግናለሁ"

ይህንን ዛሬ ኢሬቻ ዋዜማ ለይ ሆኜ ማስታወስ የፈለኩት በአንድ ምክንያት ብቻ ነው። ዛሬ ከኦሮሞ አብራክ የወጡ፣ የኦሮሞ ልጆች ዳግም ተመልሰው ወያኔ ጉያ ተወሽቀው ማየቴ ክፉኛ ስሜቴን ተፈታትኖታል። በተለይም አሁን ኦሮሚያን የጦርነት አውድማ ለማድረግ በመረጡት እቅድ ውስጥ ሆነው የነውጥ አዝማች መሆናቸው አስዝኖኛል። እኔ ብቻ ሳልሆን በርካታ ሚሊዮኖች እኔን መሰሎችን ልብ ሰብሯል።

ዛሬ ትላንት አሸባሪ፣ ጠባብና ኦነግ እያሉ ሲደፉን፣ አካል ሲያጎሉ፣ ሲያስሩና ሲያሰቃዩ እንዲሁም ሃብት ሲዘርፉ ከነበሩ ቡድኖች ጋር የሚያገናኝ ምን የጋራ ጉዳይ አለ? እኔም ሆንኩ በርካታ ኦሮሞዎች እንዲሁም ጨዋ ኢትዮጵያዊያን በጥቅሉ ዳግም ትህነግ ደጅ ወድቀው በሚልከሰከሱት የሚሰማን ስሜት ውርደትና ወርደት ብቻ እንደሆነ ይሰማኛል። ደግሞም ትክክል ነው። ውርደት ነው። ዳግም ሞት ነው። 

ውጥኑ ወደ ተግባር ሲቅየር የሚሆነው ኦሮሞን በኦሮሞ መብላት ነው። አሁን አገሪቱን የሚመሩትንም ሆነ ኦሮሚያን የሚያስተዳደሩትን ልጆቻችንን ለወያኔ ስንል እንደንበላቸው ነው እቅዱ። እርስ በእርስ የማባላት እቅድ!! ይህ እቅድ ወይም ወንድምን ከወንድም ማባላቱ ሲጀመር እንደኔ ያሉ ስሜታቸው ህወሃትን የሚጠየፍና ለህወሃት የተሸጡ መካከል ነው ግብግቡ። ይህ ግብግብ የሚፈጥረው ትርምስ የት እና በማን አሸናፊነት ሊጠቃለል እንደሚችል በተደጋጋሚ ባስብው ሊገባኝ ስላልቻለ ነው የሚሰማኝ ካገነሁ ብዬ ይህን አጭር ሃሳብ ያሰፈርኩት።

ማንኛውም የፖለቲካ ችግርም ሆነ አለመግባባት አሁን በታሰበው መልኩ መፍትሄ የሚያገኝ መስሎ የሚታየን ተሳስተናል። ኦሮሚያ ሰፊና ለመላው ኢትዮጵያ ታላቅ ሃላፊነት ያለባት ክልል ስትሆን ህዝቧም በዚሁ መጠን የተቀየጠ፣ የተለያየ አመለካከትን ያቀፈች መልከ ብዙ ናት። በመልኳ ብዛትና በዚሁ የተነሳ ባያዘችው የተለያዩ አመለካከቶች መነሻ ብስለት፣ አስተዋይነት፣ ታጋሽነትና እጅግ ብልህ መሪዎች ካላገኘች ጣጣው ብዙ ይመስለኛል። ጊዜ ካለኝ በሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ።

ለዛሬው ግን በግልጽ ለማለት የፈለኩት የውስጥ ችግራችንን ህወሃት ደጅ በመልከስከስ እንደማንፈታው፣ ከዚያም በላይ የሌለብንን ተልከስካሽነት ለልጆቻችን ባናወርስ እንደሚሻል ለመጠቆም እወዳለሁ። ከዚያም አልፎ አብሮን በኖረ ህዝብና ወዳጅ ዘመድ ላይ ከተጀመረው ክፉ ተግባር በተጨማሪ ጥቁር ታሪክ እንዳናስቀምጥ ፍርሃቻዬን ለመግለጽ እወዳለሁ።

Related stories   NUTI TOKKO" እኛ አንድ ነን "- አገራዊ እርቅ ቢደረግና ሁሉም ከቂም ፖለቲካ ነጻ ቢወጣስ?

በማናቸውም መስፈርት ከልጆቻችን ጋር ተጣልተን ለትህነግ ባንዳና ተልከስካሽ የሚያደርገን ጉዳይ የለምና ልብ እንበል። ህወሃት በቸፈጨፋቸው፣ አካላቸውን ባጎደላቸውና ባሰቃያቸው ወገኖች ደምና ቤተሰቦች ላይ ጥቁር ጠባሳ አናሳድር። ኢሬቻን አንድም ሰው ሳይሞት እናሳልፍ!!

ገመቹ ከዲሲ 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *