በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንን አደጋ ውስጥ ለመክተትና ከሱዳን ሕዝብ ጋር አለመግባባት እንዲፈጠር የሃሰት መረጃ መለቀቁን መንግስት አስታወቀ። ኢትዮጵያዊያን ማንኛውንም መረጃ ከሱዳን ኢትዮጵያ ኤምባሲ ይፋዊ የድረ ገጽና የማህበራዊ አምድ ላይ ብቻ እንዲመከከቱ ወጋናዊ ጥሪም አሰምቷል። ፋጅት ቼክ የሚከተለውን ብሏል
“በካርቱም የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኤምባሲ በገዳሪፍ እና በካርቱም ግዛቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአስቸጋሪ ሁኔታዎች መሆናቸውን በመጥቀስ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እና ለኤምባሲው እንዲያሳውቁ በአረብኛ የተጻፈ ማስታወቂያ በማህበራዊ ሚዳያ እየተሰራጨ መሆኑን እየገለጸ ማስታወቂያው የሐስት መሆኑን ያሳውቃል።
ኤምባሲው እንደዚህ ያሉ ተገቢ ያልሆኑ ድርጊቶች በኢትዮጵያ እና በሱዳን ህዝቦች እና መንግስታት መካከል አለመግባባት ለመፍጠር እና ልዩነቶችን ለማራገብ በሚሹ አካላት እንደሚከናወን ይገንዘባል ፡፡
ኤምባሲው በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በተመሳሳይ የሐሰት መረጃዎች እንዳይሸበር እየጠቆምን ትክክለኛ እና ይፋዊ መግለጫዎችን ለማግኘት የኤምባሲውን ኦፊሴላዊ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ብቻ እንዲከታተሉ ይመክራል ፡፡
ጥር 7 ቀን 2013 ዓ.ም.
የኢትዮጵያ ኤምባሲ
ካርቱም”

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ጄኔራል ዮሐንስ ገብረ መስቀል – በትግራይ አስቸኳይ ጊዜ ግብረሃይል መሪ ሆነው ተሾሙ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *