zaggole news – እነ አቶ ስብሐት ነጋ ” ወንጀለኛ አይደለንም። በጊዜ ፍርድ ቤት እንድንቀርብ አልተደረገም ” ሲሉ ለፍርድ ቤት አስታወቁ። ፖሊስ በበኩሉ ከጥልቅ ሰርጥ ውስጥ መያዛቸው፣ በቁጥጥር ስር ውለው ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ መቆም የሚቸገሩ፣ መንፈሳቸው ያልተረጋጋና ህክምና የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ ሰብአዊነትን ማስቀደሙን አመልክቷል። አያይዞም የስነ ልቦና ግንባታ በማድረግ፣ ልብስ በማልበስና አስፈላጊ ህክምና እንዲያገኙ በማስቻል ጠንክረው ችሎት ፊት መብታቸው የሚፈቅደውን እንዲጠይቁ ማድረጉን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በምስል አስደግፎ እንዳሳየው ተጠርጣሪዎቹ ማስክ ቢያደርጉም ሪዛቸውን ተላጭተው፣ ቁመናቸው ተስተካሎ፣ በተሻለ ሁኔታ ላይ ታይተዋል። ይሁን እንጂ ሱፍ አልለበሱም።

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የቀረቡት ሃያ የሚሆኑ የትህነግ ከፍተኛ አመራሮችና አካላት መካከል  ቀደምትና አቶ ስብሃት ነጋ፣ አቶ አባይ ወልዱ፣ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር) እና ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ ታይተዋል። የክስ መዝገባቸውም ስማቸውን ያትታል። አቶ ዶክተር ሰለሞንና አቶ አባይ ወልዱ በሕመም ምክንያት አልቀረቡም።

Related stories   The National Movement of Amhara(NaMA) Denounces International Violations of the Sovereignty of Ethiopia

ሕገ መንግስቱን በሃይል በመናድ፣በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሠራዊት ላይ በተፈጸመው ጭፍጨፋ፣ የነዳጅ ዴፖ እንዲዘረፍ በማድረግ፣ ከተሰታቸው ስልታን ውጪ ከውጭ መንግስታት ጋር በመነጋገርና ላሳሰቡት ዓላማ ብር በማሰብሰብ፣ሮኬት ወደ ጎንደርና ባህር ዳር በመተኮስ ወዘተ ዘርዝሮ ክስ ያሰማው ፖሊስ ተጨማሪ የጊዜ ቀተሮ እንዲሰጠው ጠይቋል። ሌሎችም ተደራራቢ የወንጀል ተግባራት የሚፈለጉ መሆናቸውን መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ እንዳስረዳ ተገልጿል።

ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የህወሓት ኃይሎች በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና የፌደራል ፖሊስ በበርካታ የህወሓት ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራሮች ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣቱ ይታወሳል።

Related stories   Let’s See the Proof of “Ethnic Cleansing” in Ethiopia, New York Times!

ተጠርጣሪዎቹ በበኩላቸው ” ወንጀል አልፈጸምንም” ሲል በዋሻ ውስጥ ተደብቀው ሳለ በመከላከያ ሰራዊት አማካይነት መያዛቸውን አመልክተዋል። አክለውም ጎደለ ያሉትን ተናግረዋል። ከቤተሰብና ከጠበቃ ጋር መገናኘት እንዲፈቀድላቸው፣ ልብስና ምግብ እንዲገባላቸው የጠየቁ ሲሆን፤ ትግራይ ከተያዙ በሁዋላ ፍርድ ቤት ለመቅረብ ጊዜ መፍጀቱን ተቃውመዋል።

ቪዲዮውን 35 ደቂቃ ላይ ያድምጡ። ምስላችውን ይመልከቱ

ፖሊሰ በበኩሉ ከጉድጋድ ወይም ሰርጥ ውስጥ ሲያዙ ተጎሳቁለው መገነታቸው፣ በትግራይ ከነበረው ግጭትና የሰዓት እላፊ አንጻር ባስቸኳይ ፍርድ ቤት ማቅረብ አለመቻሉን ለችሎት አስረድቷል። ተጠርጣሪዎቹ ወደ አዲስ አበባ እንደመጡ ቆመው ለመሄድ የሚቸገሩ በመሆናቸው ፖሊስ የስነ ልቦና ድጋፍ እንዲያደረጉ ማገዙንም ተናግሯል። አያይዞም ሰብአዊነት መቅደም ስላለበት ልብስ አልብሶና አስፈላጊውን ህክምና እንዲያገኙ አድርጎ ዛሬ ራሳቸውን ችለው ችሎት ፊት እንዲቆሙ ጥንካሬ እንደፈጠረላቸው አብራርቷል።

Related stories   በኢትዮጵያ የትግራይ ጉዳይ ላይ የጸጥታው ምክር ቤት ሳይስማማ ተበተነ፤ አማራ ትህነግን በህግ ሊጠይቅ ነው

ችሎቱም ግራ ቀኙን ስምቶ ተጠርጣሪዎቹ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናኙ፣ ጠበቆቻቸውን እንዲያወያዩና ልብስና ምግብ እንዲገባላቸው ትዕዛዝ ሰጥቷል። ከክሱ ከባድነትና ውስብስብነት አንጻርም የተጠየቀውን የጊዜ ቀጠሮ ተቀብሏል።

በድምጸ ወያኔ ቲቪ ቀርበው መንግስትን ሲያወግዙ ለመጨረሻ ጊዜ የታዩትና በቅርቡ ተጨማሪ ልጅ ያገኙት የቀድሞዋ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሰብሳቢ ወ/ሮ ኬሪያ ከተሽከርካሪ ወርደው ወደ ችሎት ሲያመሩ ዛሬ በምስል ታይተዋል። ወይዘሮዋ ወደ ምሽግና ሰርጥ ሳይሄዱ እጃቸውን ለመከላከያ በመስጠት ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸው ይታወሳል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *