ማህበራዊ ድረ-ገጽን በአግባቡ አለመጠቀም የህግ ተጠያቂነትን እንደሚያስከትል ተገለጸ፡፡ ቅጣቱ በህግ በተደነገገው መሰረት እስከ መቶ ሺህ ብርና አምስት ዓመት የሚደርስ ቅጣት እንደሚያስቀጣ ተገለጸ።
በሀገራችን ከማህበራዊ ድረ-ገጽ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ ክፍተቶች እንደሚስተዋሉ በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ህግ የሰውዘር አበበ ናቸው የገለጹት።
የማህበራዊ ድረ-ገጽ አጠቃቀምን በማዘመንና በህግ በተቀመጠው አግባብ በመጠቀም እራስን ከተጠያቂነት መከላከል እንደሚገባ የገለጹት ዐቃቤ ህጓ የማህበራዊ ድረ-ገጽ አጠቃቀምን አስመልክቶ በህግ የተቀመጡ ገደቦችን ሳያልፉ ለታለመለት አላማ ብቻ በመጠቀም ተገቢ ነው ብለዋል፡፡
ነገር ግን የማህበራዊ ድረ-ገጽን ላልተፈለገ እኩይ ተግባር በማዋል የሀሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግ ለማስተላለፊያነት በመጠቀም የሌሎችን ሰብዓዊ ክብር የሚነኩ እንዲሁም ባልተጨበጠ መረጃ ህብረተሰቡ ግራ እንዲጋባ ለማድረግ ያለአግባብ በሚጠቀሙ አካላትን ተጠያቂ የሚያደርግ የሀሰሰኛ መረጃ ስርጭትና የጥላቻ ንግግን የሚከለክል አዋጅ ወጥቶ ስራ ላይ እንደዋለ አስታውሰዋል፡፡
በአዋጁ ከተካተቱት መካከልም የጥላቻ ንግግርን በብሮድካስት፣ በህትመት ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ወይንም ሌላ ተመሳሳይ ዘዴዎችን በመጠቀም ያስተላለፈ እስከ 2 አመት በሚደርስ እስራትና በብር 100,000 እንደሚያስቀጣ አብራርተዋል፡፡
በተጨማሪም በተላለፈው የጥላቻ ንግግር ምክንያት በግለሰብ ወይም በቡድን ላይ ጥቃት ደርሶ እንደሆነ የቅጣቱ ጊዜ እስከ 5 ዓመት የሚደርስ ሲሆን ሀሰተኛ መረጃዎችን በአደባባይ ስብሰባዎች፣ በብሮድካስት፣ በማህበራዊ ሚዲያ ወይም በሌላ ተመሳሳይ ዘዴዎች አማካኝነት በምስል፣ በጽሁፍ ወይም በቪዲዮ በመጠቀም ያሰራጨ እንደሆነ 1 ዓመት በሚደርስ እስራት ወይም በ50,000 ብር ቅጣት ሊተላለፍበት ይችላል ያሉት ዐቃቤ ህጓ መረጃው ከ5000 በላይ ተከታይ ባለው ማህበራዊ ድረ-ገጽ የተላለፈና ጉዳት የደረሰ እንደሆነ ግን የቅጣት መጠኑ ከ2 እስከ 5 ዓመት ሊደርስ ይችላል ብለዋል፡፡
ምንጭ – አቃቤ ህግ
- በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በተጠርጠሩ አራት ተከሳሾች ብይን ሰጠየፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የፀረ-ሽብርና ሕገ መንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ምርመራ ችሎት በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ተጠርጥራ የነበረውን ላምሮት ከማልን በነጻ አሰናበተ። የተቀሩትን ሦስቱንContinue Reading
- በእነ ጃዋር የህክምና ጥያቄ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሁሉንም ተከራካሪዎች ጥያቄ ውድቅ አደረገ፤ ቃሊቲ ሆነው ይታከማሉ፤በእነ ጃዋር ጉዳይ ይግባኝ የቀረበለት የየቅላይ ፍርድ ቤት የክፍተኛውን ፍርድቤትና የአቃቤ ህግ ይግባኝ ውድቅ አድርጎ አዲስ ውሳኔ አሳለፈ። የፌደራል ማረሚያ ቢት ምክትል አስተዳዳሪ ታስረርው እንዲቀርቡContinue Reading
- የሙለር ሪል ስቴት ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ በሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸውየሙለር ሪል ስቴት ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ በሙስና ወንጀል ዐቃቤ ህግ ክስ መሰረተባቸው፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በዛሬው እለት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮContinue Reading
- ከህዋሓት አመራሮች የጥፋት ተልዕኮ ተቀብሎ ጥቃት ለማድረስ ተንቀሳቅሷል የተባለ ተጠርጣሪ ላይ ክስ ሊመሰረት ነውከህዋሓት አመራሮች የጥፋት ተልዕኮ ተቀብሎ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ህዝብ ላይ ጥቃት ለማድረስ ተንቀሳቅሷል የተባለ ተጠርጣሪ ላይ ክስ ሊመሰረት ነው ከህዋሓት አመራሮች የጥፋት ተልዕኮ ተቀብሎ በአዲስContinue Reading