የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ በኢትዮጵያ አዲሱ የብር ለውጥ ከተጀመረ ወዲህ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ገንዘብ ወደ ባንክ ስርዓቱ መመለሱንና 580 ሺህ ዜጎች አዲስ የባንክ የሂሳብ መክፈታቸውን አስታወቁ።
አዲሱ የብር ለውጥ ከተጀመረ ባሉት 14 ቀናት ውስጥ ብቻ 580 ሺህ ዜጎች አዲስ የሂሳብ አካውንት መክፈታቸውን ትፋ ያደረጉት አቶ ይናገር፣  ከባንክ ስርዓት ውጭ ከሚንቀሳቀሰው ሃብት ውስጥ 14 ቢሊዮን ብር ወደ ባንክ ስርዓት መግባቱን አመልክተዋል።
67 ቢሊየን አዲሱን የብር ኖት በመላ አገሪቱ ባሉ 99 ነጥብ 9 በመቶ የባንክ ቅርንጫፎች ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲደረስ መደረጉን የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ ተናግረዋልልል
የብር ለውጡ ያስፈለገበት አንዱ ዓላማ ከባንክ ውጭ ያለን ገንዘብ ወደባንክ የማስመለስ ጉዳይ እንደነበር ያስታወሱት የባንኩ ገዥ ÷ ከዚህ አንጻር በአጭር ጊዜ ውስጥ ይሄንን ያህል ገንዘብ ወደ ባንክ ስርዓቱ መመለሱ የዓላማውን መሳካት ያሳያል ብለዋል።
የብር ለውጡ ሌላኛው ዓለማ የባንክ አገልግሎት ተደራሽነትን ማሳደግ እንደሆነ የገለጹት ዶክተር ይናገር÷ አዲስ የባንክ ሂሳብ ከተከፈቱት 580 ሺህ ዜጎች በተጨማሪ በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎች አካውንት ይከፍታሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ህብረተሰቡ በተያዘው የጊዜ ገደብ ውስጥ በእጁ ያለውን አሮጌ የብር ኖት በአዲሱ መቀየር እንዳለበትም ዶክተር ይናገር ማሳሰባቸውን ኢቢሲ ነው የዘገበው።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   Ministry Urges Amnesty Int’l to Use Appropriate Sources in Report to Uncover the Truth

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *