ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት/ትህነግ) በማለት የሚጠራውና በኢትዮጵያ እጅግ አስከፊ የሚባልና ትውልድን ያወደመ ርዕዮት በመከተል አገር ያፈረሰው የወንበዴዎች ጥርቅም፤ እስካሁንም በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት በአሸባሪነት ተመዝግቦ የሚገኝ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል። አባላቱና ደጋፊዎችም በዚሁ ሁኔታ የሚታዩ መሆናቸውን ብዙዎች የሚስማሙበት ነው።
ለአብነት ያህል፤ በአዲስ አበባ በሚኒባስ የፈነዳ ቦምብ በኦነግና በኤርትራ ላይ የተሳበበ መሆኑን የሚያስታውሱ ወገኖች ህወሓት ያኔ የፈጸመውን የአሸባሪነት ተግባር ላሁኑ እንደ ግብዓት ያነሳሉ። ሆኖም ቆየት ብሎ የታተመው የዊኪሊክስ (ሹልክ ዓምድ) ዘገባ ፍንዳታውን አቀነባብሮ ያከናወነው ህወሓት ስለመሆኑ እዚህ ላይ በዝርዝር አስረድቷል። ከበረሃ ጀምሮ ማሸበር ሙያው የሆነው ህወሓት ሥልጣን ይዞም ይህንኑ በደም የተነከረ ታሪኩን ቀጥሎበታል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትላንት (ማክሰኞ) በመደበኛነት ከያዛቸው አጀንዳዎች አስቀድሞ በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ግፍና ጭፍጨፋ ላይ ውይይት አድርጓል።
ምክር ቤቱ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን ማንነትን መሰረት ያደረገው ጭፍጨፋ ላይ የተሰማውን ሀዘን በመግለፅ እና የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማድረግ መደበኛ ውይይቱን ሊያደርግ ቢያስብም አባላቱ ቅድሚያ ሊሰጥ የሚገባው የዜጎች ህይወት በመሆኑ ውይይቱ ከዚህ እንዲጀምር በሚል በጉዳዩ ላይ በስፋት ተወያይቷል።
የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤው አቶ ታገሰ ጫፎ ምክር ቤቱ አጀንዳውን ቀድሞ ቀርፆ የተዘጋጀ መሆኑን በመጥቀስ በዜጎች ላይ የተፈፀመውን ጥቃት በሚመለከት ትናንት ማምሻውን የምክር ቤቱ አመራር ምክክር አድርጎበት አስፈፃሚው አካል ማብራሪያ እንዲሰጥበት ውሳኔ ላይ መደረሱን አንስተዋል።
ይህንን ተከትሎሞ በጉዳዩ ላይ የምክር ቤቱ አባላት ሀሳብ እንዲሰጡበት ተደርጓል።
በዚሁ መሰረት ህወሓትን ጨምሮ ጥቃት የሚፈፅሙ ህገ ወጥ ቡድኖችን በሽብርተኝነት በመበየን የማያዳግም እርምጃ እንዲወሰድባቸው የሚል ሀሳብ ቀርቧል።
ምክር ቤቱ በጉዳዩ ዙሪያ በስፋት ከተወያየ በኋላ አስፈፃሚው አካል ምክር ቤት ቀርቦ ማብራሪያ እንዲሰጥ፣ ምህረት የሌለው እርምጃ እንዲወሰድ እና ችግሩ እንዳይደገም ምን መወሰን አለበት በሚለው ጉዳይ ላይ የውሳኔ ሀሳብ እንዲቀርብ አቅጣጫ አሳልፏል ሲል የዘገበው ኤፍቢሲ ነው።
ሰሞኑን ማንነትን በማተኮር የተካሄደውን ጭፍጨፋ በተመለከተ የምክር ቤት አባላት በስሜት የተናገሩበት ቪዲዮ ከዚህ በታች ቀርቧል፤
ጎልጉል
- የአምነስቲ ” ሽንቁረ ብዙ” ሪፖርት የተከፋዮች የቲውተር ዜና ድምርአገር መከላከያ ባላሳበው መንገድ ተጨፍጭፏል። በመኪና ተጨፍልቋል። እንደጠላት ” ሌባ ” እየተባ ባዶ እግሩን መሳሪያ ተወድሮበት ተተፍቶበታል፤ ብወልቃይት ጠገዴ፣ በራያ የሚኖሩ ሰዎች ላይ የተፈጸመው ግፍ፣Continue Reading
- Ministry Urges Amnesty Int’l to Use Appropriate Sources in Report to Uncover the TruthAmnesty International should use appropriate sources in its report to uncover the truth regarding allegations related to the incidents in the city of Axum, accordingContinue Reading
- Ethiopia: Eritrean troops’ massacre of hundreds of Axum civilians may amount to crime against humanityAmnesty International interviewed 41 survivors and witnesses to mass killings in November Troops carried out extrajudicial executions, indiscriminate shelling and widespread looting Satellite imagery analysisContinue Reading
- በትግራይ 3.5 ሚሊዮን ተረጂዎች የዕለት ቀለብና ተመሳሳይ እርዳታ እየተደረገላቸው ነውበትግራይ ለ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች የዕለት ደራሽ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎች እየተደረገ መሆኑን የብሄራዊ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ በክልሉ በነበረው ህግ ማስከበርContinue Reading