ቁጥራቸው 16 የሆኑ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ውስጥ የነበሩ የህወሃት መኮንኖች ወደ ጅቡቲ ቢኮበልሉም ጅቡቲ ለኢትዮጵያ መንግሥት ተላልፈው እንደተሰጡ ተነገረ።
የጅቡቲ ዜና ወይም Les Nouvelles de Djibouti በድረገጹ ይፋ ያደረገው ዜና ርዕስ “የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ወታደሮችን ጅቡቲ ለኢትዮጵያ አሳልፋ ልትሰጥ ነው” የሚል ነበር።
ይህ አሳልፎ የመስጠት ስምምነት የተፈረመው እኤአ በመጋቢት ወር 2017 ነበር። በወቅቱ ኢትዮጵያን ይጎበኙ በነበሩት ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጉሌህና ጠቅላይ ሚኒስትር በነበረው ኃይለማርያም ደሳለኝ መካከል ነበር።
በስምምነቱ መሠረት ማንኛውም “ወንጀለኛ፣ አሸባሪ” ተብሎ የተጠረጠረና ከአንዱ አገር ወደሌላው ጥገኝነት ለመጠየቅ የሄደ አገራቱ አሳልፈው እንዲሰጡ የሚያደርግ ነበር።
ይህንን ስምምነት በዋንኛነት የፈለገው ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር በማለት የሚጠራው የበረኻ ወንበዴዎች ቡድን ነበር። ቡድኑም በአገር ወስጥ የሚነሳበትን ተቃውሞ በማፈን በእጅጉ የተካነ በመሆኑ ከአገር ውስጥ አምልጠው ወደ ጎረቤት አገራት የሚሄዱትን በቁጥጥሩ ሥር ለማዋል ያደረገው እንደነበር ይታወቃል።

በዚህ ስምምነት ምክንያት የፖለቲካ አቋማቸው ከወንበዴው ህወሃት ጋር ያልተስማማ ተቃዋሚዎች በሙሉ እየተያዙ ተላልፈው ሲሰጡ መቆየታቸው ይታወቃል። ህወሃት በተመሳሳይ የኬንያን ድንበር በመጣስ ተመሳሳይ ተግባራት ሲፈጽም እንደነበር ይታወቃል።
ከሁለት ቀናት በፊት (ማክሰኞ) የፖለቲካ ጥገኝነት ለመጠየቅ ወደ ጅቡቲ የሄዱት 16 የህወሃት ወታደሮች መካከል አንድ ኮሎኔል፣ አንድ ኮማንደር እና 12 ሌፍተናንቶች እንደሆኑ ዜናው ሲዘግብ ሁሉንም የትግራይ ተወላጆች መሆናቸውን በመጥቀስ ነበር።
ግለሰቦቹ ወደ ጅቡቲ ከገቡ በኋላ በጅቡቲው የሰነድና ደኅንነት አገልግሎት ምርመራ የተካሄደባቸው ሲሆን በነጋታው ማለትም ረቡዕ ማምሻው ላይ በጅቡቲ አየር ኃይል ተጭነው ወደ ኢትዮጵያ ተላልፈው ሲሰጡ ድርጊቱን ተቃውመው እንደነበር ዜናው ዘግቧል።
ጅቡቲ ኒውስ ዘገባውን ሲያጠናቅቅ “እነዚህ ግለሰቦች አዲስ አበባ የነበሩና ከህወሃት ጋር ሲሠሩ የቆዩ” መሆናቸውን በመጥቀስ ነበር።
አስራ ስድስቱ ከሃዲዎች ረቡዕ ዕለት አመሻሹ ላይ ወደ አዲስ አበባ ተጭነው በመጡበት ወቅት በጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሙሀመድ አሊ ዮሱፍ የተመራ ከፍተኛ የልኡካን ቡደን ረቡዕ ማምሻውን አዲስ አበባ መግባቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መዘገቡ ይታወሳል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
- የአምነስቲ ” ሽንቁረ ብዙ” ሪፖርት የተከፋዮች የቲውተር ዜና ድምርአገር መከላከያ ባላሳበው መንገድ ተጨፍጭፏል። በመኪና ተጨፍልቋል። እንደጠላት ” ሌባ ” እየተባ ባዶ እግሩን መሳሪያ ተወድሮበት ተተፍቶበታል፤ ብወልቃይት ጠገዴ፣ በራያ የሚኖሩ ሰዎች ላይ የተፈጸመው ግፍ፣Continue Reading
- Ministry Urges Amnesty Int’l to Use Appropriate Sources in Report to Uncover the TruthAmnesty International should use appropriate sources in its report to uncover the truth regarding allegations related to the incidents in the city of Axum, accordingContinue Reading
- በትግራይ 3.5 ሚሊዮን ተረጂዎች የዕለት ቀለብና ተመሳሳይ እርዳታ እየተደረገላቸው ነውበትግራይ ለ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች የዕለት ደራሽ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎች እየተደረገ መሆኑን የብሄራዊ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ በክልሉ በነበረው ህግ ማስከበርContinue Reading
- ሱዳን ክፉኛ ተመታ የወረረችውን መሬት ማስረከቧ ተረጋገጠ፤ ከዱላው በሁዋላ ” ከኢትዮጵያ ጋር መረዳዳታን መልካም ግንኙነት እንሻለን” አለችኢትዮጵያ በወረራ የተወሰደባትን መሬት በሃይል ማስመለሷን ተከትሎ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ድርድር እንደምትፈልግ አስታወቀች። የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን ጠቅሶ ብሉምበርግ እንደዘገበው፣ ሚኒስትሩ ” ከኢትዮጵያ ጋር መልካምContinue Reading