የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መሰተዳደር ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሀሰን መሀመድን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በገራድ ዊል ዋል አየር ማረፊያ በመገኘት ለባለሀብቶቹ አቀባበል አድርገዋል።
የነዳጅ ካምፓኒ ባለቤትና ስራ አስኪያጅ ሼህ ሀምዛ አብዲአዚዝ አል ሱኬሪያና የጊፍት ሪልዕስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ገብረእየሱስ ከክልሉ ምክትል ርዕስ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ጋር በክልሉ ስላለው ምቹ ኢንቨስትመንት ሁኔታመክረዋል፡፡
ምክትል ርዕስ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሉኡካን ቡድኑ በክልሉ ለሚያከናውናቸው የኢንቨስትመንት ስራዎች የክልሉ ህዝብና መንግስት ከጎናቸው እንደሚቆምም አረጋግጠዋል።
ባለሀብቱ ወደ ክልሉ የመጡበት ዋነኛ አላማ በክልሉ የኢንቨስትመንት መስክ ተሳትፎ ለማድረግ ሲሆን ቤቶች ግንባታ፣ በፀሀይ የሚሰራ የሶላር መገጣጠሚያ፣ የመኪና መገጣጠሚያ ዘርፍ ላይ ለመሰማራት ነው፡፡
በክልሉ በሪል እስቴት መስክ ያሉ ክፍተቶችን ለመቅረፍ የባለ ሀብቶቹ ድርሻ የጎላ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን የመገጣጠሚያ ካምፓኒዎቹ መገንባትም በኢኮኖሚው ረገድ ያለው ሚና የጎላ እንደሆነም ከክልሉ መገናኛ ቡዙሃን አጄንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።


Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *