የአዲስ አበባ ፖሊስ በህገወጥ መንገድ የተከማቸ ከ2 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ብር በህዝብ ጥቆማ መያዙን አስታወቀ።
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በአንድ ንግድ ቤት ውስጥ የተከማቸ ከ2 ሚሊዮን 6 መቶ ሺህ በላይ የኢትዮጵያ ብር በህዝብ ጥቆማ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ኮሚሽኑ ገልጿል።
ከባንክ ውጪ የሚገኙ በርካታ ብሮችን ወደ ባንክ እንዲገቡ በማድረግ የኢኮኖሚ ሥርዓቱን ለማስተካከል እና የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር ታሳቢ ባደረገ መንገድ የብር ኖት መቀየሩን ተከትሎ የሚፈፀሙ ህገ- ወጥ ተግባራትን ለመከላከል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በርካታ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ደንበል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአንድ የንግድ ቤት ውስጥ የተከማቸ ገንዘብ ስለመኖሩ ከህዝብ ጥቆማ መምጣቱን የደንበል አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ሀላፊ ኢንስፔክተር ሰለሞን ደጀኔ የጠቀሱ ሲሆን ፖሊስም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በማውጣት በንግድ ቤቱ ላይ ባደረገው ብርበራ ብሄራዊ ባንክ ካስቀመጠው መመሪያ ውጪ ተከማችቶ የተገኘ 2 ሚሊዮን 631 ሺህ 735 አዲሱን እና ነባሩን የኢትዮጵያ ብር በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልፀዋል፡፡
(ኢትዮ ኤፍ ኤም) ፎቶ ጎልጉል
- መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋልሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የጁንታውን ሃይል በከፍተኛ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቁ። ” ጁንታው ካሁን በኋላ ሰራዊትና ጠባቂ ይዞ መንቀሳቀስ አይችልም”Continue Reading
- Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho… To set the record, Mr. Obang, my self as part of his admirers and supporters, started out his career in search of justice for hisContinue Reading
- ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫኢዜማ አዲስ አበባ ላይ ካሸነፈ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግለሰብ ንብረት በሁለት ዓመት ውስጥ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ። የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ነጋ ለዓመታት እንደ ፖለቲከኛም ሆነ እንደContinue Reading
- “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገውአዲስ አበባ በጥናት የተዘረፉ ዜጎች ቁጥር ቀላል አይድለም። ስም መጥቀስ አያስፈልግም እንጂ ያለውን አስረክቦ በባልደረቦቹ ድጋፍ ከእብደት የዳነ ስፖርተኛ ታላቅ ምሳሌ በሆነ ነበር። አንድ በህይወትContinue Reading