የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶከተር ደብረጽዮን ገ/ ሚካኤል የትግራይ ሕዝብ ዝግጅቱን አጠናክሮ እንዲጠብቅ ማሳሰባቸውን “አሁን የደረሰን ዜና” ዜና ሲል የትግራይ ማስ ሚዲያ ኤጀንሲ አስታወቀ።
በወለጋ ጉሊሶ እጅግ ዘግናኝ የተባለ የጅምላ ጭፍጨፋ በአማራ ተወላጆች ላይ መፈጸሙን ተከትሎ የትግራይ ሕዝብ ዝግጁ እንዲሆን ጥሪ ያቀረቡት መስተዳድሩ የሃይል እርምጃ መወሰዱን ጠቁመዋል።
የሃይል እርምጃ ወሰደ ሲሉ የከሰሱት የፌደራል መንግስትን ሲሆን የትና መቼ እርምጃው እንደተወሰደ በይፋ የተገለጸ ነገር የለም። በደፈናው ህብረተሰቡ ዝግጅቱን እንዲያጠናክር ጥሪ ያስተላለፉት ርዕሰ መስተዳድሩ የዝግጅቱን አይነትም አልጠቆሙም።
ህወሃት ከገዢው ፓርቲ ራሱን ካገለለ በሁዋላ እየተካረረ የሄደው ልዩነት ዋና መንስዔ ለበርካቶች ግልጽ ባልሆነበት ሁኔታ ህወሃት ሰፊ ቁጥር ያለው ሚሊሻና ልዩ ሃይል መልምሎ ሲዘጋጅ እንደነበር ይታወቃል። በተላያዩ ጊዜያት እንደተደመጠው ክልሉ ቀለብ በማዘጋጀት፣ ምሽግ በመቆፈርና የጦርነት ዝግጅት በማድረግ ላይ መቆየቱ የሚታወስ ነው።
- ምክር ቤቱ በሕግ ማስከበር ዘመቻ ጉዳት ለደረሰባቸው የሠራዊቱ አባላት 9 ሚሊዮን ብር የሚገመት የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ አደረገየኢትዮጵያ ዳያስፖራ ተግባር ምክር ቤት በትግራይ ክልል በተካሄደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ጉዳት ለደረሰባቸው የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት የሚውል የ160 ሺህ ዶላር እና 2 ሚሊዮን ብርContinue Reading
- ዝነኛው የቴሌቭዥን መርሀ ግብር መሪ ላሪ ኪንግ አረፈዝነኛው አሜሪካዊ የቴሌቭዥን መርሀ ግብር መሪ ላሪ ኪንግ በ87 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ሎስ አንጀለስ ውስጥ በሚገኝ ካዳርስ-ሲናይ በተባለ ሆስፒታል ውስጥ ሕይወቱ እንዳለፈ ተገልጿል።Continue Reading
- Gov’t Condemns Claim Ethiopia “Using Hunger as Weapon”: State of Emergency Fact Check( ENA ) Ethiopia State of Emergency Fact Check stated today the Gov’t of Ethiopia condemns in the strongest of terms the accusation that itContinue Reading
- ክቡር ገና በመጪው ምርጫ ኢዜማን ወክለው በአዲስ አበባ ምክር ቤት ለመወዳደር በዕጩነት ቀረቡየኢዜማ መሪ እና ምክትላቸው ለተወካዮች ምክር ቤት ለመወዳደር ነገ በየምርጫ ወረዳዎቻቸው ይፎካከራሉ በተስፋለም ወልደየስ የቀድሞው የኢትዮጵያ እና የአዲስ አበባ ምክር ቤት ፕሬዘዳንት የነበሩት አቶ ክቡር ገና፤Continue Reading