የመከላከያ ሠራዊታችን በአድዋ ተምቤን መሥመር ማይቅናጥል በተባለውና ልዩ ስሙ ሰላስል በተሰኘው የሐውዜን ተምቤን መገንጠያ መንገድ የገጠመውን የጁንታውን ኃይል ሙሉ በሙሉ ተደመሰሰ። በዚሁ መገንጠያ ላይ የሠራዊቱን ግሥጋሴ ለመግታት በኮሎኔል ጸጋዬ ማርክስና በኮሎኔል ሸሪፎ የሚመራው የጁንታው አንድ ክፍለ ጦር ነው በሙሉ የተደመሰሰው። የጁንታው አንድ ክፍለ ጦር 2500 አባላት የሚዋቀር ነው ተብሏል።
የመከላከያ ዘመቻ ዋና መመሪያ ማምሻውን እንዳስታወቀው ፣ የመከላከያ ሠራዊታችን ክፍለ ጦሩን ሙሉ በሙሉ ከደመሰሰ በኋላ ወደ መቀሌ የሚያደርገውን ጉዞ አጠናክሮ ቀጥሏል።
ከዚሁ ድል ተያይዞ “”የማንም የመንደር ወመኔ ቡድን ሀገር ሊያፈርስ አይችልም።… ይህ ቡድን መጥፋት አለበት…የወያኔ ቡድን ሞቶም ሊያወራ ይችላል።” ሲሉ ሹመት ከድል በሁዋላ ያሉት ሌ/ጄ አበባው ታደሰ አድዋ ተራሮች ሆነው መልዕክት አስተላልፈዋል።
በሌላ በኩል ጁንታው የህወሐት ቡድን የሰራዊታችንን ሕግ የማስከበር እርምጃ መቋቋም እንደተሳነው የመከላከያ ህብረት ዘመቻ ዋና መምሪያ ኃላፊ ብ/ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ተናገሩ።
ጄኔራል መኮንኑ የሠራዊታችንን ፈጣን የማጥቃት እንቅሰቃሴን አስመልክተው በካርታ የደገፈ ገለፃ አድርገዋል። ፅንፈኛው የህወሃት ቡድን የሠራዊታችንን ወቅታዊ አቋም በተሳሳተ መንገድ ገምግሞ በድሮ የጫካ ስሌት ወደ ውጊያ በመግባቱ ለውርደት ተዳርጓል ብለዋል።
ብ/ጄ ተስፋዬ አክለውም ፅንፈኛው ቡድን ልዩ ኃይል ብሎ የሚጠራውን ታጣቂና ሚሊሻውን ከፊት አሰልፎ ከሰራዊቱ በተለያየ ምክንያት የወጡ ከሃዲያንን ከኋላ በማሰለፍ በግዴታ እንዲዋጉ እያደረገ ነው ብለዋል።

ፅንፈኛው የህወሃት ጁንታ ህዝቡን ከመናቁ የነተነሳ የልማት አውታሮችን እያወደመ እንደሚገኝ ተናግረው ይህም የሽንፈቱ ማሳያ ነው ሲሉ ገልፀዋል ። በምስል እንደታየው ጁንታው የአክሱም አየር ማረፊያን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ አፈራርሶታል። ይህ የተስፋ መቈርጡ መገለጫ የሆነው ተግባሩ ” ሲመጣ አፍርሶ፣ ሲሞት በመጣበት መንገድ አፍርሶ” የሚከስም እንደሆነ አመላክቷል። ከፍተኛ መኮንኖች ሽንፈት ሲከናነብ መሰረተ ልማት አፍርሶ ከፈረጠጠው የዚያድባሬ ሃይል ጋር አመሳስለውታል።

ጁንታው ከአሁን በኋላ ያለው ብቸኛው አማራጭ ተዋግቶ መሞት አሊያም እጅ መስጠት ብቻ ነው ብለዋል። ሲል የመከላከያ ሰራዊት በማህበራዊ ገጹ አመልክቷል።
ምስል – የፈራረሰው አክሱም አየር ማረፊያ
- “የትግራይ ልሂቃን የት ገቡ? ዳያስፖራው ለቆሰቆሰው፣ ወያኔ ላነደደው እሳት ማን እንደሚጠየቅ ለምን ፊትለፊት አይናገሩም ? “አስመሮም ጣይቄ አለው። ጥያቄው በቀጥታ ለትግራይ ልሂቃኖች ነው። ” የትገቡ” ይላል። ” ዳያስፖራው ለቆሰቆሰው፣ ወያኔ ላነደደው እሳት ማን እንደሚጠየቅ ለምን አይናገሩም” አስከትሎም “የኢትዮጵያ ሕዝብ ሃያContinue Reading
- ብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሃሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ ማህበራዊ አንቂዎችን ” አደብ ግዙ” ሲል አስጠነቀቀበተያያዘ ዜና ሰሞኑን ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብታቸውን ያላግባብ ተጠቅመው አገልግሎት መሥሪያ ቤቱን በተመለከተ ሃሰተኛ መረጃዎችን በማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው በማሰራጨት ህብረተሰቡን ለማደናገር ሲሞክሩ የነበሩ አንዳንድ የማህበራዊContinue Reading
- Sudanese protest in Khartoum over bread shortages(KHARTOUM) – Hundreds of people demonstrated in different areas in the Sudanese capital on Saturday to protest breadlines and fuel shortages. Hundreds of protesters marchedContinue Reading
- አትሌት ለተሰንበት ግደይ በቶክዮ ኦሎምፒክ ትሳተፉለች!!“በትግራይ ክልል በነበረው ግጭት የአትሌቷ ልምምድ ተስተጓጉሎ ይሆን?” የሚል ጥያቄ ከኢትዮጵያ ቼክ የቀረበለት አልጣኝ ሀይሌ “በነበረው ችግር ምክንያት አርፍደን መጥተናል። እኛ የነበርነው ደቡባዊ ትግራይ አካባቢContinue Reading