ለጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በተጠራ የድጋፍ ሰልፍ ላይ በተቀነባበረ ትስስር ቦንብ ወርውረው ጉዳት ያደረሱ ተከሳሾች ላይ ከ5 እስከ እድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንደተፈረደባቸው ተገለጸ።
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በኦፊሳል ገጹ ይፋ እንዳደረገው ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተጠራው የድጋፍ ሰልፍ ላይ በመስቀል አደባይይ ቦንብ በመወርወር ለሁለት ሰዎች ህይወት ማለፍ እና ለ150 ሰዎች የአካል ጉዳት መድረስ ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ 5 ግለሰቦች ከ5 ዓመት እስከ እድሜ ልክ ፅኑ እስራት ቅጣት እንደተወሰነባቸው ይፋ አድርጓል።
በዚሁ መሰረት 1ኛ ተከሳሽ ጌቱ ግርማ በ23 ዓመት፣ 2ኛ ተከሳሽ ብርሀኑ ጃፈር 22 ዓመት፣ 3ኛ ተከሳሽ ጥላሁን ጌታቸው በእድሜ ልክ፣ 4ኛ ተከሳሽ ባህሩ ቶላ በ17 ዓመት እንዲሁም 5ኛ ተከሳሽ ደሳለኝ ተስፋዬ በ5 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የህገ መንግስት እና የፀረ ሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ብይን መስጠቱ ታውቋል።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በተጠርጠሩ አራት ተከሳሾች ብይን ሰጠ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *