የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በምዕራብ ወለጋ ዞን በተፈጸመው ጥቃት ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር ሰላሳ ሁለት እንደሆኑ፣ ጥቃቱን የመራውና ያቀነባበረው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር እያለ ራሱን የሚጠራው ቡድን ከኦነግ ሸኔ ጋር እንደፈጸሙት ተገለጸ። ከድርጊቱ ፈፃሚዎች የተወሰኑት መያዛቸው ታውቋል።
በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቃንቃ ቀበሌ በተፈጸመው ጥቃት ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር ሰላሳ ሁለት እንደሆነ የገለጹት
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል አራርሳ መርዳሳ ናቸው። ኮሚሽነሩ ዛሬ ማምሻውን ለኢቢሲ እንዳሉት፤ በጥቃቱ የተነሳ የተፈናቀሉ 200 ያህል አባወራዎችን ናቸው።
የዞኑ አስተዳደር ለአማራ ቲሌቪዥን እንዳሉት ጥቃት አድራሺዎቹ ከብት በመጠበቅና እርሻቸው ላይ የነበሩ ሰላማዊ ሰዎችን ስብሰባ ጠርተው ጥድ ዛፍ ስር ከሰበሰቡ በሁዋላ ነው የገደሏቸው። ግድያው እጅግ ዘግናኝ ሲሆን ሕዝብ እንዲያየው ቀረጻው ሲጠናቀቅ አየር ላይ እንዲውል እንደሚላክ አስታውቀዋል።
መኖሪያ ቢቶችን፣ የሰብል መጠበቂያ ማማዎችን፣ በጎተራ ያለ እህል በእሳት ያጋዩት ወንበዴዎች 800 የሚሆኑ ክብቶችና ክብቶቹን እንዲነዱ አስር የሚጠጉ ሰዎችን አግተው መውሰዳቸውን አስተዳዳሪው አመልክተዋል።
በተፈጸመው ጥቃት 23 ወንድና 9 ሴቶች በድምሩ 32 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የገለጹት ኮሚሽነር ጄኔራሉ፤ 10 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና እየተከታተሉ እንደሚገኙ አመልክተዋል።
በጥቃቱ የመኖሪያ ቤቶችና አንድ ትምህርት ቤት እንደተቃጠለ ተናግረው፤ ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር በመተባበር መልሶ የማቋቋም ስራ መጀመሩን ገልጸዋል።
የጥቃት ድርጊቱን የፈጸመው አካል ኦነግ ሸኔ መሆኑን ገልጸው፤ ከጀርባ በመሆን የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) እየደገፈው እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በተለይም ቡድኑ የታጠቃቸው እንደ ስናይፐርና ብሬል ያሉ የጦር መሳሪያዎች ህወሃት ያስታጠቀው እንደሆነ ገልጸዋል። ከኦነግ ጀርባ በመሆን ህወሃት በህብረተሰቡ ላይ ጥፋት እያደረሰ እንደሆነም ገልጸዋል።
ጥቃት የተፈጸመበት ቀበሌ ከወረዳ ከተማ በ75 ኪሎ ሜትር የሚርቅ መሆኑን ገልጸው፤ ህወሃት በብሔሮች መካከል ግጭት ለመፍጠር በስሌት የፈጸመው ተግባር ስለመሆኑ ማረጋገጫ መኖሩን ተናግረዋል። ትህነግ ይህ ከሆነ በሁዋላ አስቀድሞ ለክልሉ ህዝብ ራስህን አዘጋጅ የሚል ጥሪ በዶክተር ደብረጽዮን አማካይነት ተላልፏል።
ከድርጊቱ ፈጻሚዎች መካከል የተወሰኑት መያዛቸውን ያመለከቱት ኮሚሽነር ጀነራሉ ቀሪዎቹን ለመያዝ አሰሳው ቀጥሎ እንደሚገኝ ገልጸው፤ ተመሳሳይ ጥቃት እንዳይፈጸም ከህብረተሰቡ ጋር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የመከላከያ ሰራዊት፣ የኦሮሚያ ልዩ ሃይልና የፌደራል ፖሊስ በሶስት አቅጣጫ ከበባ አድረገው ወንበዴዎቹን እያሰሱ መሆኑንን መንግስት አስታውቋል።
የአማራ ክልል፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ የኦሮሚያ ክልልና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ” ይህንን ተጋባር ከሚፈጽምና ከሚያስፈጽም ቡድን ጋር በዚህ መልኩ መቀጠል ስለማይቻል በቃ ሊባል ይገባል” ለሚለው የህዝብ ጥያቄ መልስ ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን የሚያመላክት መግለጫ በየፊናቸው አውጥተዋል።
- ትህነግ ከትግራይ አስተዳደር ጋር መሳሪያ አስረክቦና ጦሩን በትኖ እንዲደራደር ታስቧል፤ መንግስ የተረፈውን ሃይል ሊያጸዳ ነውራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር / ትህነግ ብሎ የሚጠራው ቡድን አሁን ካለበት ዋሻ በመውጣት ወደ ሰላማዊ ውይይት ለመውጣት በውጭ አገር ባሉት አመራሮቹ በኩል ድርድርContinue Reading
- ም.ጠ.ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከካናዳው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር – ሳህለወርቅ ዘውዴ ከኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር ተወያዩየውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከካናዳው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ጋርኒው ጋር በስልክ ተወያዩ፡፡ በውይይታቸው ወቅትም ስለትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ገለጻContinue Reading
- ትግራይን እንደ ማይናማር!… ኘሮጀክቱ የግብፅን ፍላጎት ለማሳካት በሰብአዊ ድጋፍ ስም የሚካሄድ ሴራ ሊሆንም ይችላል። ግብፅ ደግሞ ከኢትዮጵያ የተሻለች የአሜሪካ ስትራቴጂክ ወዳጅ መሆኗንም መርሳት አያስፈልግም። ሱዳንም በኢትዮጵያ ላይ የታቀደውንContinue Reading
- ኦፌኮ ራሱን ከምርጫው ማግለሉን አረጋግጧልየኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ከዘንድሮ አገራዊ ምርጫ ሙሉ ለሙሉ መውጣቱን ያረጋገጠ ሲሆን በእነ አራርሶ ቢቂላ የሚመራው ኦነግ በበኩሉ፤ በቅርቡ ጠቅላላ ጉባኤ አድርጎ በምርጫው የመሳተፍ ፍላጎትና ዝግጁነትContinue Reading