በርካታ ፈቃደኞች የህግ ማስከበር ዘመቻውን ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን በፍጥነት ለማጠናቀቅ ጥያቄ እያቀረቡና እየተቀላቀሉ ባለበት በአሁኑ ሰዓት ጎን ለጎን በርካታ አካባቢዎች ከትህነግ ቁጥጥር ውጪ መደረጋቸው እየተገለጸ ነው። ዛሬ በወጣው መረጃ አክሱም አየር ማረፊያ ሙሉ በሙሉ በወገን እጅ ገብታለች።
ሌፍተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ በትናትናው እለት በሰሚን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ የተፈጸመውና ” ሰይጣን ይሻላል” ያሰኘውን ጭካኔ የተሞላው የክህደት ተግባር ሲያስረዱ ነገና ዛሬ በርካታ ድሎች ይፋ እንደሚሆን ፍንጭ ሰጥተው ነበር። ጀነራሉ ሕዝብን ባስቆጣውና እልህ ውስጥ በከተተው መግለጫቸው ሰራዊቱ የተፈጸመበትን ክህደትና ጭፍጨፋ ተቋቁሞ ዳግም በመደራጀት ማጥቃት መቀጠሉንም በይፋ አስታወቀው ነበር።
ዛሬ ማለዳ ላይ እንደተሰማው የአክሱ አየር ማረፊያና ከተማዋ ሙሉ በሙሉ ” ጁንታ” በሚል ስያሜ ከሚጠራው የትህነግ መዳፍ ተላቃለች። ጁንታው በአክሱም አየር ማረፊያ አካባቢ ጠንካራ ምሽግ የገነባና ሰፊ የመከላከያ መስመር ያደራጀ በመሆኑ ከባድ ትንቅንቅ መደረጉን መረጃዎች ያስረዳሉ።
የጥቃቱን ስፋራ በዝርዝር ባይገልጹም የአየር ሃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄነራል ይልማ መርዳሳ ” እንዳሻን እየተመላለስን ደብድበናል” በማለት ጁንታው ያከማቸው የጦር መሳሪያና የነዳጅ ዲፖ እንዲሁም የተመረጡ ኢላማዎች ከጥቅም ውጭ እንደሆነ ዛሬ ለመንግስት ሚዲያዎች ተናግረዋል። ጥቃቱ ጁንታው እጁን እስኪሰጥና የህግ ማስከበሩ ስራ እስኪተናቀቅ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል። ጀነራሉ የጁንታው አፈ ቀላጤ አየር መተን ጥለናል በሚል ላሰራጨው ዜና ” እንዳሻን በመመላለስ ደብድበናል። ህዝብ እንዳይነካ በሚል ቦታው ላይ ደርሰን ድብደባ ሳንፈጽም ተመልሰናል” ሲሉ በአየር ክልሉ ላይ አየር ሃይሉ ምን ያህል እንደተንሸራሸረ በመግለጽ ተሳልቀውበታል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ
- “ፍትህ ለትግራይ! ሞት ለመከላከያ ሰራዊትና … በትግራይ ሕዝብ ስም ትህነግ የመዘዙ ምንጭ ላይሆን?ድሮ ገና በፊት የወደፊቱ የታያቸው ” በስሜ አታድርጉት በሉዋቸው” ሲሉ እያለቀሱ ለምነዋል። ጀርመኖች አይሁዶችን ሲጨፈጭፉ ነበር የወደፊቱ የታያቸው ጀርመኖች ” do not do it byContinue Reading
- የአምነስቲ ” ሽንቁረ ብዙ” ሪፖርት የተከፋዮች የቲውተር ዜና ድምርአገር መከላከያ ባላሳበው መንገድ ተጨፍጭፏል። በመኪና ተጨፍልቋል። እንደጠላት ” ሌባ ” እየተባ ባዶ እግሩን መሳሪያ ተወድሮበት ተተፍቶበታል፤ ብወልቃይት ጠገዴ፣ በራያ የሚኖሩ ሰዎች ላይ የተፈጸመው ግፍ፣Continue Reading
- Ministry Urges Amnesty Int’l to Use Appropriate Sources in Report to Uncover the TruthAmnesty International should use appropriate sources in its report to uncover the truth regarding allegations related to the incidents in the city of Axum, accordingContinue Reading
- Ethiopia: Eritrean troops’ massacre of hundreds of Axum civilians may amount to crime against humanityAmnesty International interviewed 41 survivors and witnesses to mass killings in November Troops carried out extrajudicial executions, indiscriminate shelling and widespread looting Satellite imagery analysisContinue Reading