ዝነኛው አሜሪካዊ የቴሌቭዥን መርሀ ግብር መሪ ላሪ ኪንግ በ87 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ሎስ አንጀለስ ውስጥ በሚገኝ ካዳርስ-ሲናይ በተባለ ሆስፒታል ውስጥ ሕይወቱ እንዳለፈ ተገልጿል።
ለስድስት አሰርት ዓመታት ባዘጋጀው የቴሌቭዥን መርሀ ግብር ላይ ለበርካታ ታዋቂ ግለሰቦች ቃለ መጠይቅ አድርጓል። ለ25 ዓመታት በሲኤንኤን ላይ “ላሪ ኪንግ ላይቭ” የተባለ የራሱ መርሀ ግብር ነበረው። በፖለቲካው፣ በመዝናኛው፣ በስፓርቱና በሌሎችም ዘርፎች እውቅ ባለሙያዎችን በመሰናዶው አቅርቧል።
ላሪ ኪንግ በኮሮናቫይረስ ተይዞ ሆስፒታል ውስጥ ሕክምና ሲከታተል ነበር። ከባልደረቦቹ ጋር የመሠረተው ኦራ ሚዲያ በትዊተር ገጹ እንዳሰፈረው፤ “ላሪ ኪንግ ናው”፣ “ላሪ ኪንግ ላይቭ”፣ ”ፓሊቲኪንግ ዊዝ ላሪ ኪንግ” በተሰኙት ታዋቂ መሰናዶዎች ይታወሳል።
ምንጭ ቢቢሲ
(ኢ.ፕ.ድ)

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *