ሁሌም ስሉሱ ከዞረ ዞረ ነው። ዛሬ ትህነግ ላይ የጠለቀችው ጀንበር እየጎተተች ያለችው አጀንዳ ቀደም ሲል ዜጎች የጮሁበት፣ ያነቡበት፣ የተሟገቱበት፣ በብርድና በሃሩር የተሰለፉበት፣ ፍትህን የወተወቱበትን ጉዳዮች ነው። ከእነዚህም መካከል የዓለም የጤና ድርጅትን እየመሩ ያሉት የዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ጉዳይ በዓለም መገናኛዎች ጨሶ እየሸተተ ነው። ለውጡን የሚመራው መንግስትም መረጃ ለመስጠት የሚያቅማማ አይመስልም።
ኢትዮጵያዊነትን ካወደመው፣ የዘር ፖለቲካን ሲያራምድ ከነበረው ፍጹም ጽንፈኛና ዘረኛ፣ እንዲሁም በከፍተኛ ደረጃ ኢትዮጵያውያንን በዘራቸው፣ በፖለቲካ እምነታቸው ካኮላሸ፣ ከጨፈጨፈ፣ ቶርቸር ካደረገ፣ በጅምላ ሴቶች እንዲደፈሩና ከነነፍሳቸው ለአውሬ እንዲጣሉ ካደረገ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር/ትህነግ የተቀዱት ቴድሮስ አድሃኖም የሕዝብ ዓመጽ በጋመበት ወቅት ” እኔ ወያኔ ነኝ” ሲሉ ድጋፋቸውን ሃይል ይጠቀም ለነበረው ወካጃቸው ትህነግ ሲሰጡ ነበር።
የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት ሦስት የኮሌራ ወረርሽኞች በምሥጢር እንዲያዙ ማድረጉ ለዓለም ጤና ድርጅት ተወዳዳሪነት አያበቃቸውም በሚል ጉዳይን “የጥቅምት ዱብ ዕዳ” አድርጎ ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ ሜይ 13- 2017 ዓም ሲዘግብ “የዓለም ጤና ጥበቃ ድርጅትን ለመምራት የሚወዳደረው እጩ ወረርሽኝ በመደበቅ ተከሰሰ” በሚል ርዕስ ነበር።
ዓለም በውቅቱ ችላ ያለው ነገር ግን በቴዎድሮስ አድሃኖም የጤና ጥበቃ ሚኒስትርነት ዘመን በአማራ ምስኪኖች ላይ ዘራቸውን የማምከን ወንጀል ስለመፈጸሙ በመረጃ የተደገፈ ሪፖርት ይፋ ነበር። ሁሉም ታልፎ እሳቸውም በዚህ ታላቁ የዓለም የጤና ድርጅት ወነበር ላይ ቢቀመጡም ከትህነግ ጋር ያላቸው የልጅነት ስሜት ግን ቦታው ከሚጠይቀው የዲሲፒሊን ህግ ውጪ እያስኬዱት እንደሆነ ቅርብ ጊዜ መረጃ መጥቶባቸው ነበር።
ለተጨማሪ መረጃ ይህንን ያንብቡ –የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!?
እንደ መረጃው ከሆነ ሃላፊነታቸውን በመጠቀም ዓለም ዓቀፍ ተቋማት የትህነግን አመራሮች ከመንግስት ጋር አሸማግሎ ወደ እርቅ እንዲያመጣ የሚችሉትን አድርገዋል። ቻይና ” ዞር በሉ” እንዳለቻቸው ዛጎል ዘግባ ነበር። ከተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ ሃላፊዎች ጀምሮ በጎንና በቁም በርካታ ድንጋይ ሲፈነቅሉ የነበሩት ቴዎድሮስ በስተመጨረሻ በገሃድ ወጥተው ” ለሰላም ስል ነው። ስለማ ደግሞ የዓለም የጤና መርህ ነው” ሲሉ አንዳን ሙከራ ማድረጋቸው ሊወገዝ እንደማይገባ አመላክተው ነበር።
ይህቺን ሁለት ቀን በስፋት የተሰራጨው መረጃ ግን እሳቸው ” ስድብ መስላቹህ እንጂ እኔ ዛሬም ወያኔ ነኝ” እንዳሉት ” አዎ ወያኔ ነዎት፣ ይጠየቃሉ፤ የሚጠየቁትም በዓለም ዓቀፉ የወንጀለኞች መሞገቻ መድረክ ነው” የሚል ነው።