“Our true nationality is mankind.”H.G.

አዲስ አበባ ከ2000 በላይ ጥቆማ ተሰጠ፤10 አመራሮች ተይዘዋል፤ አዲስ አበባ መታወቂያ መስጥት ተከለከለ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በአንድ ቀን ብቻ ከሁለት ሺህ በላይ ጥቆማዎችን ለመንግስት የጸጥታ አካላት በስልክና በአካል ማቅረቡን፣ ከጥቆማዎቹ ውስጥ ዘጠና በመቶ የሚሆኑት ትክክለኛ መረጃ ሆነው መገኘታቸው ተገለጸ።

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት የመንግስትን ጥሪና የወቅቱን ሁኔታ በማገናዘብ ሕዝቡ የሰጠውና እየሰጠ ያለው ምላሽ የሚደነቅ ነው።

በዚህም የጸጥታ ሃይሉ በርካታ የጥፋት ሃይሎችን በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉንና ህዝቡ ስራውን አብሮ መስራቱን አወደሰዋል። የኢትዮጵያን ህዝብ የማይመጥን በርካታ ክፉ ተግባራት ሲፈጸሙ እንደነበር አስታውሰው ይህንኑ ክፉ ተግባር ለማከናወን ከጥፋት ሃይሉ ህወሃት ተልዕኮ ወስደው አገር ሊያተራምሱ ሲነቀሳቀሱ የነበሩ ተይዘዋል።

በአዲስ አበባ 240 የሚሆኑ የትግራይ ተወላጅ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች እንደነበሩ ያስታወሱት አዳነች አቤቤ ከእለት እለት ኢትዮጵያዊ ይሆናሉ ተብሎ፣ ከቀን ወደ ቀን ራሳቸውን ከለውጡ ጋር ያስታርቃሉ በሚል ዝም ቢባሉም አስር ያህሉ ከሽብር ተልዕኮ ፈጻሚዎች ጋር ሆነው ሲሰሩ በህዝብ ጥቆማና በመረጃ ሰራተኞች ተደርሶባቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አመልክተዋል።

Related stories   የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤

የተወሰኑ ከሃጂዎች ተያዙ ማለት በከተማዋ ያሉትን ሰላማዊ የትግራይ ተወላጆች እንደማይወክል የገለጹት ምክትል ከንቲባዋ ከትግራይ ተወላጆች ጋር ተከታታይ ውይይት እየተደረገ መሆኑንንም ገልጸዋል።

ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ያልተገባ ጥቅም ለማግበስበስ ሸቀጥ ደብቀው በውድ ለሚሸጡ ነጋዴዎች ከጥፋት ሃይሎች ያልተናነሰ ተግባር የመፈጸም ያህል ነው። ሃያ አምስት ድርጅቶች ህጋዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ከንቲባዋ አስታውቀዋል። ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው መኖራቸውን አስታውሰው፣ ገንዘብ ለመሰብሰብ በሚል ይህንን አጋጣሚ ለአጉል ተግባር ለመጠቀም በሚንቀሳቀሱ ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወሰድ በግልጽ አስታውቀዋል።

በአሁኑ ወቅት በብዛት መታወቂያ እየተጠየቀ በመሆኑ የመታወቂያ መስጠት ለጊዜው ለጥንቃቄ ሲባል መታገዱን አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።  አገር ከብሄርና ከጎሳ በላይ በመሆኑ ይህንን ጊዜ አመራሮች በጀግንነት አኩሪ ተግባር በመፈጸም የደጀን ሃይል እንዲሆኑ ጥሪ አቅረበዋል።

በሌላ ዜና

በደቡብ ክልል በተለያዩ ዞኖች ህገወጥ የጦር መሳሪያ ሲያዘዋውሩ የነበሩ ሰባት ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ፖሊስ አስታወቀ።
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኢንስፔክተር እታገኘሁ ዜና ለኢዜአ እንደተናገሩት፥ ባለፉት ሁለት ቀናት በደቡብ ኦሞ፣ ካፋ፣ ኮንሶና ሸካ ዞኖች በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ 25 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣ 4 ሽጉጦችና 11 ተተኳሽ ጥይቶች ተይዘዋል።
እነዚህን ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች ሲያዘዋውሩ የነበሩ ሰባት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ እንደሚገኝም አስታውቀዋል።
ከተያዙት ተጠርጣሪዎች መካከል በደቡብ ኦሞ ጂንካ ከተማ ሁለት ግለሰቦች የአዕምሮ ህመምተኛ መስለው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ እንደሚገኙበት ገልጸዋል።
ግለሰቦቹ በህብረተሰቡ ጥቆማ ተይዘው ምርመራ ሲደረግባቸው ስድስት ሞባይል ስልክና 11 የተለያየ የባንክ የሂሳብ ደብተሮች እንደተገኘባቸውም ተናግረዋል፡፡
ህወሓትና ሀገር ለማፍረስ የሚሯሯጡ ቡድኖች በተለያዩ አካባቢዎች የህዝብን ሠላም ለማደፍረስ የሚያደርጉትን ጥረት ለማክሸፍ የክልሉ የጸጥታ ሀይልና ህብረተሰቡ በተቀናጀ መልኩ እየሰሩ ነውም ብለዋል።
ህብረተሰቡ አካባቢውን በንቃት እንዲከታተልና የሚያጠራጥር ጉዳይ ሲገጥመው በአካባቢው ለሚገኝ የጸጥታ ሀይል እንዲጠቁም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

 

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0