የ22 ዓመት ወጣት ነው፡፡ ትውልድና እድገቱ በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ሸዋ ዞን ግንደ በረት ከተማ ነው፡፡ ትምህርቱን ከስምንተኛ ክፍል አቋርጦ ሀገራችንን ነጻ እናውጣ እያለ በሚሰብከው ታደሰ ጆንሴ በሚባል ሰው አማካኝነት ለኦነግ ሰራዊትነት ተመልምሎ ጊንጪ አካባቢ ጭልሞ በምትባል ቦታ ከጥር 2012 ዓ.ም ጀምሮ ከ26 ባልደረቦቹ ጋር ስልጠና እንደወሰደ ይናገራል፡፡
ከስልጠና በኋላም ሁሉም ወደ መጡበት አካባቢ እንዲመለሱና ስልክ ሲደወልላቸው የሚፈለጉበት ቦታ ድረስ እንዲመጡ ትእዛዝ ተሰጣቸው፡፡ እንደተባለውም የሰሜን እዝ ሰራዊት ላይ ጥቃት ከመፈጸሙ አስቀድሞ ማንነቱን በማያውቀው ሰው አማካኝነት ስልክ ተደወለለት፡፡
በተባለው ቦታ ተሰባሰቡና ጉዟቸውን ወደ ትግራይ አደረጉ፤ በእግርም በተሸካርካሪም ከተጓዙ በኋላ ጨርጨር አካባቢ ከትግራይ ታጣቂዎች ጋር ተቀላቀሉ፡፡
ከጥቂት ቀናት በኋላ በሰሜን እዝ ሰራዊት ላይ ጥቃት እንዲፈጽሙ ትእዛዝ ተሰጥቷቸው እንደነበርና እርሱ ግን አለመሳተፉን ፈይሳ ይናራል፡፡ አመራሮች የትግሉ ዓላማ ሀገሪቱን ነጻ ለማውጣት እንደሆነ ይነግሯቸው እንደነበረር ይገልጻል፡፡
እንደ ፈይሳ ሁሉ በርካታ የኦነግ ታጣቂዎች ከጁንታው ጋር አብረው ተሠልፈው የነበረ ሲሆን፤ እጃቸውን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት መስጠታቸውን በስፍራው የሚኘገው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢ አረጋግጧል።
በኢያሱ መሰለ
(ኢ.ፕ.ድ)