በየደረጃው ያለው የፀጥታ ኃይል ፀረ-ሰላም ኃይሎች እየሠሩ ያሉትን አገር የማፍረስ ሴራ የማስቆም የመቆጣጠርና የዜጎችን ሰላምና ደኅንነት የመጠበቅ ኃላፊነቱን የሚወጣ መሆኑን ያረጋግጣል። ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ቡድን የሀገሪቱን ሕግ በማክበርና በማስከበር የዜግነት ግዴታውን ሊወጣ ይገባል። ከዚህ ያለፈ ሕገ ወጥ እንቅሰቃሴዎችን ግን በየደረጃው ያለው የፀጥታ ኃይል ሕግን በተከተለ መንገድ ተገቢውን ሕጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ይገልፃል።

ሀገራችን የለውጥ ጉዞ ከጀመረች ጊዜ ጀምሮ ዓለምን ያስደመሙ በዓለም አቀፍ ደረጃም ዕውቅና የተቸራቸውና በርካታ ሥራዎች ይሁንታ ያገኙ ተግባራት መከናወናቸው ይታወቃል።

ባለፉት ሁለት ዓመት ተኩል ሆነ በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱን ዜጎች የሚጠቅሙና ሀገራችን ከገባችበት ችግር ሊያወጡ የሚችሉ፤ ዕደገትና ሰላምን የሚያረጋግጡ ሥራዎች በመሠራት ላይ ናቸው።

እንደሚታወሰው ታዋቂ ሰዎችና ፖለቲከኞች እንዲሁም ነፍጥ አንግተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የፖለቲካ ድረጅቶችም ጭምር በሰላማዊ ጥሪ ሀገር ውስጥ ገብተው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።

በተለያዩ ጊዜያትም በርካታ ሕዝባዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ሁነቶች በሰላማዊ መንገድ መከበራቸውም ይታወቃል።

ባለፈው ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ትልቅ ከበሬታ ያለው የኢሬቻ በዓል በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ የክልሉ ተወላጆችና ሌሎች ኢትዮጵያውያን በታላቅ ድምቀት እጅግ ሰላማዊ በሆነ መልኩ ተከብሮ እንደነበር አይዘነጋም።

Related stories   Speaking Truth to Power, Samantha: Stop Defending Ethiopia’s “Proud Boys”!

ዘንድሮ ግን የዓለማችን ክስተት በሆነው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የአደባባይ በዓላት በውስን ሰዎች እንዲከበር አስገድዷል።

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባስቀመጠው ምክረ ሐሳብ መሠረት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የመስቀል በዓል በቤተ ክርስቲያኗና በሚመለከታቸው አካላት በጋራ በወሰኑት መሠረት የሃይማኖቱ ተከታዮችና ዓለም አቀፍ ታዳሚዎች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት በሰላም ተከብሯል። የበዓሉ ዝግጅት በሰላማዊና በደማቅ ሥነ-ሥርዓት እንዲከበር የቤተ ክርስቲያኗ ከፍተኛ መሪዎች፣ የሃይማኖቱ ተከታዮችና ኅብረተሰቡ እንዲሁም የፀጥታ አካሉ በጥምረት ስለሠሩት ተግባር ብሔራዊ የፀጥታ አስተባበሪ ኮሚቴው የላቀ ምስጋና ያቀርባል።

በመሆኑም በመጭው ቅዳሜና እሑድ በአዲስ አበባና በቢሾፍቱ በታላቅ ድምቀት የሚከበረውን የኢሬቻ በዓል የአባ ገዳዎች ምክር ቤትና የክልሉ መንግሥት በወሰኑት መሠረት በውስን የበዓሉ ታዳሚዎች ቄሮዎች፣ በቀሬዎችና ጥሪ የተደረገላችው እንግዶች በተገኙበት እንዲከበር መግባባት ላይ ተደርሷል። ሆኖም በዓሉ በሰላም እንዳይከበር ለማድረግና ብሔርን ከብሔር ለማጋጨትና በዜጎች ዘንድ መተማመን እንዳይኖር ውዥንብር ለመፍጠር አንዳንድ ፀረ ሰላም ኃይሎች ከወዲሁ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን የብሔራዊ ፀጥታ አስተባባሪ ኮሚቴው ደረሶበታል።

በተጨማሪም በበዓሉ ላይ የተለያዩ ጉዳቶችን ለማድረስ ሽብር ፈፃሚ ኃይሎችን በመመልመል እና በማሰልጠን እንዲሁም በማስታጠቅ እያሰማሩ ሲሆን ከተሰማሩት ውስጥም ውስን የጥፋት ቡድኖች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ለዚህ እኩይ ተግባር ማስፈፀሚያ የሚጠቀሙበት የተለያዩ ጦር መሣሪያና በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ገንዘብ በቁጥጥር ስር ውሏል።

Related stories   US Attempt To Make Pronouncements On Ethiopia’s Internal Affairs Regrettable :MoFA

ይህ የጥፋት ኃይል የተለያዩ የሽብር ውዥብሮችን በመንዛት ሀገር የማፍረስና የማተራመስ እኩይ ተግባሩን ቀጥሎበታል።

በመሆኑም ይህ ውስን የጥፋት ኃይል በሀገራችን ለዘመናት የዳበረውን የመቻቻልና የአብሮነት እሴት ለመናድ እያደረገ ያለውን አፍራሽ ዝግጅት ለማምከን መላው የፀጥታ ኃይላችን ሌት ተቀን ከሕዝባችን ጋር በመሆን እየሠራ ይገኛል።

በየደረጃው ያለው የፀጥታ ኃይል ፀረ-ሰላም ኃይሎች እየሠሩ ያሉትን አገር የማፍረስ ሴራ የማስቆም የመቆጣጠርና የዜጎችን ሰላምና ደኅንነት የመጠበቅ ኃላፊነቱን የሚወጣ መሆኑን ያረጋግጣል።

ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ቡድን የሀገሪቱን ሕግ በማክበርና በማስከበር የዜግነት ግዴታውን ሊወጣ ይገባል። ከዚህ ያለፈ ሕገ ወጥ እንቅሰቃሴዎችን ግን በየደረጃው ያለው የፀጥታ ኃይል ሕግን በተከተለ መንገድ ተገቢውን ሕጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ይገልፃል።

መልካም የኢሬቻ በዓል ለሁላችን እንዲሆን ፀጥታ አስተባባሪ ኮሚቴው ይመኛል!
ብሔራዊ ፀጥታ አስተባባሪ ኮሚቴ።

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *