የሁለቱ ምክር ቤት እንደራሴዎች የተሰጡትን የውክልና ድምጾች (ኤሌክቶራል ቮት) በመቁጠር ጆ ባይደን ቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸውን አረጋግጧል።

ኮንግረስ ጆባይደን እና ምክትላቸው ካምላ ሀሪስን ቀጣዮቹ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንት በማድረግ ያገኙትን ድምጽ አጽድቋል። የተሰጡት የውክልና ድምጾች የጸደቁት የሁለቱ ምክር ቤት ተወካዮች በፔንሰልቫንያ እና አሪዞና ግዛቶች የቀረበውን ተቃውሞ ውድቅ ካደረጉ በኋላ ነው

Related stories   አለቃ አጽመ ጊዮርጊስ – የተሳሳተውን የውጫሌ ውል የመረመሩ ጀግና ኢትዮጵያዊ

የአገሪቱ ሕዝብ እንደራሴዎች ተሰብስበው ቀጣዩ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የምርጫ ውጤት ዙሪያ በመነጋገር ላይ ሳሉ በድንገት በሺህ የሚቆጠሩ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች ምክር ቤቱን ሰብረው ገብተዋል።

በዚህም የተነሳ ተቋርጦ የነበረው የምክር ቤቶቹ የጋራ ስብሰባ ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ እንዲወጡ ከተደረገ በኋላ ቀጥሏል። ዋሺንግተን ውስጥ የተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች የአገሪቱን ምክር ቤት ጥሰው መግባታቸውን ተከትሎ በተፈጠረ ፍጥጫ አራት ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል።

Related stories   አለቃ አጽመ ጊዮርጊስ – የተሳሳተውን የውጫሌ ውል የመረመሩ ጀግና ኢትዮጵያዊ

በተቀሰቀሰው ግርግር ሳቢያ የዋሺንግተን ከንቲባ በከተማዋ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ የሰዓት እላፊ ገደብ ጥለዋል። የካፒቶል ሂል አካባቢም ሙሉ በሙሉ ዝግ እንዲሆን ተደርጓል።

ከጥቃቱ በኋላ ጆ ባይደን በቴሌቪዥን ቀርበው በቀጥታ ለሕዝባቸው ባደረጉት ንግግር”በአሜሪካ ዲሞክራሲ ላይ ጥቃት ተሰንዝሯል” ብለዋል። ተቀናቃኛቸው ትራምፕም በአስቸኳይ ወጥተው ውንብድና ላይ ያሉ ደጋፊዎቻቸውን አደብ እንዲያሲዙ ጠይቀዋል።

ካፒቶል ሒል በነውጥ ላይ እያለ ከዋሺንግተን ዲሲ በሚጎራበቱ ግዛቶች የአሜሪካ ወታደሮች በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ሆነዋል። የካፒቶል ሒል ፖሊሶችን ለመደገፍም ኤፍቢአይ ወደ ስፍራው ተሰማርቷል። BBC AMHARIC

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *