ከአፍሪካ ህብረት በፊት ጫና ፈጥራ የህግ ማስከበር ዘመቻውን እንድታስቆምላቸው ተጠይቃ የነበረችው ቻይና ” ስራቹህ ያውጣቹህ” የሚል አጭር ምላሽ መስጠቷን ተቀማጭነታቸው በአውሮፓ የሆነ ዲፕሎማት ለዛጎል ገለጹ። ስዩም መስፍን ዘመቻው ከመጀመሩ ሳምንት በፊት መሰወራቸው ተሰማ።
ራሱን የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር በሚል ስም ሰይሞ በኢትዮጵያ ላይ የመንግስትነት እርካቡን ለሃያ ሰባት ዓመታት ጨብጦ የነበረው ቡድን ከስልጣን ከተባረረ በሁዋላ የገጠመውን የፖለቲካ ሽንፈት ለማስመለስ የመረጠው መንገድ ዛሬ ለገባበት አጣብቂኝ ዳርጎታል። በዚሁ የስልታን ዘመኑ ከቻይና ጋር በድርጅት ደረጃ መስርቶት የነበረውን ግንኙነት ተጠቅሞ ለቻይና “የአደራድሪኝ” ጥያቄ ማቅረቡን ነው ዲፖሎማቱ ያስታወቁት።
እሳቸው እንደሚሉት ስዩም መስፍን በቻይና በነበራቸው ቆይታ ከዘረጉት ግንኙነት ጋር ተያይዞና ስማቸውን ያልጠቀሷቸው አንድ የትህነግ የቀድሞ አባል አሁን ያሉበትን ወንበርና የግል ግንኙነታቸውን በመጠቀም ቻይና ኢትዮጵያ ላይ ተጽዕኖ እንድታደርግ ተማጽነዋል። በአካልም ሄደው ሰፊ ንግግር አድርገዋል።
ቻይና ጥያቄውን እንደማታስተናግድ በገሃድ መግለጿንና ይህንንም ለመንግስት በይፋ ማስታወቋን፣ በዚህም መንግስት ምስጋና ማቅረቡን ዲፕሎማቱ አመልክተዋል። እሳቸው እንደሚሉት ትህነግ ለበርካታ አገራትና ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ደብዳቤ በትኗል። ኢትዮጵያ እንደምትበታተንና ምስራቅ አፍሪቃ እንደሚናወጥ በመጥቀስ መንግስት ላይ ተጽዕኖ ተደርጎ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ቀደም ሲል ጀመሮ ውስወሳ ሲያካሂዱ እንደነበር ያስታወሱት ዲፕሎማቱ፣ አንዳንዶቹ አገራት የደረሳቸውን ደብዳቤና መልዕክት ይልኩላቸው እንደነበር ገልጸዋል።
በተያያዘ ዜና “ኢትዮጵያን ለመውጋት ከብጽ ጋር ገጥመን እንሰራለን” በማለት በትግራይ መገናኛ በይፋ የተናገሩት ስዩም መስፍን የመከላከያ ሰራዊት ላይ የተፈጸመው በዕቅድ የተከናወነ ክህደት ከመፈጸሙ አንድ ሳምንት በፊት ራሱን መሰወሩ ለትህነግ ቅርብ የሆኑ እየጠቆሙ ነው። እነዚህ ወገኖች እንደሚሉት ስዩም መስፍን የሱዳን ድንበር ከመቀርቀሩ በፊት ነው ራሱን የሰወረው። ጠቋሚዎቹ ይህን ቢሉም ራሱ መስፋንም ሆነ ሌሎች የትህነግ ሰዎች እስካሁን ፍንጭ አልሰጡም።
በሌላ ዜና በቅርቡ የደህንነት አማካሪ ሆነው የተሾሙት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ወደ ሱዳን አምርተዋል። ገዱ ሱዳን የሄዱበት ምክንያት በይፋ ባይገለጽም ከዚሁ ከፍርጠጣ ጋር በተያያዘ እንደሆነ ግምት የሚሰጡ አሉ።
- በትግራይ የፖሊስ አባላት ተሃድሶ ወስደው ወደ ስራ እየተመለሱ ነውየአጭር ጊዜ የተሃድሶ ስልጠና የተሰጣቸው የትግራይ ክልል ተወላጅ ፖሊስ አባላት በትግራይ ክልል ህዝብን እንዲያገለግሉ ስምሪት መስጠቱን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። ዛጎል ምንጮቹን ጠቅሶ የተሃድሶ ስልጠናContinue Reading
- ከዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ በወቅታዊ ጉዳዮች እና በምርጫ 2013 ዙሪያ የተሰጠ መግለጫኢዜማ እንደሀገር ያለንበት ሁኔታ እና መጪው ሀገራዊ ምርጫ የሁሉንም ባለድርሻ አካለት በኃላፊነት መንቀሳቀስ እና ሀገራችንን ወደ ተረጋጋ ሁኔታ የምንቀይርበት ሊሆን ይገባል ብሎ ያምናል። በዚህ መግለጫContinue Reading
- Sudanese Delegation in Chad to Discuss Ties, Dispute with EthiopiaDeputy Chairman of the Sovereign Council in Sudan Mohamed Hamdan Dagalo, also known as Hemedti, arrived in the Chadian capital Saturday with an accompanying delegationContinue Reading
- የስምንተኛው ጉዞ አድዋ የሽኝት መርኃግብር እየተካሄደ ነው።– 125ኛውን የአድዋ ድል ለመዘከር መነሻቸውን አዲስ አበባ አድርገው መዳረሻቸውን ደግሞ አድዋ ተራሮችን የሚያደርጉ 125 ወጣቶች ( 107 ወንዶችና 18 ሴቶች) በጉዞው ላይ ይሳተፋሉ። –Continue Reading