በህገወጥ መንገድ የተቋቋመ ነው ላለው የትግራይ ክልል ምክር ቤት እና ካቢኔ የፌዴራል መንግሥት የበጀት ድጎማ እንደማያደርግ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስታወቀ፡፡
የክልሉ ምክር ቤት እና ከፍተኛው የህግ አስፈፃሚ አካል (ካቢኔ) ህገመንግሥታዊ ቅቡልነት የላቸውም ያለው ምክር ቤቱ ሁሉም የፌዴራል ተቋማት ምንም ዓይነት ህጋዊ ግንኙነት ማድረግ እንደማይችሉ ገልጿል፡፡
ተቋማቱ የክልሉን ከፍተኛ ስራ አስፈፃሚ አካላት እንደ ህጋዊ አካል በመቁጠር ደብዳቤ መፃፃፍ፣ መረጃ መላላክ፣ ድጋፎች ማድረግ፣ በፌዴራል ደረጃ በሚካሄዱ መድረኮች ላይ ማሳተፍ እንደማይችሉም ነው የምክር ቤቱ አፈ-ጉባዔ አቶ አደም ፋራህ የተናገሩት፡፡
በአንጻሩ የክልሉ ህዝብ መሰረታዊ የልማትና የአገልግሎት ተጠቃሚነቱ እንዳይስተጓጎል እንደ ቀበሌ፣ ወረዳ፣ ከተማ ካሉ ህጋዊ የክልሉ መዋቅሮች ጋር ብቻ ግንኙነት እንደሚደረግ እና ይህም በሚዋቀር ኮሚቴ ክትትል እንደሚደረግ አፈ-ጉባዔው በተለይ ለኢቲቪ አስታውቀዋል፡፡
ከዚህ ውሳኔ ሊደረስ የቻለው የትግራይ ክልል መንግሥትና ገዥው ፓርቲ ህውሃት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔን ባከበረ መልኩ የሥራ ዘመኑ በምክር ቤቱ ውሳኔ የተራዘመውን የክልሉን ምክር ቤት የህግ አስፈፃሚ አካል ወደ ቦታው መመለስ ስላልቻሉ ነው ብለዋል አፈ ጉባኤው፡፡
ውሳኔው የትግራይ ህዝብ ኢ-ህገመንግሥታዊ አካሄድ እየተከተለ ባለ ቡድን ምክንያት ከሰላም፣ ልማትና መሰረታዊ አገልግሎት አንፃር እንዳይጎዳና የትግራይ ህዝብ እንደሌሎች የአገራችን ህዝቦች መሰረታዊ የልማትና የደህንነት አገልግሎቶች እንዲያገኙ ታስቦ መተላለፉንም አመልክተዋል፡፡
“ይሄ ሊሆን የቻለው ለትግራይ ህዝብ ካለን ክብር ነው” ያሉት አቶ አደም “ህዝብም እንደ ሌሎች የአገራችን ህዝቦች ሊያገኘው የሚገባውን ጥቅም ሊከበርለት ይገባል ከሚል ጽኑ እምነት የመነጨ ነው” ሲሉም ተናግረዋል፡፡
የውሳኔ አፈፃፀምም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጥናት ላይ ተመስርቶ የሚከናወን ይሆናል ተብሏል፡፡
በቀጣይ በክልሉ ካሉ የከተማ አስተዳደሮች፣ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ጋር ስለሚኖረው ግንኙነት በተለይ ህዝቡ ማግኘት የሚገባውን መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዲያገኝ በጥናት ተመስርቶ ተፈፃሚ ይደረጋልም ተብሏል፡፡
በወረርሽኙ ምክንያት የ6ኛውን ሃገራዊ ምርጫ መራዘም በመቃወም የራሱን ክልላዊ ምርጫ ያደረገው የትግራይ ክልል ህገ መንግሥቱን በብቸኝነት እንዳከበረ በመግለጽ ከመስከረም 25 በኋላ የፌዴራሉ መንግስት ህጋዊ የስልጣን ዘመን እንደሚያበቃ እና እውቅና የሚሰጠው የፌዴራል መንግሥት እንደማይኖር ማስታወቁ የሚታወስ ነው፡፡
ይህ የድጎማ በጀቱን የተመለከተው ውሳኔ በፌዴራሉ እና በክልሉ መንግሥት መካከል ያለውን ውጥረት ይበልጥ እንደሚያከረው ይጠበቃል፡፡ (EBC)
- Ethiopia: What’s Next After Tigray?n early 2018, amidst incessant protests especially in Ethiopia’s Oromo and Amhara regions, Abiy Ahmed Ali became the new prime minister of Ethiopia. His ascentContinue Reading
- “ አንገት ቆረጣ ” የ – ሰለጠነው የ- እርስ በርስ መበላላት!ሃኪሙ የተረኛ ስም ጠራ፤ አስናቀ “ አቤት” ብሎ ከተቀመጠበት ተነሳ፡፡ ሃኪሙ አስናቀን በምልክት “ የት አለ” ሲል ጠየቀው፡፡ አስናቀ መዘናጋቱን አስታወቆ የተጠየቀውን ሊያመጣ ላፍታ ወደContinue Reading
- Death toll from violence in Sudan’s West Darfur risesCAIRO (AP) – The death toll from tribal violence between Arabs and non-Arabs in Sudan’s West Darfur province climbed to at least 83, including womenContinue Reading
- Violence flares for third day in Sudan’s DarfurMilitia fighters staged a deadly attack in Sudan’s Darfur on Monday, residents said, as doctors said the death toll from a separate attack that beganContinue Reading