በቦሌ ክፍለ ከተማ ከ2 ሚሊየን ብር በላይ የሀሰተኛ ብር ኖት ሲያዘጋጁ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን ለአቤቱታ ፖሊስ ጋር መጥተው በነበሩ ግለሰብ ጥቆማ ሰጪነት በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርን በመቆጣጠር የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ሥርዓት ለማረጋጋት የተጀመረውን አሮጌ የገንዘብ ኖቶችን ቅያሪ ተከትሎ የሚከሰቱ የተለያዩ የወንጀል ድርጊቶችን ለመቆጣጠር ፖሊስ ጥብቅ የወንጀል መከላከል ተግባሩን እያከናወነ እንደሚገኝ ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ያሬድ ታረቀኝ እንደተናገሩት ሁለት ተጠርጣሪዎች ከሀሰተኛ የብር ኖት በተጨማሪ የአሜሪካ ዶላር እና የተለያዩ አገራትን ገንዘቦችን በመኖሪያ ቤታቸው ሲያዘጋጁ ከሚጠቀሙበት የተለያዩ ቁሳቁሶች ጋር እጅ ከፍንጅ በመያዝ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ተጠርጣሪዎቹ የኮትዲቫር ተወላጆች ሲሆኑ ወደ ኢትዩጵያ የመጡት ለጉብኝት በሚል ሰበብ የገቡና በጉሙሩክ በኩል ምንም ዓይነት ያስመዘገቡት ንብረት እንደሌላቸው በመግለጽ ዋነኛ አላማቸው የሀሰተኛ የብር ኖቶችን ለማባዛትና ለማሰራጨት እንደሆነ አስበው ወደሀገር ቤት መግባታቸውን የምርመራ መዝገባቸውን ዋቢ አድርገው ኃላፊው ገልጸዋል፡፡
ኃላፊው ባስተላለፉት መልዕክት ወቅትን ጠብቀው የሚፈጸሙ የወንጀል ድርጊቶችን ለመከላል ፖሊስ የሚያደርገውን ጥረት በማገዝ በኩል የህብረተሰቡ ተባባሪነት የሚደነቅ መሆኑን አብራርተው ህብረተሰቡ ተባባሪነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማስተላለፋቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ምንጭ – ፋና
- ወርቃማ ድል የተጎናጸፍነው ትልቁን ስዕል ማየት የሚችሉ ፣ ችግሮቻቸውን የመፍታት ልምድ ያላቸው እናትና አባቶች ስላሉን ነው – ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ”በስልጡን ምክክር አዲስ ተስፋ ምዕራፍ “በሚል መሪ ሀሳብ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የነበረውን የምክክር መድረክ የማጠቃለያ ፕሮግራም በወዳጅነት አደባባይ ተካሂዷል። በዚህ መርሃ ግብር ላይ ፕሬዚዳንትContinue Reading
- አለቃ አጽመ ጊዮርጊስ – የተሳሳተውን የውጫሌ ውል የመረመሩ ጀግና ኢትዮጵያዊአለቃ አጽመ ጊዮርጊስ – የተሳሳተውን የውጫሌ ውል የመረመሩ ጀግና ኢትዮጵያዊ ባሕር ዳር፡ የካቲት 23/2013 ዓ.ም (አብመድ) አለቃ አጽመ ጊዮርጊስ የውጫሌ ውል ጣልያንኛ ትርጉም ኢትዮጵያን ጥገኛContinue Reading
- The Legend of the “Greater Republic of Tigray” and the Delirious TPLF MediaAfter TPLF’s humiliating defeat at the war it has started, its remnants and well-funded social media continued to spread lies and fabricated news, as theyContinue Reading
- እውነትን ለሥልጣን መናገር !! ሳማንታ ፖወር – ለኢትዮጵያ ዘር ፖለቲከኞች መከላከል አቁሚ!እ.ኤ.አ. በሚያዝያ ወር መጨረሻ ላይ በሪቻርድ ክላርክ ስር የሰራችው በNSC መረጃ ክፍል ውስጥ ስትሰራ የነበረችው ሱዛን ራይስ ፣ “የዘር ማጥፋት ወንጀል” የሚለውን ቃል የምንጠቀም ከሆነContinue Reading